Saturday, 21 May 2022 11:35

“የቀን ወጣልኝ ፖለቲካ” መፅሐፍ ዛሬ ለንባብ በቃ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የደራሲ በሪሁን አዳነ ሁለተኛ ሥራ የሆነው “የቀን ወጣልኝ ፖለቲካ” ጥቅመኝነትና የሽግግር ክሽፈት መፅሐፍ በዛሬው ዕለት ገበያ ላይ ውሏል፡፡ መፅሐፉ በዋናነት በሀገራችን ፖለቲካ “የጎር ዲያን ቋጠሮ” ሆኗል ስለሚባው የአገረ መንግስትና ብሔረ መንግሰት ግንባታና ከዚሁ ጋር ተያዞ ስለመጣው የብሔርተኝት እንቅስቃሴ የሚያትት ነው ተብሏል፡፡ በመፅሐፉ ውስጥ አገራችን የገጠማት አሁናዊ ተግዳሮቶችና መንስኤዎቹ፣ በደንብ ስለመተንተናቸው ደራሲው በሪሁን አዳነ ገልጿል፡፡ በ221 ገፅ የተቀነበበው መፅፍ በ150 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም ማለትም በ2007 ዓ.ም “በምርኮ የተያዘ ህዝብ” የአውራ ፓርቲ ሥርዓት ወይስ የአፈና አገዛዝ? የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

Read 10786 times