Print this page
Saturday, 26 March 2022 10:47

የኦቲዝም ጉዳይ አሁንም ልዩ ትኩረት ይሻል ተባለ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  የኦቲዝም ጉዳይ አሁንም ልዩ ትኩረት እንደሚሻ ሴንተር ፎር ፋሚሊ ሰርቪስ የተሰኘ አገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት አስታወቀ፡፡ በጎ አድራጎት ድርጅቱ ይህንን ያሳሰበው ባለፈው ሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ቀንን ምክንያት በማደረግ ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡
የሴንተር ፎር ፋሚሊ ሰርቪስ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተፈራ ሀይሉ በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር የኦቲዝም ተጠቂ ልጆች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን አስታውሰው ድርጅታቸውም በኢቲዝም ተጠቂዎች፣ ልዩ ፍላጎት ባላቸውና የአገር ውስጥ ማደጎን በማበረታታ ላይ አተኩሮ እንደሚሰራ አስታውሰው በተለይም በነዚህ ልዩ ፍላጎት ባላቸው ልጆች ወላጆችና መምህራን ዙሪያም እንደሚሰሩም አስታውቀዋል፡፡
በእለቱም ስለ ኦቲዝም ምንነት፣ ኦቲዝምን የተመለከተ የህጻናት ህብረ ዝማሬ፣ በኦቲዝም ዙሪያ ፈር ቀዳጅ ተጋድሎ ያደረጉትና በቅርቡ በኮቪድ ወረርሽኝ ያጣናቸውን የኒያ ፋውንዴሽን ጆይ ኦቲዝም ሴንተር የመሰረቱትና መሩትን ወ/ሮ ዘሚ የኑስን የመዘከርና እሳቸውን የሚያወድስ ግጥም፣ልጆቻቸው የኦቲዝም ተጠቂ የሆኑ ወላጆች ተሞክሮዎቻ ለታዳሚ ቀርበዋል፡፡

Read 11603 times