Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 13 October 2012 10:29

በስህተት በተቀበረው ህፃን አስከሬን ጉዳይ ክስ ቀረበ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እያካሄደ ነውልጄን ያለአግባብ ወስደው የቀበሩት ሰዎች በህግ ሊጠየቁ ይገባል - እናትበየካቲት 12 ሆስፒታል በህክምና ላይ ቆይቶ ህይወቱ ያለፈውን የአንድ ዓመት ከ6 ወር ህፃን ብሩክ ጣሰውን አስከሬን የአዲስ አበባ ጽዳትና ውበት መናፈሻ በስህተት ወስዶ በመቅበሩ የህፃኑ ወላጆች ክስ መሰረቱ፡፡ በሆስፒታሉ ለአራት ቀን ቆይቶ መስከረም 27 ቀን 2005  ዓ.ም ህይወቱ ያለፈው ህፃን እናት ወ/ሮ ፀሐይ ታመነ እንደተናገሩት፤ ልጃቸው ህፃን ብሩክ ጣሰው ባጋጠመው ህመም ምክንያት የህክምና እርዳታ ለማግኘት መስከረም 24 ቀን 2005 ዓ.ም ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ይገባል፡፡በሆስፒታሉ የነበረውን የሕክምና ቆይታ አጠናቆ መስከረም 27 ቀን 2004 ዓ.ም ህይወቱ ያልፋል፡፡

እንደ ወላጅ እናቱ ገለፃ፤ የሆስፒታሉ ሐኪሞችና ነርሶች ወደ ቤታቸው ሄደው እረፍት እንዲያደርጉና አስከሬኑን ማምሻቸውን መውሰድ እንደሚችሉ ይነግሯቸዋል፡፡  እናት ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፡፡ ከቆይታ በኋላ አስከሬን ለማውጣት ወደ ሆስፒታሉ የተጓዙት የህፃኑ ቤተሰቦች አስከሬኑ እንደሌለ ይነገራቸዋል፡፡ ሁኔታው በእጅጉ ያስደነገጣቸው ቤተሰቦችም፣ አስከሬኑ ወዴት እንደሄደ አጥብቀው ይጠይቃሉ፡፡ በዚህ መሃከልም የአዲስ አበባ ጽዳትና ውበት መናፈሻ ሰዎች በዕለቱ ከሆስፒታሉ ከወሰዷቸው ሰባት ቤተሰቦቻቸው ያልቀረቡና በማዘጋጃ ቤት የሚቀበሩ አስከሬኖች ጋር በመቀላቀል የህፃኑን አስከሬን ይዘው እንደሄዱ ይነግሯቸዋል፡፡ በጉዳዩ በጣም ያዘኑትና የደነገጡት የህፃኑ እናትና ቤተሰቦች የጽዳትና ውበት መናፈሻ ድርጅቱ አስከሬኑን እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ፡፡ ድርጅቱ አስከሬኑን መቅበሩንና ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ አውጥቶ መስጠት እንደማይችል ይገልጽላቸዋል፡፡ ሁኔታው ከሐዘንም በላይ ሐዘን ሆኖባቸው በአስከሬን ክፍል ሠራተኞች ስህተት የልጃቸውን አስከሬን ለመቅበር ባለመቻላቸው ጉዳዩን ለፖሊስ ያመለክታሉ፡፡ ክሱ የቀረበለት የጃንሜዳ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ፣ ስለጉዳዩ ምርመራ ማድረግ የጀመረ ሲሆን ተፈፀመ በተባለው ጉዳይ ላይ ሆስፒታሉ ምላሹን እንዲሰጥ ደብዳቤ መፃፉንና ምላሹን እየተጠባበቁ እንደሆነ ምርመራውን የያዙት ሣጅን ዮናስ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡

 

Read 3681 times Last modified on Saturday, 13 October 2012 10:37