Saturday, 28 May 2022 13:34

የኢትዮጵያ ታሪክ-የሀያላኑ ጣልቃ ገብነትና የሰሜኑ ጥያቄ” መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በሀጋሪ ኤልሪች “Ethiopia And The Challenge Of Independence” በሚል በእንግሊዘኛ የተጻፈው መፅሐፍ በዳንኤል ሙለታ “የኢትዮጵያ ታሪክ የሃያላኑ ጣልቃ ገብነትና የሠሜኑ ጥያቄ” በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ ተመልሶ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ አርትኦቱ “በሙሉቀን ታሪኩ የተሰራለት ይሄው መፅሐፍ ኢትዮጵያ ከምዕራቡ ዓለም ከተጋረጡባት ተግዳሮቶች ጀምሮ አብዛኛውን የኢትዮጵያን ታሪክና ኢትዮጵያ ተጋፍጣ  ያለፈችበትን ታሪክ የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡
በ12 ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ332 ገፅ የተመጠነው መፅሀፉ በ250 ብርና በ25 ዶላር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በዋናነት በእነሆ መፅፍት መደብር እንደሚከፋፈልና በሁሉም አዟሪዎች እጅ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

Read 11070 times