Saturday, 25 June 2022 20:32

ታሪክ - ለልጆች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ውሻውና አጥንቱ

            ውድ ልጆች፡- ከዚህ ታሪክ የምንማረው ቁምነገር፣ ማንንም በቅጡ ሳናውቅ ገጽታውን ብቻ አይተን ወደ ንቀትና ማሾፍ መግባት እንደሌለብን ነው። እጃቸው ላይ ልንወድቅ እንችላለንና፡፡

               በአንድ ወቅት፣ ምግብ ፍለጋ ቀንና ሌሊቱን በየጎዳናው ላይ ሲዞር የሚውል የሚያድር አንድ ውሻ ነበረ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ከዚህ በፊት አግኝቶት የማያውቀው ዓይነት ጥሩ አጥንት ያጋጥመውና በአፉ ይዞ ጉዞ ይጀምራል - ወደ ቤቱ፡፡ በመንገዱ ላይ ያለውን ወንዝ ሊሻገር ሲል ታዲያ አንድ ሌላ ውሻ እንደሱው አጥንት በአፉ መያዙን ያስተውላል፡፡ ራሱን ከጉዞ ገታ አድርጎ ውሻው ላይ አፈጠጠ፡፡ አስፈራርቶ አጥንቱን ሊቀማው ነው ያሰበው፡፡ እናም ቁጣውን በጩኸት ለመግለጽ አፉን ሲከፍት አጥንቱ አምልጦት ወንዙ ውስጥ ገባ፡፡ ከየት ያምጣው? እንደተራበ በባዶ ሆዱ  ወደ ቤቱ አመራ፡፡
ውድ ልጆች፡- ከዚህ ታሪክ የምንማረው ቁምነገር፤ የሌሎችን ንብረት ለመንጠቅ ስንሞክር የራሳችንንም ልናጣ እንደምንችል ነው፡፡ ሁሌም ያለፋንበትንና የኛ ያልሆነን ነገር አንመኝ፡፡



Read 1632 times