Saturday, 05 March 2022 12:04

የኢትዮጵያ መንግስትና ህወኃት ለድርድር እንዲቀመጡ ቻይና ጥሪ አቀረበች

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

      የኢትዮጵያ መንግስትና ህወኃት ጦርነት አቁመው ለድርድርና ለውይይት እንዲቀመጡ የቻይና መንግስት ጥሪ አቀረበ።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን በሃገሪቱ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የማህበራዊ ድረ-ገጽ በኩል ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ መንግስት በራሱ ውሳኔ ጦሩን ወደ ትግራይ አለማስገባቱና  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳቱ የሚደነቅ ተግባር ነው ብለዋል።
 የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም አካታች ለሆነ ምክክር እየተዘጋጀ መሆኑንና  በሰሜን ያለውን ጦርነት ለማርገብ አዎንታዊ እርምጃዎች መውሰዱን ያደነቀው የቻይና የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት፤ ይህም የኢትዮጵያ መንግስት  ጦርነቱ በውይይት እንዲፈታ ያለውን  ፍላጎት  አመላካች ነው ብሏል።
ከህውኃት በኩልም ተመሳሳይ አዎንታዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ፤ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላትም ልዩነቶቻቸውን በውይይት  ለመፍታትና አገሪቱን ወደ ሰላምና ልማት ጎዳና ለመመለስ እንዲሰሩ የቻይና የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት  ጥሪ አቅርቧል።
የቻይና መንግስት በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት የሚደረጉ ውይይቶችንና ድርድሮችን በሁሉም ረገድ ለመደገፍ ዝግጁ ስለመሆኑም በመግለጫው ተመልክቷል። ጦርነቱ በአስቸኳይ ቆሞ ድርድር እንዲጀመርም ቃል አቀባይ ጽ/ቤቱ ጥሪውን አቅርቧል።


Read 11752 times