Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 06 October 2012 13:38

መቐለ ዓደይ

Written by 
Rate this item
(19 votes)

ባለፈው ሳምንት “ፖለቲካ በፈገግታ” በሚለው አምዳችሁ ረድኤት መ. የተባሉ ፀሐፊ የጉዞ ማስታወሻ በሚል ስለ መቐለ ከተማ ጽፈው ያነበብኩ መሰለኝ፡፡ ቆይ ቆይ… ፀሐፊው የመጣጥፋቸውን ርዕስ በምንኛ ነው የፃፉት? በትግርኛ ነው በአማርኛ? “ጓል መቐሌ” ማለት ምንድነው? አማርኛና ትግርኛ ቀላቅለው ይሆን የጻፉት? ምናልባት የመቀሌ ልጅ ለማለት ተፈልጎ  ከሆነ “ጓል መቐለ” ነው መባል ያለበት፡፡ እግረ መንገዴን ትግርኛውንና አማርኛውን ባንቀላቅለው ብዬ ብመክርዎትስ፡፡
እኔማ ጓል መቐለ ሲል ስለ መቐለ ኮረዶች ያወራናል ብዬ ነበር የጠበቅኩት፡፡ ግና ስለ ጓል መቐለ ምንም አያወሳም፡፡ ፅሁፉ የሚያወራው ስለ መቐለ ከተማ ነው፡፡ አውራምባና ቆቦ በሉት! አርእስቱና ፅሁፉ ስለየትኛዋ?
እኔን ያልገባኝ ምን መሰላችሁ? ፀሐፊው ስለየትኛዋ መቐለ እንደፃፉ! ያቺ የተወለድኩባት መቐለ አልመስልህ አለችኝ እኮ! በጣም የገረመኝ ደግሞ ራስዎን ችለው አለመፃፍዎ ነው፡፡ “ማህሙድ ጋ ጠብቂኝ” የፃፉትን አቶ መሐመድ ሰልማንን ጠቅሰዋል /ሰው ጥራ ቢሉት…/ ፀሐፊው በተጨማሪ መቐለ በኤርትራ ዘፈን ፀሐፊው በከተማው መስተዳድር ስር ያለው ኤፍ ኤም 104.4 የሬዲዮ ጣቢያ እንኳን ከተማዋን በኤርትራውያኑ የሄለን መለስና በአብርሃም አፈወርቂ ዜማ ያስጨፍራታል ብለዋል፡፡ ግን ፍፁም ሐሰት ነው!
እንዲህ ያለው ተግባር በሬድዮ ጣቢያው እንደማይደረግ ለፀሐፊው ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ፡፡ እርግጥ መንግስታችን የሚከተለው የኖርማላይዜሽን  አገባብ በሁሉም ዘርፍ ይተገበራልና ሬዲዮ ጣቢያውም የተወሰነ የኤርትራ ሙዚቃ ያስገባ ይሆናል እንጂ እነረድኤት እንዳሉት ከተማውን የሚያውረገርግ ወይም የሚያሳብድ አይደለም፡፡ እንዲያውም ባይገርማቸው የአማርኛ ዘፈን ነው የሚበዛው፡፡  ፀሐፊው እንዳሉት ግን ሙሉ ቀን ሲያስጨፍር አይውልም፡፡ ኢዲቶሪያል ፖሊሲውም አይፈቅድለትም፡፡ እውነት ግን እንዳሉት ዞር ዞር ብለው ከተማዋን ጎብኝተዋል? ምነው ታዲያ የትግርኛ ዘፋኞቻችን ጆሮ ነሱዋቸው፡፡ ወይስ የእሳቸው ጆሮ የሚሰማው የኤርትራ ዜማ ብቻ ነው? ምናልባት እርስዎ መረጃ የለዎት ይሆናል እንጂ እስከ ኤርትራ ድረስ የሚደመጡ በሲንግልም በሙሉ አልበምም ያቀነቀኑ የእኛ ዘፋኞች አሉ እኮ! እና እነኝህን ጥሩ ጥሩ ጣዕም ያላቸውና ደሳስ የሚሉ ዜመኞቻችንን ወደ ኤርትራ ማስጠጋት ደስ አይልም፡፡እኔ የምለው ግን… እርስዎ እንዳሉት የኤርትራ ዘፈን ቢሰማስ ችግሩ ምንድነው? ህዝብ ከህዝብ ይቀራረባል እንጂ ሌላ ምን ይፈጠራል? እስቲ አንዲት ጥያቄ ልጠይቅዎ፡፡ ለመሆኑ የኤርትራና የትግራይ ዘፋኞችን /ዘፋኞች/ ለይተዋል? የሚለዩ ግን አይመስለኝም፡፡ ይህንን ለመለየት አንድም ትግርኛ ተናጋሪ አሊያም ደግሞ የሙዚቃ ሰው ለዚያውም ትግርኛ ዘፈኖች ላይ የሰሩ ሊሆኑ ይገባል፡፡ እርስዎ ግን እንዲያ አልመሰሉኝም፡፡
እስቲ በደንብ ስለማያውቋት ከተማ ትንሽ ልንገርዎ /ታሪክ ቢጤ በሉት!/ መቐለ ከተማ ያሁኑን ስያሜዋን ከማግኘቷ በፊት እንዳ መስቀል ትባል ነበር፡፡ ከአፄ ዮሐንስ ክፍለ ዘመን በፊት /ከተማዋ ከመቆረቆሯ በፊት/ የተለያዩ መንደሮች ነበሯት፡፡ እንዳ መድሃኒአለም፣ ማይ ሊሐም፣ እንዳ መስቀል የመሳሰሉት ነበር ስያሜያቸው፡፡ እንዳ መድሃኒአለም ቤተክርስትያን በወቅቱ በአረንጓዴ እፅዋት የተሸፈነ ገዳም ሲሆን ገዳሙን የአባ ታትዮስ ተከታይ የነበሩ አባ አብሳሊ የሚባሉ አስተዳዳሪ ነበሩ የሚመሩት፡፡ በወቅቱ አባ አብሳሊ የሚያስተምሯቸውን ዲያቆናት ጠዋትና ማታ ከመቁነናቸው በተጨማሪ ብርቱካን ያድሉዋቸው ስለነበር በትግርኛ “ተመቓቐሉ” /ተካፈሉ እንደማለት/ ይሏቸው ነበር፡፡ “ምምቕቓል” /ማከፋፈል እንደማለት/ መቐለ ስያሜዋን ያገኘችው… ከዚህ ነው የሚል አፈ-ታሪክ አለ፡፡
አፄ ዮሐንስ መቐለ ከተማን ከመመስረታቸው በፊት ብዙ ጊዜ መንበረ መንግስታቸው ደብረ ታቦርና ዓድዋ ነበር ይባላል፡፡ በኋላ ግና መንበረ መንግስታቸው የምትሆን ከተማ ሲመርጡ ከመቐለ ከተማ ወጣ ብላ በሃያ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አጉላዕ ከተማ ተመርጣ ነበር፡፡ ቢሆንም የመቐለ ከተማ አየሩና ንፋሱ ተስማሚ ሆኖ ስላገኙት፣ እሳቸው በድንኳን ተቀምጠው ቤተ መንግስታቸው እንዲገነባ አደረጉ፡፡ ቤተ-መንግስቱ በሁለት ጣሊያናውያን መሃንዲሶች በ1860 ተጀምሮ በ1864 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡ /አቶ ፀጋ ዘአብ የታሪክ ምሁር እንደገለፁት/
ቤተ-መንግስቱ በአሁኑ ሰዓት ለጎብኝዎች ክፍት ሲሆን የአፄ ዮሐንስ ዘውድ፣ የንጉሱ አልባሳት፣ አልጋ፣ ጎራዴዎችና የተለያዩ መድፎች እና ሌሎች ቅርሶች ይገኙበታል፡፡  ቤተ-መንግስቱን መጎብኘት የሚፈጥርብህን ስሜት አልነግርህም፡፡ /እርስዎ ግን ምን ጎብኝተው እንደመጡ አላውቅም!/
