Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 06 October 2012 13:04

የስንታየሁ “ሂቦንጐ” አልበም ተመረቀ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

“ሂቦንጐ” በሚለው የሃዲይኛ ስልቱ የሚታወቀው ድምፃዊ ስንታየሁ ጥላሁን የፍቅር ጥሪ በሚል ርዕስ የመጀመሪያ አልበሙን ከትናንት ወዲያ ምሽት  H2O ክለብ አስመረቀ፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት በሠራው ሂቦንጐ የተባለ ነጠላ ዜማ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘው “የፍቅር ጥሪ” አልበሙን ፤ በናሆም ሪከርድስ አሳታሚነት ለገበያ አቅርቧል፡፡

በአልበሙ ላይ በግጥምና ዜማ ከተሳተፉት መካከል ነዋይ ደበበ፣ አንተነህ ወራሽና አለማየሁ ደመቀ ሲገኙበት በሙዚቃ ቅንብር ካሙዙ ካሣ፣ ሚካኤል ሃይሉና መኮንን ለማ (ዶክተሬ) ሰርተዋል፡፡  “የፍቅር ጥሪ” የሚለውን ስያሜ ሁለት ዘፈኖች የሚወክል እንደሆነ ስንታየው ገልፆ፤  አንደኛው ዘፈን የፍቅር አጋሩን ስለሚፈልግ ወጣት የተጫወትኩበት ነው ብሏል፡፡  “መነድ አያዶ” የሚለው ዘፈን ደግሞ በሃድያ ባህል ሰዎች ለፍቅር የሚገናኙበትን መንገድ የሚገልጽ ሲሆን፣ 83 የአገራችን ብሔረሰቦች እርስበርስ እንዲገናኙበት ጥሪ በማድረግ የሠራሁበት ነው ብሏል፡፡

 

Read 3806 times Last modified on Saturday, 06 October 2012 13:17