Saturday, 26 March 2022 11:24

ከፌስቡክ ገጾች በጨረፍታ

Written by  አንዷለም ቡኬቶ ገዳ
Rate this item
(1 Vote)

   ኢትዮጵያ ላይ የተነጣጠረው አስከፊው - HR6600
                                    

             አሜሪካና አጋሮቿ የኢትዮጵያን እጅ ለመጠምዘዝ የሚሄዱበት ርቀት ከእለት ወደ እለት አስገራሚ እየሆነ ነው። አሁን ላይ ደግሞ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚገስ፣ እስከዛሬ ከተሞከሩት በአይነቱም ሆነ በይዘቱ አስከፊ የሆነ HR6600 የሚባል ህግ ለማጽደቅ እየተንቀሳቀሱ ነው።
በዚህ ህግ የአሜሪካን የፋይናንስ ቢሮና የውጭ ጉዳይ ቢሮ፣ ለኢትዮጵያ የሚደረጉ ማናቸውም ብድሮችና እርዳታዎችን (ከአሜሪካ የምናገኘውን ብቻ ሳይሆን ከታላላቆቹ የገንዘብ ተቋማት (እነ ወርልድ ባንክን ማለት ነው) እንዳይሰጠን ቢሮዎቹ ተከታትለው ብሎክ እንዲያደርጉ አደራ ተጥሎባቸዋል!
ይህ እጅግ መረን የወጣ ብልግና ነው!
ረቂቅ ህጉ ከጸደቀ ምናልባት አሜሪካን ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ለሃገር ቤት ድሃ ዘመዶቻቸው ድጋፍ ማድረግ መቻላቸው እራሱ አጠራጣሪ ነው! ኢትዮጵያ የትኛውም አይነት ወረራ ቢያጋጥማት እንደ ረቂቅ ህጉ ከሆነ ከየትኛውም ሃገር የጦር መሳሪያ መግዛት አትችልም!
ይህን ህግ መቃወም ለሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ (ባንዳን አይጨምርም) የተገባ ነው!!
በአንጻሩ ይህ ህግ እንዲጸድቅ ማናቸውም አይነት ድጋፍ መስጠት በሞራል ብቻ ሳይሆን በህግም ጭምር ተጠያቂ የሚያደርግ ይመስለኛል!
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ ከአንቀጽ 248 እስከ 251 በጥቅሉ ሲታይ፣ ይህንን በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣን አደጋ መደገፍ ‘በሃገር ክህደት’ እና ‘ከጠላት ጋር በመተባበር’ የሚያስጠይቅ ከመሆኑም በላይ እንደ ነገሩ ሁኔታ ከ15 አመት ጽኑ እስራት እስከ ሞት ፍርድ ሊያስፈርድ ይችላል!
በዚህ ተግባር ላይ ባለማወቅ የሚሳተፉ ግለሰቦች (ከባንዳ በስተቀር) ምናልባት ይህ ድርጊታቸው በጠቅላይ አቃቤ ህግ አይን እኔ ከላይ ባስቀመጥኩት አግባብ የሚታይ ቢሆን ያላሰቡት መዘዝ የሚያስከትልባቸው መሆኑን ከግምት በማስገባት ሊታቀቡ ይገባል!
በሃገሬ ላይ የሚደረግ ማናቸውንም የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ሙከራ አምርሬ እቃወማለሁ!!


Read 1675 times