የመቐለ የተለያዩ አካባቢዎች የየራሳቸው ታሪክ አላቸው፡፡ ለምሳሌ እንዳ ስራ ቤት የሚባለው በቤተ መንግስቱና በአንዋር መስጊድ /የመቐለ አንዋር/ መሃከል የሚገኝ ሰፈር ሲሆን የንጉሱ ሰራተኞች - ጠጅ ጠማቂዎች፣ ምግብ አዘጋጆች፣ የቤተ መንግስቱ አገልጋዮች የሚኖሩበት ሰፈር ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ የስራ ቤት የሚል ስም የተሰጠው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ማንኛውም የመቀሌ   ነዋሪ በአንድ ላይ አብሮ ይኖርበታል፡፡
ሆሳዕና የሚባለው ሰፈር ደግሞ በጣም ፀጥታ የሰፈነበት ሰፈር ነው፡፡ እድሜ ለኮብል ስቶን… የውስጥ ለውስጥ መንገዱ ዝንጥ ብሎ በኮፊ ሃውስና፣ በቡና ቤቶችና በሬስቶራንቶች ተወሯል፡፡ ቢሆንም ያ’ ሰፈረ ሰላም /ሆሳዕና/ የነበረው ስሙ አሁንም በልዋጭነት ያገለግላል፡፡ በነገራችን ላይ መቐለ ቀን ላይ ሙቀት ያጣድፋታል፤ አመሻሽ ላይ ግና ንፋሱ ለዛ ያለው ስለሆነ በፍቅረኞች ጎዳና ማታ ማታ ተቃቅፈው የሚሄዱ ጥንዶች አይታጡም፡፡ ፍቅረኞች ጎዳና ማለት ከጠቅላይ ፍርድ ቤት /ድሮ ደጀን ጽ/ቤት የነበረው/ ወይም ኤፍ ኤም መቐለ 104.4 ማሰራጫ ጣቢያ  እስከ ጤና ጣቢያ ድረስ ያለው ጎዳና ነው፡፡ /ፀሐፊው ሳያውቁት አይቀሩም/
ሌላው ከመቐለ ሰፈሮች ሳይጠቀስ የማይታለፈው እንዳጡረታ የሚባለው ሰፈር ነው፡፡ እንዳ ጡረታ ማለት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጊዜና በደርግ መንግስት የነበሩት የደርግ ወታደሮችና መኮንኖች ጡረታ ሲወጡ የሚሰጣቸው የመኖሪያ ሰፈር ነው - ለመኖሪያነት፡፡ እንዳ ጡረታ ማለት በቀድሞ ቀበሌ 18 አሁን ጣቢያ ሐድነት የሚገኝ ነው፡፡
የመቐለ ልጅ ሆኖ ጠላ ሳይጠጣ ያደገ የለም፡፡ ምናልባት ከእምነት ጋር በተያያዘ ምክንያት ካልሆነ በቀር፡፡ የተለያዩ ዓይነቶች ጠላዎች አሉ:- ጉዕሽ፣ ፅራይ፣ ድቋ፣ ፊልተር፣ ሂፖ... እና ሌሎችም ስያሜዎች ይሰጧቸዋል፡፡ እነኝህን የሚጠጧቸው የተለያዩ ሰዎች ናቸው፡፡ ሂፖ ማለት ነጭ ጠላ ሲሆን በጣም ጠንካራ ነው፡፡ ይህንን የሚጠጡት ወጣቶችና የመጠጥ ልምዱ ያላቸው ናቸው፡፡ ድቋና ፅራይ ደግሞ የአዛውንቶች መጠጥ ነው፡፡ ጉዕሽ ደግሞ የቤት ልጆችና የሰፈር ሰው ነው የሚጠጣው፡፡ ይገርማችኋል! ልክ እንደ ስማቸው መለያየት የሚከፈቱበት ሰዓትም ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ከሌሊቱ 10፡30 ተከፍቶ ንጋት ላይ 12፡30 የሚጠናቀቅ ጠላ ቤት አለ፡፡ ይኸኛው ጠላ ቤት ለጉልበት ሰራተኞችና መናኸሪያ አካባቢ ለሚውሉ ለፍቶ አደሮች ነው፡፡ ጠዋት 2፡00 ሰዓትና 4፡00 እንዲሁም ማታ 12፡00 የሚከፈት አለ፡፡ ሁሉም ታዲያ በተለመደው ሰዓት ብቻ ነው የሚከፈቱት፡፡ ከዚህች ዝንፍ አይልም፡፡ ከዓመት ዓመት እንዲሁ ነው፡፡
እንዳልኳችሁ ጠላ ቤቶች በሽበሽ ናቸው፡፡ በቀናት የሚለዩ ሁሉ ጠላ ቤቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ እንዳ ዓርቢ ሮቡዕ /ሮብና ዓርብ/፣ እንዳ እነይ ጓልይ /የእናትና ልጅ/፣ እንዳ መረባዕ /ገረወይና ቤት /፣ እንዳ ሂፖ /ነጭ ጠላ /፣ ሰንበት ሰናብቲ /እሁድ / እንዳ ዓርቢ ዓቢዳ/ ጠላዋ ያበደች አርብ የሚያስውል/፣ እንዳ ወርቂ ስና /ወርቅ ጥርሷ ቤት/ የመሳሰሉት ከብዙዎቹ በጥቂቱ ናቸው፡፡ የመቀሌ ጠላ ቤቶች የውስጥ የማይፈተፈት ወሬ፣ ሐሜት፣ ፖለቲካ፣ ትዳር ወዘተ.. የለም፡፡ ህዝቡ ህወሓት የሰራውን እያደነቀ፤ የተበላሸውን እየነቀፈ፣ በቱባ ቱባ ባለስልጣናት እየቀለደ፤ በዋንጫ ጠላውን እያወራረደ ይጫወታል፡፡ ይቆዝማል፡፡
መቐለ ስትመጡ ጠላ ለመጠጣት ከፈለጋችሁ በዕዳጋ ብዕራይ /ሰንጋ ተራ/፣ ዓሰርተ አርባዕተ /አስራ አራት ቀበሌ/፣ ጅብሩኽ፣ እንዳ ጡረታ፣ ዒላላ፣ እንዳማርያም /ማርያም ቤተ ክርስትያን አካባቢ/ ጎራ በሉ፡፡ እኒህ ሁሉ ጠላ የሚሸጥባቸው ስፍራዎች ናቸው፡፡ በተለይ ዕዳጋ ብዕራይና 14 ቀበሌ እኩለ ቀን ላይ ከጠላ ቤቱ ውጭ ሰው መንገዱን ሞልቶት እያውካካ ጠላውን ሲጨልጥ ቢያዩ አይደንግጡ! የተለመደ ነው፡፡ የመቀሌ ሰው ጠላ የሚጠጣው ውጭ ሜዳ ላይ ነው፡፡ እዛ ሰፈር ከገቡ ባይተዋርነት የለም፡፡ ባይተዋር ልሁን ቢሉስ ማን እሺ ሊልዎት! ድሮ በደርግ ጊዜ እንዲህ ሜዳ ላይ ተሰበስበህ ጠላ መጠጣት፣ ፖለቲካ መቅደድና ባለስልጣንን መዘንጠል ቀርቶ ከሁለት ሰው በላይ አብሮ ሲጓዝ ከታየ ወንበዴ ተብሎ ተከርቸም ነው፡፡
መቐለ በደርጉ ጊዜ የተወሰኑ ቦታዎች መሄድ ክልክል ነበር፡፡ አንድ ሙሉ ቀበሌ፣ “የተከለከለ” ተብሎ ታጥሮ ማንም ሰው እንዲያልፍ አይፈቀድም ነበር፡፡ ምናልባት ዘመዶቹ እዚያ የታጠረው ቀበሌ ከሆኑ፣ ከቀበሌው  የይለፍ ወረቀት አውጥቶ የሚያልፍበት ጊዜ ነበር፡፡ አይ ጊዜ!
