Sunday, 27 March 2022 00:00

“የቃል ሰሌዳ” የግጥም መፅሐፍ ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የገጣሚ መንበረ ማሪያም ሀይሉ “የቃል ሰሌዳ” የግጥም መፅፍ ሰኞ መጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡
በእለቱ ግጥም ከክራር ጋር፣ ግጥም ከስዕል ጋር፣ ግጥም ከሙዚቃና ከወሎ መንዙማ ጋር ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን የመፅሀፉን አርትኦት የሰሩት መምህር ደራሲና ሀያሲ ሀይለመለኮት መዋዕለና አርቲስት ስዩም ተፈራ ስለ መፅሐፉ ንግግር እንደሚያደርጉ ገጣሚዋ ገልፃለች፡፡
በተፈጥሮ በሰውና በመለኮት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ከ50 በላይ ግጥሞች ያሉት “የቃል ሰሌዳ” የግጥም መፅሀፍ በ145 ገፅ ተቀንብቦ በ120 ብር ለገበያ መቅረቡ ታውቋል፡፡

Read 10510 times