Saturday, 04 June 2022 15:18

አለም… ጤና እና ክብርን ለሴቶች እውን ታድርግ፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

  ፌስቱላ ያብቃ….May 23 …አመታዊ የፊስቱላ ቀን፡፡
እ.ኤ.አ እስከ 2030 ፌስቱላ ከአለም ላይ እንዲወገድ ሀገራት ተስማምተዋል፡፡
ሰኞ  እ.ኤ.አ ሜይ 23/2022 በአለም አቀፍ ደረጃ ፊስቱላ ያብቃ በሚል መሪ ቃል እለቱ ተከብሮ ውሎአል፡፡ ሴት ልጆች ልጅ በሚወልዱበት ጊዜ በሚፈጠረው በማህጸንና አካባቢው መቀደድ ምክንያት የሚከሰተው የፊስቱላ ህመም ባለም ላይ ጨርሶ እንዲወገድ ለማድረግ አስፈላ ጊውን እውቀት ለህብረተሰቡ በየአመቱ የሚሰጥበት እንዲሁም ፊስቱላ ምን ያህል ጎጂ መሆኑን አጉልቶ ለማሳየት እንዲቻል በየአመቱ እ.ኤ.አ ሜይ 23 የፌስቱላ ቀን ሆኖ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ ዘንድሮም በተለይም ሐምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል በድረ ገጹ የሚከተሉትን ለንባብ ብሎአል፡፡
በአለም ላይ ሴቶች በፌስቱላ ምክንያት ከሚደርስባቸው የጤና ቀውስ እና በዚያም ተያይዞ ከሚከሰተው መገለል ነጻ እንዲሆኑ፤
በአለም ላይ ያሉ ሴቶች ጤናማ በሆነ መንገድ ልጆቻቸውን እዲወልዱ እና የዘገየ ወይንም በምጥ ጊዜ የተለያየ ችግር እንዳይገጥማቸው ለማድረግ፤
በአለም ላይ ያሉ ሴቶች ምንም እንኩዋን በገጠር ወይንም እርቀት ካለው ቦታ ቢኖሩ የእናትነት ጤናቸው እንዲከበርላቸው ወይንም በቀላሉ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ፤
አለም ጤና እና ክብርን ለሴቶች እውን እንድታደርግ ፤     
ከላይ የተዘረዘሩትን ቁም ነገሮች እውን ለማድረግና አለም ከፌስቱላ ነጻ እንድትሆን የበኩ ሉን ጥረት የሚያደርገው በኢትዮጵያ የሚገኘው ሐምሊን ፌስቱላ ጠንክሮ በመስራት ላይ መሆኑን እለቱን በማስመልከት ለመላው አለም በድረገጹ ይፋ አድርጎዘል፡፡በኢትዮያ የሚገ ኘው ሐምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል ፌስቱላን በሚመለከት የሚከተሉትን ነጥቦች በተጨማሪ ለንባብ አቅርቦአል፡፡
በኢትዮጵያ ከ70% በላይ የሚሆኑ ሴቶች ልጆቻቸውን የሚወልዱት በቤታቸው ነው፡፡በቤታቸው በሚወልዱበት ጊዜም የህክምና እርዳታ በቅርብ ስለማያገኙ የፌስ ቱላን ሕመም ለመጨመር አንዱ መንገድ ነው፡፡ ሴት ልጆች በፌስቱላ ምክንያት ሽንትን ያለመቆጣጠር በመሳሰሉት ምክንያቶች ከቤተሰብ እና አካባቢያቸው ከመለየት ጀምሮ የአካል ጉዳት(ፓራላ ይዝድ) እስከመሆን ይደርሳሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወደ 93% የሚሆኑት የፌስቱላ ተጎጂዎች የሚገላገሉት የሞተ ህጻን ሊሆን ይችላል፡፡
ሐምሊን ፊስቱላ እስከአሁን ባለው ስራው ለ60.000 ሴቶች የፊስቱላ ቀዶ ሕክምና በማድረግ በሕይወታቸው ላይ ለውጥ ያመጣ ሲሆን እስከ 100.000 የሚደርሱ ሴቶችን በሰላም ሕይወታቸውን ለመኖር የሚያስችላቸው ሕክምና እንዲደረግላቸው እቅድም አለው፡፡ ሐምሊን ፌስቱላ ሐኪም ቤትን በኢትዮጵያ የከፈቱት ጥንዶች Drs Reg and Catherine በኢትዮጵያ ለመስራት በገቡባቸው የመጀመሪያዎቹ ሶስት አመታት ወደ 300 የሚሆኑ ሴቶችን በቀዶ ሕክምና ወደ ትክክለለኛው ሕይወታቸው እንዲመለሱ ረድተዋል፡፡
