Print this page
Saturday, 16 April 2022 13:48

“አሸዋ ቴክኖሎጂ” የ20 ሚ.ብር አዲስ ፕሮጀክት አስተዋወቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

    በሎጂስቲክስና ዴሊቨሪ ዘርፍ ሊሰማራ ነው

            በወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የዛሬ 2 ዓመት የተቋቋመውና በኢ-ኮሜርስ ገዥና ሻጭን በማገናኘት የዘመነ ግብይት ለማቀላጠፍ የሚሰራው አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሊዩሽን፤ በ20 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት አዲስ ፕሮጀክት አስተዋወቀ፡፡
አዲሱ ፕሮጀክት የሎጂስቲክስና ዴሊቨሪ አገልግሎትን በብቃት፣ በቅልጥፍናና፣ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማቅረብ ያለመ ሲሆን “አሸዋ ሎጂስቲክስና ኤክስፕረስ” የሚል ስያሜም ተሰጥቶታል፡፡
የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉዩሽን እህት ኩባንያ እንደሆነ የተገለፀው አዲሱ ፕሮጀከት መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ፣ በሎጀስቲክስና ዴሊቨሪ አገልግሎት ዓለምን ከዳር እስከ ዳር ያካልላል ተብሏል፡፡
 ከትላንት በስቲያ ሃሙስ በሳፋየር አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሊዩሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል በቀለ እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ወቅት የሎጂስቲክ ዘርፍ በዓለም ላይ በትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ቢዝነስ ሲሆን እኛም በአግባቡ ከሰራንበት አገርን የሚያበለጽግ፣ የሰዎችን ህይወት የሚያቀልና ብዙዎችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡
ኩባንያችን በዚህ ዘርፍ ለመሰማራትም በ20 ሚ ብር ኢንቨስትመንት በሙሉ አቅሙ ወደ ስራው ለመግባት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ እስካሁን 11 ሞተር ሳይክሎች፣ አንድ ቫን (ኮንቴየነር ካር) መግዛቱንና ትልቅና ምቹ መጋዘን መከራየቱን ገልጸው ተጨማሪ መኪኖች በግዢ ሂደት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ወደ የትኛውም የዓለም ክፍል የሻጭን  እቃ ወደ ገዢ በአስተማማኝ በተቀላጠፈ  መንገድና በተመጣጣኝ ክፍያ ለማጓጓዝና ለማቀበል እንደ DHL የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት፣አየር መንገድና ከሌሎች ስመጥር ድርጅቶች ጋር በትብብርና በቅንጅት የመስራት ዕቅድ እንዳላቸውም አስረድተዋል፡፡አሸዋ ሶሉሽን ቴክኖሎጂ አክሲዮን ማህበር የ7 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት አስጀመረ፡፡ – Ethio FM 107.8
ኩባንያው መቀመጫው አዲስ አበባ ሲሆን በመዲናዋ 8 ዲስትሪክቶች ይኖሩታልም ተብሏል። በዋናነት ደንበኛን ማዕከል ያደረገ አሰራር እንደሚከተል የተነገረለት አሸዋ ሎጂስቲክና ኤክስፕረስ፤ዋነኛ አላማውም ሰዎችን ከጊዜ በጉልበትና ከገንዘብ ብክነት በመታደግ ዘመናዊ ቀላልና ምቹ ኑሮ የሚመሩበትን ዕድል መፍጠር ነው ተብሏል፡፡ ኩባንያው በመጪው ሰኔ ወር ላይ ስራውን በይፋ እንደሚጀምር የተገለፀ ሲሆን ራዕዩም ለ500 ሺህ ያህል ሰዎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተነግሯል፡፡
በሁለት ሠራተኞች ብቻ ሥራውን የጀመረው አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሊዩሽን፤በአሁኑ ወቅት 200 ሰራተኞችን መቅጠር የቻለ ሲሆን የአክስዮን ሽያጩን በማቀላጠፍ ኩባንያው የ160 ሚ ብር ኢንቨስትመንት ሊሆን መብቃቱን አቶ ዳንኤል በቀለ ተናግረዋል፡፡


Read 1281 times
Administrator

Latest from Administrator