Saturday, 09 April 2022 13:17

አምባሳደሩ HR 6600 እና S 3199 ረቂቅ ህጎች እንዲዘገዩ ተደርጓል መባሉን አስተባበሉ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   “በወልቃያት ጠገዴና ጠለምት የዘር ማጥፋት ጥናት ላይ ቅሬታ ያላቸው በሳይንሳዊ መንገድ ማረጋገጥ ይችላሉ”
          “ከአረብ አገር ለማምጣት ከታቀደው 100 ሺህ  ያህል ዜጎች 45 ሺህ ተመዝግበዋል“
               
               HR 6600  እና  S 3199  የተሰኙትና  የአሜሪካ መንግስት  በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ሊጥላቸው የነበሩትን ማዕቀቦች የአሜሪካ መንግስት አዘይቷቸዋል መባሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስተባበሉ፡፡
አምባሳደሩ ይህንን የገለፁት ከትላንት በስቲያ በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ጎሀ ሆቴል ሳምንታዊ መግለጫ ለጋዜጠኞች በሰጡበት ወቅት ነው፡፡ አምበሳደር ዲና፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሳምንቱ ውስጥ ያከናወናቸውን ዲፕሎማሲያዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁነቶችም አብራርተዋል፡፡
በተለይም  HR 6600  እና  S 3199 የተሰኙትና ኢትዮጵያ ላይ በአሜሪካ መንግስት ሊጣሉ የተዘጋጁት ማዕቀቦች ለጊዜው በአሜሪካ መንግስት እንዲዘገዩ ተደርጓል መባሉን እንደማያውቁና በይፋ የተገለፀ ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። እስካሁንም እነዚህ ማዕቀቦች በሂደት ላይ እንዳሉ እንደሚያውቁ የጠቆሙት አምባሳደሩ፤ እንዲህ አይነት ያልተረጋገጡ ወሬዎች የኢትዮጵያ መንግስትና ዲያስፖራው ማህበረሰብ የሚያደርገውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማዘናጋት ሆን ተብሎ የሚፈበረኩ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡Why H.R. 6600 Bill is Dangerous to Ethiopians and Why We Need to Reject It
አምባሳደሩ በሌላ በኩል፤ በጎንደር ዩንቨርስቲ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ጥናት ማዕከል መመስረቱን በተመለከተ  ሲናገሩ፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደነዚህ አይነት ማዕከላት መቋቋማቸው ኢትዮጵያ እንደ አሁን አይነት ፈተናና ተግዳሮት ሲገጥማት በእውቀትና በብልሀት የሚመክት ዜጋን በማፍራት፣ ጠንካራና ራሷን መከላከል የምትችል ሀገር እንድትኖረን ያስችለናል ብለዋል እስካሁን በቦንጋ ፣በሀዋሳና ፣በአርባ ምንጭ ዩኑቨርስቲዎች ማዕከሉ መከፈቱንና የመሰረተ ተቋም መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በጎንደር ዩኒቨርስቲ የጥናት ቡድን ከአንድ ዓመት በላይ  የወሰደና በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ባለፉት 40 ዓመታት የደረሰውን የዘር ፍጅት ጥናት ሪፖርትን በተመለከተ፤ ዩኒቨርስቲው የወሰደውን ሀላፊነት፤ ይህ የማዋጥላቸው አካላት “ጥናቱ የፈጠራ ነው፤ እውነት የለውም” ከሚሉ ገለልተኛ በሆነ አካልና በሳይንሳዊ ዘዴ ማጠራት  እንደሚችሉና መንግስትም ይህን እንዲያደርጉ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻት ገልፀው ያን ጊዜ ፈጠራ ሆኖ ካገኙት ግኝታቸውን ይፋ ማድረግ እንጂ ከውጪ ሆነው እንዲህ አይነት ወሬና ያልተጨበጠ ነገር ማናፈሳቸው ተቀባይነት የለውም ብለዋል። አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አክለውም፤ በተለይ የወቅቱን የአሜሪካና የኢትዮጵያ ግንኙነት በተመለከተ አገዋንም ሆነ ሌሎች ከአሜሪካና  ጋር የሚያስተዳስሩን ነገሮች እንፈልጋቸዋለን፤ ለዚህ ግንኙነት እንቅፋት የሆኑትን ነገሮች ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት እያደረግን እንገኛለን” ብለዋል።
ዜጎችን  ከአረብ አገር የመመለሱን ሂደት አስመልክቶ በሳምንት ሶስት ቀን፣ በቀን  ደግሞ ሶስት በረራዎች እየተደረጉ ዜጎቻችን የመመለሱ ስራ እየተከናወነ እንደሆነ ጠቁመው፤ ፣መንግስት 100 ሺ ዜጎችን ወደ ሀገር ለመመለስ ማቀዱንና እስካሁን 45 ሺህ ዜጎች መመዝገባቸውን ገልፀዋል። እስካሁን ምን ያህሉ ዜጎች ወደ አገር ቤት መልሳችኋል? በሚል ከጋዤጠኞች ካቀረበው ጥያቄም  እስካሁን የተመለሱትን ቁጥር አጣርተን በቅርቡ ይፋ እናደርጋለን ሲሉ መልሰዋል።
በሌላ በኩል፤ በዚሁ ሳምንት የብራዚል ፕሬዝዳንት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰጡት ሽልማት ተጠቃሽ የሚያኮራ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ብራዚል ከመብረርም አልፎ ብራዚልን በማገልገል በኩል የሰራው ትልቅ ተግባር የብራዚል መንግስት ከፍተኛውን ሽልማት ለአየር መንገዳችን ሰጥቶታል ብለዋል። የጎረቤት አገር ጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኡመርጊሌ የኢትዮጵያ የሁለት ቀን ጉብኝት ማድረጋቸውንና ከጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ በሁለትዮሽ ግንኙነት በተለይም በወደብና በአየር ግንኙነትም ሆነ በሌሎች መስኮች ያሏቸውን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ውይይት አድርገዋል ብለዋል ቃል አቀባዩ፤


Read 773 times