Saturday, 12 March 2022 14:32

ጄኬ ሮውሊንግ ለዩክሬን ህጻናት 1 ሚ. ፓውንድ እለግሳለሁ አለች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በዩክሬን የህፃናት ማሳደጊያ ተቋም መስርታለች
           ሃሪፓተር በተሰኘው ዝነኛ ድርሰቷ የምትታወቀው እንግሊዛዊቷ ደራሲ ጄኬ ሮውሊንግ፣ በዩክሬን ወላጅ የሌላቸው ህጻናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ ለሚኖሩ እስከ 1ሚሊዮን ፓውንድ (1.3 ሚ.ዶላር ገደማ) የሚደርስ የገንዘብ ልገሳ እንደምታደርግ ቃል ገብታለች፡፡
እ.ኤ.አ በ2005 በደራሲዋ የተመሰረተውና  ለህጻናት ድጋፍ የሚሰጠው “ሉምስ” የተሰኘው የበጎ አድራጎት ድርጅት፤ በዩክሬን  ጦርነት በተፈጠረው ሰብአዊ ቀውስ ጉዳት ለደረሰባቸው  ዜጎች የምግብ፣  የህክምና ቁሳቁስና የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ ለማድረግ ገንዘብ እያሰባሰበ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
“እኔ በግሌ እስከ 1 ሚሊዮን ፓውንድ”  የሚደርስ የገንዘብ ድጋፍ አደርጋለሁ-” ብላለች- ጆኬ ሮውሊንግ፡፡
ደራሲዋ በማከልም፤ “ቀደም ብላችሁ ድጋፍ የለገሳችሁ ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ፡፡ ፋውንዴሽኑ በዩክሬን ለሚገኙ ተጋላጭ ህጻናት ወሳኝ ስራዎችን እንዲያከናውን አስችላችሁታል” ብላለች፡፡
ከመዲናዋ ኬይቭ በስተምዕራብ የሚገኘው የዝይቶሚር ክልል፣ ከሩሲያ ወረራ በፊት፣ ከ1500 በላይ  ህጻናት በማሳደጊያዎች ውስጥ  የሚኖሩበት አካባቢ ነበር ብሏል-“ሉሞስ” በድረ ገፁ፡፡
በመላ ዩክሬን ወደ 100 ሺ የሚጠጉ ህጻናት፣ በማሳደጊያዎች ውስጥ እንደሚኖሩም ፋውንዴሽኑ ያመለክታል፡፡
“የሩሲያ ሃይሎች ዩክሬንን ከወረሩ በኋላ ደግሞ  የበለጠ ቁጥር ያላቸው ህጻናት አደጋ ላይ ይወድቃሉ ማለት ነው” ያለው ፋውንዴሽኑ፤ በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ህጻናት ድጋፍ ለማድረግ እንደሚሻም አስታውቋል፡፡

Read 1713 times