Saturday, 09 April 2022 13:38

ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማቱ ያወጡት ሪፖርት ዳግም ሊጤን ይገባዋል ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 “የተቋማቱ ምክረ ሃሳቦች የአገሪቱን ሉአላዊነት የሚዳፈር ነው”
                            
               አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች ምዕራብ ትግራይን አስመልክቶ ከሰሞኑ በጋራ ያወጡት ሪፖርት፣ ሚዛናዊነት የጎደለውና ወገንተኝነት የገነነበት ነው ሲሉ ምሁራን ተችተዋል። የሰሞኑ ሪፖርት ሁለቱ ተቋማት ቀደም ሲል በተናጥል አውጥተውት ከነበረው ሪፖርት በእጅጉ የሚቃረን እንደሆነም ምዑራኑ ጠቁመዋል። ተቋማቱ ሪፖርታቸውን ዳግም ሊያጤኑት እንደሚገባም ነው የመከሩት።
 ሁለቱ የመብት ተሟጋች ተቋማት ሰሞኑን ይፋ ባደረጉት ሪፖርት ላይ እንደተመለከተው፤ በምዕራብ ትግራይ ወልቃይትና አካባቢዎቹ ላይ የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይሎች፣ በንፁሀን ዜጎች ላይ የመብት ጥሰቶች ፈፅመዋል። “የአማራ የፀጥታ ኃይሎች በበቀል የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሰንዝረዋል፤ ቤትና ንብረት ዘርፈዋል” ብለዋል፡፡
በአካባቢው የዘር ማፅዳት ዘመቻ ተፈፅሟል ያለው ሪፖርቱ፤ ህገወጥ ግድያ፣ የጅምላ እስራትና ወሲባዊ ጥቃት መፈጸሙንም አመልክቷል። ተጨማሪ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳይፈፀም ለመከላከል  በአፍሪካ ህብረት የሚመራ አለማቀፍ ሰላም አስከባሪ ኃይል በስፍራው እንዲሰማራ ጠይቀዋል።Tigrai Media House - 	  </div>
	  
		<div class=

Read 10983 times