Thursday, 09 June 2022 11:15

የፓስፖርት አገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር ለመፈጸም የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

Written by 
Rate this item
(0 votes)
ኢትዮ ቴሌኮም፤ አዲስ ፓስፖርት የሚያወጡ፣ የሚያሳድሱና ምትክ የሚፈልጉ ደንበኞች ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹና አስተማማኝ የሆነውን የዘመኑን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ቴሌብርን ተጠቅመው፣ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ሆነው የአገልግሎት ክፍያቸውን መፈጸም እንዲችሉ ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጋር ስምምነት ፈጸመ፡፡
በዛሬው ዕለት የተደረገው የአጋርነት ስምምነት በዋናነት የኢትዮ ቴሌኮም የቴሌብር አገልግሎትን ከፓስፖርት አገልግሎት ክፍያ አሰራር ጋር በማስተሳሰር በየጊዜው እያደገ የመጣውን የደንበኞች የክፍያ አማራጭ የአገልግሎት ፍላጎት ቀላልና አስተማማኝ በማድረግ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት፣ ለማሳደስ፣ ለጠፋ ምትክ ለማውጣትና የተበላሸ እንዲስተካከልላቸው የሚፈልጉ ደንበኞች የአገልግሎት ክፍያቸውን ባሉበት ቦታ በቀላሉ መክፈል ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ደንበኞች ለከፈሉት የአገልግሎት ክፍያ ማስረጃው በቅርብ እንዲኖራቸው፣ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣትም ሆነ ለማሳደስ ወደ ኤጀንሲው ሲሄዱ የሚደርሰውን የገንዘብና የጊዜ ብክነት፣ የጉልበት ድካምና የደላሎች ወከባ በመቀነስ ለደንበኞች ምቹና ቀልጣፋ የአገልግሎት ክፍያ አማራጭ ለማቅረብ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
Read 4257 times