Saturday, 04 June 2022 18:19

ትምባሆ በመላው አለም በየአመቱ 8 ሚ. ሰዎችን ይገድላል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በትምባሆ ልማት 600 ሚ. ዛፍ፣ 200 ሺህ ሄክታር መሬትና 22 ቢ. ቶን ውሃ ይባክናል

             በመላው አለም በየአመቱ ከ8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በትምባሆ ምክንያት ለሞት እንደሚዳረጉና አብዛኞቹ ሞቶች የሚከሰቱትም በአለማችን ከሚገኙ ትምባሆ አጫሾች መካከል 80 በመቶው በሚገኙባቸው መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት መሆኑን ሰሞኑን የወጣ አለማቀፍ ሪፖርት አመልክቷል፡፡
ትምባሆ በአብዛኛው የሚለማው መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት መሆኑንና በአገራቱ ለምግብ ሰብሎች ልማት ይውል የነበረ ከፍተኛ መጠን ያለው ሃብት እንደሚባክን የጠቆመው የአለም የጤና ድርጅት ያወጣው አለማቀፍ ሪፖርት፣ በትምባሆ ልማት ሳቢያ በመላው አለም በየአመቱ 600 ሚሊዮን ያህል ዛፎች እንደሚጨፈጨፉ፣ 200 ሺህ ሄክታር መሬት እና 22 ቢሊዮን ቶን ውሃ እንደሚባክንም አመልክቷል፡፡
ከትምባሆ ጋር በተያያዘ በየአመቱ ወደ አየር የሚለቀቀው በካይ ካርቦንዳይኦክሳይድ 84 ሚሊዮን ቶን ያህል እንደሚደርስና የትምባሆ ምርቶች ከ7000 በላይ መርዛማ ኬሚካሎችን የያዙ እንደመሆናቸውና ተረፈ ምርታቸው ብዙ እንደመሆኑ በአካባቢ ብክለት ሚናቸው ከፍ ያለ እንደሆነም አመልክቷል፡፡


Read 1909 times