የህመምተኞችን ሁኔታ የሚገመግሙት ኦፊሰሮች እንዳገኙት እውነታ ከሆነ ወደ 31.000 የሚገመቱ የፌስቱላ ታማሚዎች አሁንም ድረስ ጤናቸው በአካላዊ ጉዳት የሚታይ ሲሆን በፌስቱላ ምክንያት በደረሰባቸው ሕመምና ችግር ምክንያት ከቤተሰ ባቸው እንዲሁም ከአካባቢያቸው ተገልለው ይኖራሉ፡፡ በየአመቱ በኢትዮጵያ ወደ 3,000 የሚጠጉ ሴቶች በፌስቱላ ተጎጂ ናቸው፡፡
ወደ 22,344 የሚሆኑ ህጻናት በሐምሊን ሚድዋይፎች እጅ ተወልደዋል፡፡ በ2021 የበጀት አመት የእናቶችን እና የህጻናትን ደህንነት በተለይም በርቀት ለሚገኙት የተደረገ አገልግሎት ነው፡፡ 32,938 የሚሆኑ እርጉዝ እናቶች የእርግዝና ክትትል አድር ገው ነበር፡፡ ፌስቱላን በመከላከል ረገድ በገጠሩ አካባቢዎች ሚድዋይፍ ነርሶች በጣም አስፈላጊ መሆናቸው እሙን ነው፡፡
1,052 ሴቶች ስልጠና ያገኙ ሲሆን በሐምሊን ፊስቱላ በተቋቋመው በደስታ መንደር እና የፌስቱላ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ክልላዊ ሆስፒታሎች በ2021 ትምህርት አግኝተዋል፡፡
ፌስቱላን እንዲወገድ መርዳት ለመላው ሴቶች በፍቅርና በጥንቃቄ ሕክምናውን እንደመ ስጠት ይቆጠራል፡፡ የካትሪን ሐምሊን ፕሮግራም ሴቶችን ህይወታቸውን በራሳቸው አቅም እና ክብር እንዲመሩ ያስችላቸዋል፡፡  በአውስትራሊያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪም በነበሩት ዶ/ር ካትሪን እና ዶ/ር ሬግ ሐምሊን አማካኘነት የተቋቋመው ፊስቱላ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በስድስት መስተዳድሮች በሚገኙ ሆስፒሎች ቅር ንጫፍ በመክፈት ሴቶች ፌስቱላ ከተባለው አስከፊ ሕመም እንዲድኑ የሚያስችል ሕክምና በመስጠት ላይ ነው፡፡
የፌስቱላ ታማሚዎች ወደመጡበት ሳይመለሱ ወይንም ከህክምና ክትትል ርቀው እንዳይ ሄዱ ወይንም በደንብ እስኪድኑ ድረስ በአቅማቸው የልማት ስራዎችን እየሰሩ እንዲቆዩ የተዘጋጀው የደስታ መንደር ሌላው ተቋም ነው፡፡ በፌስቱላ ሕመም ምክን ያት በሆስፒታል ተኝተው የነበሩ ሴቶች በደስታ መንደር ሲገቡ የተለያዩ የከብት እርባ ታዎ ችን፤ የጉዋሮ አትክልቶችን የመሳሰሉትን ነገሮች እያረቡ እና እየተከሉ እራሳቸውን የሚ ረዱበትን እንቅ ስቃሴ ያደርጋሉ። ከዚህም በተጨማሪ የሃምሊን ኮሌጅ በመባል የሚታወቀው የትምህርት መንደር ተወዳዳሪ የሆኑ ሴት ልጆች በሚድዋይቭ (አዋላጅ) ነርስነት ተምረው የሚመረቁበት ሲሆን ሚድዋይፎቹ ከተመረቁ በሁዋላ ወደመጡበት የገጠር አካባቢ በመመለስ ሴቶች በምጥ እንዳይጎዱ እና ለፊስቱላ እንዳይጋለጡ የሚያደርግ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ ይመ ደባሉ፡፡ በሐምሊን ኮሌጅ የተመረቁት ሚድ ዋይፎች ከ50 በላይ በሆኑ ክሊኒኮች የሚሰሩ ሲሆን እስከአሁን ባለው መረጃ ወደ (550) የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ፌስቱላን ለማጥፋት ታትረው እየሰሩ ነው፡፡
