Saturday, 19 March 2022 11:42

ቢጂአይ ኢትዮጵያ፤ በግዢ የወሰደውን የሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ለማነቃቃት፤ የባለስልጣኑን ይሁንታ በመጠባበቅ ላይ እንደሆነ ገለፀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  - የፋብሪካውን ሰራተኞች ከእነ ሙሉ ጥቅማቸው ይዤ እቀጥላለሁ ብሏል
   - ግዥው ለብራንዱ፣ ለሰራተኛውና ለሰበታ ማህበረሰብ አዳዲስ የዕድል በሮችን ይከፍታል ተብሏል

               ቢጂአይ ኢትዮጵያ፤ የሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ከዲያጆ ኩባንያ ለመግዛት ስምምነቱን ካጠናቀቀ በኋላ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣንን ይሁንታ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
ቢጂአይ፣ የሜታን ብራንድ ከእነ ሙሉ ክብሩ ይዞ ለማስቀጠል እንዲሁም የሜታ ሠራተኞችን ፍቅርና የስራ ተነሳሽነት ለመቀስቀስ ሀብቱን እውቀቱንና ልምዱን ለመጠቀም ማቀዱን በመግለጫው አመልክቷል።
 ቢጂአይ እንዲህ ዓይነት ግዢ ሲፈጽም የዋና ዋና ባለድርሻዎችን ፍላጎትና ስጋት ተገንዝቦና የያንዳንዱንም ጥቅም መጠበቁን ማረጋገጥና የገዛውን ድርጅት ከራሱ ጋር  አዋሕዶ መምራቱን እንደተካነበት የኩባንያው አመራሮች ገለልጸዋል። “በተለይ የሜታ ቢራ ፋብሪካ ሠራተኞችና በሰበታ የሚገኘው ማህበረሰብ ጥቅሞች ሁሉ እንደተጠበቁ የሚቀጥሉ ብቻ ሳይሆን ማሻሻያ የሚደረግላቸው ይሆናል።  ይኸውም ቢጂአይ በቢራ ፋብሪካዎቹ አካባቢና ከዚያም ባሻገር ባሉ ዜጎች ሕይወት ላይ አዎንታዊ አሻራውን ለማሳረፍ ሲል ነድፎ ከሚተገብረው ታዋቂው የማኅበራዊ ኃላፊነት ፕሮግራሙ ጋር የተስማማ ነው” ይላል መግለጫው።
የቢጂአይ ግዢ ለሜታ ብራንድ፣ ለሠራተኞችና አከፋፋዮች እንዲሁም ለሰፊው የሰበታ ማህበረሰብ መልካም የምስራች እንደሚሆን የጠቆመው ኩባንያው፤ ግዥው ለብራንዱ፣ ለሰራተኛውና ለሰበታ ማህበረሰብ አዳዲስ የዕድል በሮችን ይከፍታል ብሏል።
ቢጂአይ የባለስልጣኑን ይሁንታ እንዳገኘ የኢንቨስትመንትና የማኅበራዊ ኃላፊነት ተግባራቱን በፍጥነት ለመጀመር በጉጉት እየተጠባበቀ ነው ተብሏል።
ቢጂ አይ ኢትዮጵያ፤ ሰበታ የሚገኘውን የሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ ለመግዛት ከዲያጆ ኩባንያ ጋር ስምምነት ከተፈራረመ አንድ ዓመት ገደማ ቢሆነውም፣ የባስልጣኑን ይሁንታ  ባለማግኘቱና ፋብሪካውን ተረክቦ ወደ ሥራ መግባት ባለመቻሉ የአቅሙን ያህል እየሰራ አለመሆኑንና ሰራተኞቹም እንደሚሆን የጠቆመው ኩባንያው፤ እንዳልሆነ ተገልጿል።

Read 1427 times