Print this page
Sunday, 22 May 2022 00:00

ሦስት ታዋቂ አርቲስቶች የሩቢ ቪዛ ኮንሰልቲንግ አምባሳደሮች ሆነው ተመረጡ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በኢትዮ ኤርስ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ሥር የሚተዳደረው ሩቢ ቪዛ ኮንሰልቲንግ ሦስት ታዋቂ አርቲስቶችን የብራንድ አምባሳደሮቹ አድርጎ ሰየመ፡፡
በብራንድ አምባሳደርነት የተሰየሙት አርቲስት ዳንኤል ተገኝ፣ አርቲስት ሩታ መንግስተአብና አርቲስት ሊዲያና ሰለሞን ሲሆኑ ከአምባሳደሮቹ ጋርም የፊርማ ሥነስርዓት ተከናውኗል፡፡
በኢትዮ ኤርስ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ሥር ከሚገኙ ተቋማት አንዱ የሆነው ሩቢ ቪዛ ኮንሰልቲንግ፤ በዓለማቀፍ ደረጃ ወደ ባህር ማዶ በሥራ፣ በጉብኝት፣ በቢዝነስና በኢንቨስትመንት ቪዛ ለመሄድ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን የቪዛ ማማከር አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡ ሦስቱ አርቲስቶች በብራንድ አምባሳደርነት የተሰየሙት ይህን ኩባንያና አገልግሎቱን ለማስተዋወቅና ለመወከል ነው ተብሏል፡፡
ከትናንት በስቲያ ሐሙስ፣ በሸራተን አዲስ፣ ሩቢ ቪዛ ኮንሰልቲንግን ለማስተዋወቅና የብራንድ አምባሳደሮችን ይፋ ለማድረግ በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኢትዮ ኤርስ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታረቀኝ ቶሎሳ ባደረጉት ንግግር፤ #እ.ኤ.አ በ2007 የተቋቋመው ኢትዮ ኤርስ ንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በሥሩ በርካታ ድርጅቶችን ያቀፈ፣ ለህብረተሰብ ችግር ፈቺ የሆኑ የተለያዩ ድርጅቶችን በማቋቋም ለበርካታ ሰዎች የሥራ ዕድልን የፈጠረና በሃገር ኢኮኖሚ ግንባታ የራሱን አስተዋፅኦ እያበረከተ የሚገኝ ትልቅ ተቋም ነው”  ብለዋል፡፡ ድርጅቱ አገሪቱ ለያዘችው የልማትና ብልፅግና ጉዞ በኢኮኖሚው፣ በቱሪዝሙ፣ የውጭ ምንዛሬን በማስገኘትና በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ በርካታ ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንደሚገኝም ዋና ሥራ አስኪጁ ገልፀዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ የብራንድ አምባሳደሮች ሆነው የተሰየሙት አርቲስቶች፣ ከሩቢ ቪዛ ኮንሰልቲንግ ጋር ለመስራት ዕድሉን በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፤ ምስጋናም አቅርበዋል፡፡
በቱሪዝም በውጭ ንግድና ኢንቨስትመንት ላይ አተኩሮ የሚሰራው ኢትዮ ኤርስ ንግድ እና ኢንቨስትመንት፤ ከሩቢ ቪዛ ኮንሰልቲንግ በተጨማሪ ትራቭል ሃይ ቱር፣ ሉክስ ትራቭል የመሳሰሉ ድርጅቶችን በስሩ እንደሚመራ ለማወቅ ተችሏል፡፡



Read 2917 times
Administrator

Latest from Administrator