የማህጸን ፌስቱላ ማለት የእናቶች ጤንነት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰብአዊ መብትም ነው። ምክንያቱም ሁሉም ሰው በሕይወቱ ክብር ማግኘት ስለሚገባው ነው፡፡ ፌስቱላ ሲታከም የእናቶችን ሕይወት ማዳን ብቻም አይደለም። ተያይዞ የሚመጣውን መገለል፤ ድህነት፤ የትም ህርት ማጣት የመሳሰሉትን ችግሮች ማስወገድም ትልቁ እና ተያያዥ የሆነ አገልግሎት ነው፡፡    
23 May 2022 አለም አቀፍ የፌስቱላ ቀንን ምክንያት በማድረግ የወጣው የተባበሩት መን ግስታት አለም አቀፍ ዘገባ እንደሚያስነብበው የማህጸን ፌስቱላን ቀለል አድርጎ ወይንም ቸል ብሎ ማለፍ ይሞከር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከወሊድ ጋር በተያያዘ ሴቶችን የሚገጥማቸው አጥፊ ወይንም ጎጂ የሆነ ጤና ማጣት፤ የማህበራዊ ቀውስ፤ የስነልቡና ጉዳት ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ 90% የሚሆኑ ጽንሶች በማህጸን እያሉ ህይወታቸውን የሚያጡበት ወይንም የሚጨናገፉበት አጋጣሚም የሚፈጠርበት ነው። ስለዚህም እርግጠኛ መሆን የሚቻለው ችግሩ ከደረሰ በሁዋላ ሕክምና ሊደረግላቸው ይገባል ብቻ ሳይሆን አስቀድሞውኑም ሊከላከሉት የሚቻል መሆኑን ነው፡፡
በጥንቃቄ ሁሉም ሊያውቃቸው የሚገቡ ቁምነገሮች አሉ፡፡ የተለያዩ ከማህጸን ጋር በተያያዘ ተጠቃሽ የሚሆኑ የፌስቱላ አይነቶች ያሉ ሲሆን  በብዛት የሚታወቀው በመውለጃ እና በሽንት ፊኛ አካባቢ ያለው ፊስቱላ (የሰውነት መቀደድ) ቢሆንም በመውለጃ እና በመጨረሻው የአንጀት ክፍል (ወደሰገራ መውጫ)፤ በመውለጃ አካል እና በሽንት መስመር፤ በመውለጃ አካል እና ሽንትን ወደ ማጠራቀሚያው በሚያስገባው መስመር ላይ እንዲሁም በሽንት ፊኛ እና በማህጸን መካከል የሚፈጠሩ ቀዳዳዎች የፊስቱላ ህመምን ያመጣሉ። ፌስቱላ ከድህነት እና ከጾታ እኩልነት ጋር የተያያዘ ችግር ነው፡፡ የማህጸን ፌስቱላ የሚባለው ሕመም በመውለጃ አካል እና ዙሪያውን ባሉ የሰውነት ክፍሎች የሚከሰት ቀዳዳ ሲሆን ይህ የሚፈጠረውም በልጅነት ከሚከሰት እርግዝና፤ በቅርብ የሆነ የህክምና እርዳታ ካለማግኘት የተነሳ በሚፈጠር የተራዘመ ምጥ ምክንያት ነው፡፡
የተባበሩት መንግስታት እንደሚገልጸው የፌስቱላ ጉዳት በሁሉም ቦታ የሚኖር ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በአደጉት ሀገራት ግን አይታይም፡፡ ይህ ችግር በስፋት የሚስተዋለው ባላደጉት ሀገራት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ወደ 500.000 የሚሆኑ ሴቶችና ልጃገረዶች በህመሙ ይሰቃያሉ። መታወቅ ያለበት ግን በምንም ምክንያት ቢከሰት ሊታከም የሚችል መሆኑን እና ነው ከዚያም በላይ ትልቁ ነገር ችግሩ ሳይደርስ ሊከላከሉት የሚቻል መሆኑ ነው፡፡
ሴት ልጆች ካለ እድሜአቸው እንዳ ይዳሩ ወይንም ልጅ እንዳያረግዙ እንዲሁም በቤታቸው ካለህክምና እርዳታ እንዳይወልዱ ማድረግ፤ ሕክምናው በአቅራቢያቸው እንዲኖር ማድረግ ቀዳሚው እርምጃ ነው የተባበሩት መንግስታት እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኘው ሐምሊን ፌስቱላ በአለም አቀፉ የፌስቱላ ቀን ለንባብ ያበቁዋቸው መረጃዎች እንዳስነበቡት፡፡

Read 11077 times