Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 06 October 2012 12:00

አየር መንገድ፤ ከቦምባርዲየር አዲስ አውሮፕላን ተረከበ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካናዳው ቦምባርዲየር ኩባንያ ለመግዛት ካዘዛቸው አምስት አውሮፕላኖች ውስጥ የመጀመሪያው ከትናንት በስቲያ ማምሻውን ቦሌ ያረፈ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ እስከ ታህሳስ ድረስ ይገባሉ፡፡
በቅርቡ ከቦይንግ ኩባንያ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን በመግዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ ከዓለም 2ኛ የሆነው አየር መንገዱ፣ ዛሬም የካናዳው ቦምባርዲየር ኩባንያ ምርት የሆነውን ዘመናዊው 8Q -400 አውሮፕላን በመግዛት ከአህጉሩ የመጀመሪያው በመሆን ቀዳሚነቱን አስመስክሯል፡፡ አየር መንገዱ ቀደም ሲል ከኩባንያው በገዛቸው ስምንት አውሮፕላኖች አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፤ አዲሱ አውሮፕላን በጥራት ደረጃው በጣም የላቀ መሆኑን አብራሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ የዘመኑ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ውጤቶች የተገጠሙለት አዲሱ አውሮፕላን  የአብራሪዎቹንም የሥራ ጫና እንደሚቀንስ የጠቀሱት ካፒቴኖቹ፣ ወንበሮቹ ወደ ኋላ ስለሚለጠጡ፣ መንገደኞች ምቾታቸው ተጠብቆና ተዝናንተው ይጓዛሉ ብለዋል፡፡
ቀደም ሲል የገቡት አውሮፕላኖች ባለአንድ መፀዳጃና ባለአንድ ምግብ ማሞቂያ እንደሆኑ ጠቅሰው፣ አዲሱ ግን መፀዳጃና ምግብ ማሞቂያ ከፊትና ከኋላው እንዳለው ተናግረዋል፡፡  አዲሱ አውሮፕላን  በመቀመጫዎቹ ብዛትም ይለያል፡፡ ቀዳሚዎቹ 67 የኢኮኖሚ ክላስ መቀመጫ ብቻ ነው ያላቸው፡፡ አዲሱ ግን ክላስ 8 የቢዝነስ ክላስ መቀመጫዎች ተጨምረውለታል፡፡ አዲስ አውሮፕላን ከ17 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች በተጨማሪ ቅርብ ወደሆኑ የአፍሪካ አገራት ወደ ኬንያ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሌላንድ…ይበርራል፡፡
አየር መንገዱ ቀደም ሲል የገዛቸውን ስምንት አውሮፕላኖች የአዲሱን አውሮፕላን ደረጃ እንዲይዙ ወደ ኩባንያው በመላክ በራሱ ወጪ እንደሚያሻሽላቸው ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካናዳው ቦምባርዲየር ኩባንያ ለመግዛት ካዘዛቸው አምስት አውሮፕላኖች ውስጥ የመጀመሪያው ከትናንት በስቲያ ማምሻውን ቦሌ ያረፈ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ እስከ ታህሳስ ድረስ ይገባሉ፡፡ በቅርቡ ከቦይንግ ኩባንያ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን በመግዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ ከዓለም 2ኛ የሆነው አየር መንገዱ፣ ዛሬም የካናዳው ቦምባርዲየር ኩባንያ ምርት የሆነውን ዘመናዊው 8Q -400 አውሮፕላን በመግዛት ከአህጉሩ የመጀመሪያው በመሆን ቀዳሚነቱን አስመስክሯል፡፡ አየር መንገዱ ቀደም ሲል ከኩባንያው በገዛቸው ስምንት አውሮፕላኖች አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፤ አዲሱ አውሮፕላን በጥራት ደረጃው በጣም የላቀ መሆኑን አብራሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ የዘመኑ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ውጤቶች የተገጠሙለት አዲሱ አውሮፕላን  የአብራሪዎቹንም የሥራ ጫና እንደሚቀንስ የጠቀሱት ካፒቴኖቹ፣ ወንበሮቹ ወደ ኋላ ስለሚለጠጡ፣ መንገደኞች ምቾታቸው ተጠብቆና ተዝናንተው ይጓዛሉ ብለዋል፡፡ 

ቀደም ሲል የገቡት አውሮፕላኖች ባለአንድ መፀዳጃና ባለአንድ ምግብ ማሞቂያ እንደሆኑ ጠቅሰው፣ አዲሱ ግን መፀዳጃና ምግብ ማሞቂያ ከፊትና ከኋላው እንዳለው ተናግረዋል፡፡  አዲሱ አውሮፕላን  በመቀመጫዎቹ ብዛትም ይለያል፡፡ ቀዳሚዎቹ 67 የኢኮኖሚ ክላስ መቀመጫ ብቻ ነው ያላቸው፡፡ አዲሱ ግን ክላስ 8 የቢዝነስ ክላስ መቀመጫዎች ተጨምረውለታል፡፡ አዲስ አውሮፕላን ከ17 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች በተጨማሪ ቅርብ ወደሆኑ የአፍሪካ አገራት ወደ ኬንያ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሌላንድ…ይበርራል፡፡ አየር መንገዱ ቀደም ሲል የገዛቸውን ስምንት አውሮፕላኖች የአዲሱን አውሮፕላን ደረጃ እንዲይዙ ወደ ኩባንያው በመላክ በራሱ ወጪ እንደሚያሻሽላቸው ገልጿል፡፡

Read 2291 times

Latest from