Print this page
Saturday, 19 March 2022 12:17

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

እስከ ጊዜው ድረስ
እስከ ጊዜው ድረስ
በተያዘው ሳቁ - ከማይቀረው ራቁ
ወረፋ ነውና ተራችሁን ጠብቁ
ይመስላል የማይፈርስ
ጥበቃም የማይደርስ
ሀዘንም የማይመር
ምኞትም የማይሰምር
የረገበ ሁሉ - ዝንታለም የማይከር
የማይመስል ይመስላል!
ግን፤ ድንጋይም በሂደት
እንደ ወይን ይበስላል
ፀሀይዋም አንድ ቀን
ቀይ ድዷ ይከስላል
ጊዜ አረፋ ነው
ባላ’ረፋ ወንዝ ነው
የማይደርስ ይመስላል
ስቆ ያሳስቃል
ተራ ያስጠብቃል፡፡

         (ሌሊሣ ግርማ)

Read 1439 times
Administrator

Latest from Administrator