በመላው አለም ግጭትና ጦርነትን ጨምሮ በተለያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሚሊዮን ማለፉንና ከእነዚህም መካከል 60 ሚሊዮን ያህሉ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መሆናቸውን ተመድ አስታውቋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በሳምንቱ መጀመሪያ ይፋ ባደረገው አዲስ መረጃ እንዳለው፤ ከ14 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ያፈናቀለውን የዩክሬን ጦርነት ጨምሮ የተለያዩ የአለማችን አገራት ሰዎች ግጭት፣ ብጥብጥ፣ እስራት፣ ግድያና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በመሸሽ ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በ2012 የፈረንጆች አመት 41 ሚሊዮን የነበረው የአለማችን ተፈናቃዮች ቁጥር፣ በ2019 ላይ 79.5 ሚሊዮን፣ በ2020 ከ82 ሚሊዮን በላይ፣ በአሁኑ ወቅት ይህ ቁጥር ከ100 ሚሊዮን ማለፉንም የኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል፡፡
Published in
ከአለም ዙሪያ
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል