Saturday, 13 October 2012 10:13

ነፍሰጡሯ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ተገደለች

Written by  መልካሙ ተክሌ melkamutekle@gmail.com
Rate this item
(2 votes)

ጉዳዩ ከተጣራ በኋላ በአዛዡ ላይ ክስ ሊመሰረት እንደሚችል የተናገሩት ተወካዩ፤ የከተማዋን ፀጥታ ለማስጠበቅ የተቀሩት ሃያ አንድ ፖሊሶች በቂ ባለመሆናቸው ከአጐራባቿ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ  ተጨማሪ ፖሊሶች በውሰት መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡40ሺህ ያህል ነዋሪዎች ያሉዋት የአረካ ከተማ ተመሳሳይ አሰቃቂ ወንጀል በቅርብ ጊዜ እንዳላስተናገደች እማኞች ገልፀው ሕዝቡ በዚህ በመቆጣቱ ግብታዊ ርምጀ እንዳይወሰድ የተጠርጣሪው ቤት በፖሊስ እየተጠበቀ ነው፡፡ ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሆነና ለአዲስ አድማስ የገለፁት የከተማዋ አስተዳደር የከንቲባ ጊዜያዊ ተወካይ አቶ ወንድሙ ዋቤቶ፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰባት ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንና የፖሊስ ጣቢያው አዛዥ ተገምግመው ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን ገልፀዋል፡፡ በደቡብ ብሔራዊ ክልል አረካ ከተማ ነዋሪዋ የሶስት ወር ነፍሰ ጡር ወይዘሮ ትዕግስት ጫካ፤ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት በከተማዋ ፖሊስ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ተገደለች፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ትዳር ከመሠረተች አንድ አመት አልሞላትም፡፡ መስከረም 19 ቀን 2005 ዓ.ም በተከሰተው ግጭት ባለቤቷና በንግድ ሥራ የሚተዳደር ግለሰብ በተነሳ ጠብ በጥይት ሕይወቷ አልፏል፡፡ የአካባቢው ምንጮች ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት ከሆነ የጠቡ መነሻ የሟች ባለቤት ከሁለት ወር በፊት ጨረታ አሸንፎ ተጠርጣሪው ልቀቅልኝ ብሎት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ጊዜ እንደዛተበትና ይህንኑ ለማመልከት ከባለቤቱ ጋር ወደ ጣቢያ ይሄዳል፡፡ ተጠርጣሪውና ተባባሪዎቹ የፖሊስ ጣቢያውን ግቢ በሃይል በመጣስ ገብተው ተኩስ በመክፈት ነፍሰጡሯን ሴት እንደገደሉና ባለቤቷ ቆስሎ በሕክምና ላይ እንደሚገኝ ገልፀውልናል፡፡ ገና በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዳሉና ዋና ተጠርጣሪው ከባንክ ገንዘብ ላውጣ በማለት በቁጥጥር ሥር ከዋለበት ወደ ባንክ በአጃቢ ፖሊስ ከሄደ በኋላ 140ሺህ ብር አውጥቶ ለማምለጥ ሲሞክር በድጋሚ በቁጥጥር ሥር ውሏል ብለዋል ምንጮቹ፡፡ ሰባት ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ውለዋልጉዳዩ ከተጣራ በኋላ በአዛዡ ላይ ክስ ሊመሰረት እንደሚችል የተናገሩት ተወካዩ፤ የከተማዋን ፀጥታ ለማስጠበቅ የተቀሩት ሃያ አንድ ፖሊሶች በቂ ባለመሆናቸው ከአጐራባቿ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ  ተጨማሪ ፖሊሶች በውሰት መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡40ሺህ ያህል ነዋሪዎች ያሉዋት የአረካ ከተማ ተመሳሳይ አሰቃቂ ወንጀል በቅርብ ጊዜ እንዳላስተናገደች እማኞች ገልፀው ሕዝቡ በዚህ በመቆጣቱ ግብታዊ ርምጀ እንዳይወሰድ የተጠርጣሪው ቤት በፖሊስ እየተጠበቀ ነው፡፡ ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሆነና ለአዲስ አድማስ የገለፁት የከተማዋ አስተዳደር የከንቲባ ጊዜያዊ ተወካይ አቶ ወንድሙ ዋቤቶ፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰባት ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንና የፖሊስ ጣቢያው አዛዥ ተገምግመው ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን ገልፀዋል፡፡ በደቡብ ብሔራዊ ክልል አረካ ከተማ ነዋሪዋ የሶስት ወር ነፍሰ ጡር ወይዘሮ ትዕግስት ጫካ፤ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት በከተማዋ ፖሊስ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ተገደለች፡፡ ወ/ሮ ትዕግስት ትዳር ከመሠረተች አንድ አመት አልሞላትም፡፡ መስከረም 19 ቀን 2005 ዓ.ም በተከሰተው ግጭት ባለቤቷና በንግድ ሥራ የሚተዳደር ግለሰብ በተነሳ ጠብ በጥይት ሕይወቷ አልፏል፡፡ የአካባቢው ምንጮች ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት ከሆነ የጠቡ መነሻ የሟች ባለቤት ከሁለት ወር በፊት ጨረታ አሸንፎ ተጠርጣሪው ልቀቅልኝ ብሎት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ጊዜ እንደዛተበትና ይህንኑ ለማመልከት ከባለቤቱ ጋር ወደ ጣቢያ ይሄዳል፡፡ ተጠርጣሪውና ተባባሪዎቹ የፖሊስ ጣቢያውን ግቢ በሃይል በመጣስ ገብተው ተኩስ በመክፈት ነፍሰጡሯን ሴት እንደገደሉና ባለቤቷ ቆስሎ በሕክምና ላይ እንደሚገኝ ገልፀውልናል፡፡ ገና በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዳሉና ዋና ተጠርጣሪው ከባንክ ገንዘብ ላውጣ በማለት በቁጥጥር ሥር ከዋለበት ወደ ባንክ በአጃቢ ፖሊስ ከሄደ በኋላ 140ሺህ ብር አውጥቶ ለማምለጥ ሲሞክር በድጋሚ በቁጥጥር ሥር ውሏል ብለዋል ምንጮቹ፡፡ ሰባት ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ውለዋል

 

Read 3986 times Last modified on Saturday, 13 October 2012 10:29