Thursday, 03 March 2022 06:51

የኮሮና ክትባት አንከተብም ያሉ ኡጋንዳውያን 1,139 ዶላር ወይም በ6 ወር እስር ሊቀጡ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በኡጋንዳ የኮሮና ክትባቶችን አንወስድም ያሉ ዜጎች የ1 ሺህ 139 ዶላር የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባቸውና፣ ቅጣታቸውን ያልከፈሉ ደግሞ በ6 ወር እስራት እንደሚቀጡ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የአገሪቱ ፓርላማ የኮሮናን ስርጭት ለመግታት ታስቦ የወጣውን ይህን አዲስ መመሪያ በቅርቡ ያጸድቀዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቆመው ዘገባው፤ አገሪቱ የኮሮና ክትባት መስጠት ከጀመረች አንድ አመት ያህል ቢሆናትም፣ ከ45 ሚሊዮን ህዝቧ መካከል የተከተበው 16 ሚሊዮን ያህል ብቻ መሆኑ መንግስት ጠበቅ ያለ ህግ እንዲያወጣ እንደገፋፋውም ገልጧል፡፡

Read 4425 times