በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን የተዘጋጀውና “ፍትህ ይንገስ ሰላም ይመለስ” የሚል መጠሪያ ያለው የኪነ-ጥበብ መሰናዶ ሰኞ መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በዕለቱም ዲስኩር፣ ግጥም ፣መነባነብና ሙዚቃ የሚቀርብ ሲሆን ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ፣መምህር ፋንታሁን ዋቄ፣ ዶ/ር ወዳጄነህ መሃረነ፣ የህግ ባለሙያ ውብሸት ሙላት ዲስኩር፣ ገጣሚያኑ ዲያቆን መኩሪያ ጉግሳ፣ ሻለቃ የወይንሃረግ በቀለ፣ ገዛኸኝ ፀጋው (ዶ/ር)፣ ዘቢብ መልኬ ግጥም እንዲሁም ህጻን አሜን ካሳሁን መነባነብ እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡
ሻሎም ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ቡድን ከድምፃዊያን ጋር በሙዚቃ በሚያደምቀው በዚህ ልዩ የኪነ-ጥበብ ድግስ ለመታደም የመግቢያ ዋጋ 100 ብር እንደሆነና የመግቢያ ትኬቶቹም በጃፋር፣ አይናለምና ዮናስ መፃሀፍት መደብሮች እንዲሁም በጣይቱ ሆቴልና ካሳንቺስ በሚገኘው ጆሲ ልብስ ስፌት ቤት ይገኛሉም ተብሏል፡፡