Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 06 October 2012 12:26

አምባሳደር ብርሃነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊሆኑ ነው

Written by 
Rate this item
(6 votes)

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ሞት ተከትሎ በተጠራው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ ምክትላቸው የነበሩትን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ከሾመ ወዲህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱ ቦታ ክፍት ሆኖ የቆየ ሲሆን ለዚህም ሚኒስቴሩን ላለፉት ሁለት አመታት በሚኒስትር ደኤታነት ያገለገሉት አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ እንደታጩ መመደባቸውን ምንጮቻችን አመለከቱ፡፡
ሀገሪቱ የምትመራበትን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በማርቀቅ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው አምባሳደር ብርሃነ፤ ከሚኒስትር ደኤታነታቸው በፊት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን የተጓተቱ እቅዶችን ጨምሮ በተያዘለት ጊዜ ለማስፈፀም እንዲቻል በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራና ባለ ድርሻ ባለሙያዎች የተካተቱበት ግብረሃይል ተቋቋመ፡፡
በተያያዘም አቶ ኃይለማርያም በቦርድ ሰብሳቢነት ይመሩት የነበረው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ድሪባ ኩማ መሠጠቱንና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን በቅርቡ እንደሚቋቋም ምንጮቹ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ሞት ተከትሎ በተጠራው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ ምክትላቸው የነበሩትን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ከሾመ ወዲህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱ ቦታ ክፍት ሆኖ የቆየ ሲሆን ለዚህም ሚኒስቴሩን ላለፉት ሁለት አመታት በሚኒስትር ደኤታነት ያገለገሉት አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ እንደታጩ መመደባቸውን ምንጮቻችን አመለከቱ፡፡ ሀገሪቱ የምትመራበትን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በማርቀቅ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው አምባሳደር ብርሃነ፤ ከሚኒስትር ደኤታነታቸው በፊት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን የተጓተቱ እቅዶችን ጨምሮ በተያዘለት ጊዜ ለማስፈፀም እንዲቻል በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራና ባለ ድርሻ ባለሙያዎች የተካተቱበት ግብረሃይል ተቋቋመ፡፡

በተያያዘም አቶ ኃይለማርያም በቦርድ ሰብሳቢነት ይመሩት የነበረው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ድሪባ ኩማ መሠጠቱንና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን በቅርቡ እንደሚቋቋም ምንጮቹ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Read 4080 times