Saturday, 02 April 2022 11:32

አገሩን የማያውቅ ሰው፣ መሬት እየረገጠ መሬትን ይረግማል

Written by 
Rate this item
(4 votes)

 የሚከተለውን የፃፈልኝ ዶ/ር እጓለ ገ/ዮሐንስ ናቸው፡፡ ዶ/ር እጓለ ለሰአሊና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ የስዕል ካታሎግ ከጀርመን ሀገር በመግቢያ የፃፉ ሰው ናቸው፡፡ እንደሚታወቀው የሰአሊ ገብረክርስቶስ ደስታ ስዕሎች ዘርፋቸው ከረቂቅ ስእል ዝርያ ነው፡፡ ስለዚህም ዶ/ር እጓለ ሲፅፉ፤ “…ዛሬ በሀገራችን እያንዳንዱ ሰው በቤቱ አራቱም ግድግዳ ላይ የገዛ እራሱን ፎቶ ግራፍ ሰቅሎ በኩራት በሚኖርበት ሀገር፤ የአብስትራክት አርት (የረቂቅ ስእል) ኤግዚቢሽን አሳያለሁ ብሎ ማሰብ በጣም አስገራሚ ነው !”
ይሉናል፡፡
እራሳችንና እራሳችንን ብቻ ማሰብ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ እግዜር ከዚህ ይሰውረን፡፡ ይሄን የእለቱ መልዕክት እንበለውና ወደ ዕለቱ ተረት እንሸጋገር!
በግሪክ ሜቶሎጂ( የስነ ተረት ስርአት) አብዝቶ የሚተረት ድንቅ ተረት አለ። ይህም ስለ ፕሮሚሴቭስ የሚነገረው ነው፡፡ ትልቅ ሚስጥር ደብቆ የያዘ ስለሆነ፣ ስለሱ ዛሬም እናወሳለን፡፡ ኤስሂሎስ የሚባለው ትራጀዲ የፈጠራ ባለቅኔ፣ አንድትሮሎጂ ማለትም ሶስት ድራማዎች ያሉት ትያትር ፅፈዋል፡፡ እሱንም ተከትሎ ሼሊባይረን ጎይተ ፃፈ፡፡ የፕሮሚሲቭስ መንፈስ በአውሮፓ የመንፈስ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛውን መስመር የያዘ ነው፡፡ አሁን የጠቀስናቸው ሰዎች በአውሮፓ የስነ ፅሁፍ ጠፈር ላይ በጣም ጎልተው የሚታዩ ክዋክብት ናቸው፡፡ ተረቱም የሚከተለው ነው
ፕሮሚሴቭስ በከፊል አምላክ፣ በከፊል ሰው የሆነ፣ህላዌ ፍጡር ነበር፡፡
በከፊል አምላክ እንደመሆኑ፣ አስራሁለቱ የግሪክ አማልክት  በአሉቦስ ተራራ ሆነው ስለ ሰውና ስለ አለም አስተዳደር ይሰሙ ነበር፡፡ በከፊል ሰው እንደመሆኑ የሰው ስቃይና መከራ በጣም ያሳዝነዋል ይፀፅተውም ነበር፡፡
ሰው ቤት ንብረት ሳይኖረው በበርሀ፣ በጫካ፣ በዱር ፣በገደል ፣በዋሻ በቁርና በሀሩር እንዲኖር ተፈርዶበት ነበር፡፡ ይህ የሚሆንበት አማልክት መክረው ዘክረው፣ለሰው የእውቀት ምንጭ የሆነውን ብርሃንን የሰጡት እንደሆን፣ ከለታት አንድ ቀን ሰጪነታቸውን ክዶ፣ በነሱ ላይ በመነሳት የሚያምጽ መሆኑን በመረዳት፣ ብርሃንም ከሰዎች ደብቀው፣ ከማይደፈረስበት በመሰወራቸው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በጨለማና በሱ ተከታይ በሆኑት ችግሮች ስር ሲሰቃዩ ይኖራሉ፡፡
ይህ የሰዎች መራራ እድል ወገናቸው በሚሆን፣ በፕሮሚሴቭስ ላይ ርህራሄ አሳድሮበት፣ ብርሃኑን አማልክት አርቀው ከደበቁበት ሰርቆ፣ ለሰዎች ሰጠ! ያን ግዜ ማናቸውም ነገር ግልፅ ሆኖ ታያቸው! በብርሃን ምክንያት ጥበብና ማናቸውም የጥበብ ስልት ስለተገለጠላቸው፣እራሳቸው ከገዛ እራሳቸው  በተገኘ ዘዴ ማስተዳደር ጀመሩ፡፡
ፕሮሚስቭስ ግን ለሰዎች ብርሃን ሰጥቶ በጎ በመስራቱ አማልዕክት ቀንተው፣ በብርሃናቱ ስቃይ ይቀጣ ዘንድ ፣ አንዳች ከማይደርበት ገደል ላይ፣ ከቋጥኝ ድንጋይ ጋር በሰንሰለት ተቆራኝቶ፣ አሞራ ለዘለአለም እንዲበተብተው ፈረዱበት!!
ከፕሮሚስቭስ እጣ ይሰውረን!
አማልእክት ብርሃንን ከደበቁበት ቦታ ወስደው ለሰው እንዳበረከተ፣ የአውቀት ሰዎችን፣ እውቀትን በመለኮታዊ ሚስጢርነት፣ ከሰው ተደብቃ ስትኖር ሳለ፣ በብዙ ትግል አግኝታው፣ ከገዛ እራሳቸው አስርፀው፣ የወገኖቻቸው እድል ለማሻሻል ያበረክታሉ ዋጋቸውም ሌላ ሳይሆን ስቃይ መከራ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ሶቅራጠስ በመርዝ ተገድሏል፡፡ ጆርዳኖብሩኖ የጧፍ ቀሚስ የዝንቅ ጉራማይሌነት በባህላዊ ውበትና ድምቀት፣ የሀሳብ ነፃነት ከጋዜጣ፣ ሬድዮና አጠቃላይ ውይይት፣ የምህዳር ጥበትና ስፋት የሚያስከትል መሆን አለበት ይለናል፡፡ ወጣቱ አገሩን ያውቅ ዘንድ ጥልቅ አስተሳሰብ፣ ረጅም ራዕይና በግብረ ገብነት የታነፀ ድፍረትና መስዋዕትነት ሊኖረው ይገባል! የሀገራዊነት፣ የወገን አሳቢነት፣ የኢ-ራስ ወዳድነት የፀረ ሁሉን አውድምነት መርህ መጨበጥ አለበት፡፡ ከሁሉም በላይ ደሞ ፅንፈኝነትን መዋጋት፣ ዲሞክራሲያዊ ትጥቁ መሆኑን ማስገንዘብ ቁልፍ ነገር መሆኑን እናሳየው! አለበለዚያ፤ አፋሮች እንደሚሉት “አገሩን የማያውቅ ሰው መሬት እየረገጠ መሬትን ይረግማል” ማለት ይሆንብናልና፤ ልብ ያለው፣ ልብ ይበል!!
ዛሬም ከገጣሚ ገሞራው ጋር፤
“ነገር አልሆን ብሎ፣ ሁኔታው ሲጠጠር
ጠጣሩ እንዲላላ የላላውን ወጥር!”
እንላለን፡፡
አንድም ደሞ
“ሀገሬን ሀገሬን፣ አይልም ወይ ሰው
አንጀቱ እያረረ፣ ሆድ እየባሰው”
ማለት ያባት ነው!

Read 12688 times