ስለ መቐለ ኮፊ ሃውስ ላውጋችሁ፡፡ አሁን አሁን አዲስ አበባ የጀበና ቡና የሚሸጡ ብዛታቸውና አይነታቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡
ምናልባት የመጀመሪያዎቹ ኮፊ ሃውሶች ከመቐለ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ ተጠቃሚው በረንዳ በርጩማው ላይ ተቀምጦ ወጪ ወራጁን እያየ አረፍ ብሎ እየተዝናና ነው ቡናውን የሚጠጣው፡፡  መቐለ በጣም አሪፍና ደስ የምትል ከተማ ነች /ከተማህን ብዙ አዳነቅሀት እንዳትሉኝ/ የመሃል አገር ሰው መጥቶ ባይተዋርነት እንዳይሰማው የምታደርግ ከተማ ነች፡፡
የመቐለ ሰው በአማርኛ ብታናግረው በአማርኛ ይመልስልሃል፡፡ አማርኛ ካልቻለ በትግርኛ ይመልስልሃል፡፡
አንድ ወግ ልንገራችሁ:- አንድ የመሃል አገር ሰው መቐለ መጥቶ ጠላ ሊጠጣ ወደ አንድ ጠላ ቤት ይገባና፤ “ጠላ አለ?” ይላታል - ለባለጠላዋ “ተወዲኡ!”’ አለችው፡፡ እሱም ቀበል አድርጎ ‘’ውድም ቢሆን ስጪኝ እባክሽ‘’ አላት፤ ባለ ጠላ ቤቷ ‘’ተወዲኡ‘’ ስትል አለቀ ማለቷ ነበር፡፡  ዕዳጋ ሶኒ የሚባለው የገበያ ቦታ ዘመናዊ ነው፡፡ መሃል ከተማው ውስጥ ሲሆን ሰፋ ያለና የድሮው የገበያ ህንፃን ባልለቀቀ ዲዛይን የተሰራ ዘመናዊ የገበያ ማእከል ነው፡፡ የገበያው ቦታ ድሮ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ጊዜ አያቶቻችን በወንዛችን መተዳደር አለብን፣ የመሃል አገር ሹመኛ እኛን አያስተዳድረንም፣ ብለው ላነሱት አመፅ፣ ጃንሆይ የእንግሊዝ አውሮፕላንና አብራሪዎችን ተጠቅመው /ረድኤት እንዳሉት/ ኮረኮሙት ሳይሆን እህል፣ አህያ፣ ሰው፣ ሽንኩርት፣ ጌሾ እና ሌሎችም ተቀላቅለው ለመለየት ያቃተበት ጭፍጨፋ ነው የተፈፀመው፡፡ በወቅቱ ለተጨፈጨፉት ሰዎች መታሰቢያ ተብሎ  የድሮ የገበያው ህንፃዎች በመቃብር ዲዛይን ጣራቸው አጎንብሶ የተሰራ ነው፡፡የመቐለ ልጆች በስራ ፈጠራ ላይ ቀልድ አያውቁም፡፡ ኮብል ስቶንን እዚያ አዲስ አበባ ነፃ ሚዲያው ሲያጣጥለው እየሰሙ ያማቸዋል፤ ያንገበግባቸዋል፡፡
በብረታ ብረትና በእንጨት ስራ የተሰማሩት የትየለሌ ናቸው፡፡ ባለፈው ጊዜ “ባለ ራዕዮቹ” የሚለው ዘጋቢ ፊልም ውስጥ ያሉት የፅዳት ሰራተኞች ስራውን ሲጀምሩ ስድስቱ የቢ.ኤ ተመራቂዎች ነበሩ፡፡ የመንግስት ስራ ጠብቀን መኖር ልክ ስላልሆነ የራሳችን ስራ ለምን አንጀምርም ብለው የከተማ ፅዳት ውስጥ የገቡ ጀግኖች ናቸው፡፡ አሁን የት ደረሱ ብትሉ ያው በቴሌቪዥን እንደተናገሩት ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት “ፖለቲካ በፈገግታ” በሚለው አምዳችሁ ረድኤት መ. የተባሉ ፀሐፊ የጉዞ ማስታወሻ በሚል ስለ መቐለ ከተማ ጽፈው ያነበብኩ መሰለኝ፡፡ ቆይ ቆይ… ፀሐፊው የመጣጥፋቸውን ርዕስ በምንኛ ነው የፃፉት? በትግርኛ ነው በአማርኛ? “ጓል መቐሌ” ማለት ምንድነው? አማርኛና ትግርኛ ቀላቅለው ይሆን የጻፉት? ምናልባት የመቀሌ ልጅ ለማለት ተፈልጎ  ከሆነ “ጓል መቐለ” ነው መባል ያለበት፡፡ እግረ መንገዴን ትግርኛውንና አማርኛውን ባንቀላቅለው ብዬ ብመክርዎትስ፡፡እኔማ ጓል መቐለ ሲል ስለ መቐለ ኮረዶች ያወራናል ብዬ ነበር የጠበቅኩት፡፡ ግና ስለ ጓል መቐለ ምንም አያወሳም፡፡ ፅሁፉ የሚያወራው ስለ መቐለ ከተማ ነው፡፡ አውራምባና ቆቦ በሉት! አርእስቱና ፅሁፉ ስለየትኛዋ?

Read 6581 times Last modified on Saturday, 06 October 2012 13:46