Saturday, 12 March 2022 12:26

የውጪ አገር ህክምናዎችን ለማስቀረት የሚያስችችል ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

     በአሁኑ ወቅት በአገራችን እየተሰጠ ያለውን የሕክምና አገልግሎት በአንድ ደረጃ ለማሳደግ ያስችላል የተባለለትና በውጪ አገር የሚሰጡ ህክምናዎችን በማስቀረት በአገር ውስጥ ለመስጠት ያስችላል የተባለለት ተርሸሪ ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው።
በመቅረዝ ጤና አገልግሎት አክስዮን ማህበር የተመሰረተው መቅረዝ ሆስፒታል በአገራችን የማይሰጡ የሕክምና አገልግሎቶችና በዘመናዊ የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች የታገዙ ምርመራዎችን ለማካሄድ የሚያስችል አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።
መቅረዝ ጤና አገልሎት ያከናወናቸዋል ከተባሉት ተግባራት መካከል ጠቅላላ ሆሰፒታል፣ የአሜጂንግ ዲያግኖስቲክ ማዕከል፣ የመድሃኒትና ህክምና ዕቃዎች አስመጭና አከፋፋይ  የማማከር አገልግሎትንም ያጠቃልላል።
ሆስፒታሉ የተርሸሪ ሆስፒታል ግንባታ በማካሄድ በአገራችን የማያሰጡ የሕክምና አገልግሎቶች መስጠት በሚጀምርት ወቅት ለከፍተኛ ህክምና ወደ ውጪ አገር የሚሄዱ ታካሚዎችን እንግልት ለማስቀረትና ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬን ለማዳን ያስችላል ተብሏል።
ሆስፒታሉ በቀጣዮቹ አራትና አምስት ወራት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ተገልጿል።


Read 5328 times