Saturday, 20 August 2022 12:53

“ኦነግ ሸኔ” ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ጠየቀ

Written by  መታሰቢያ ሳሣዬ
Rate this item
(2 votes)

 • ተኩስ አቁሙ የሚደረገው በድርቅ ለተጠቁ አካባቢዎች ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ ነው፡፡
    • ተኩስ አቁሙ ተቀባይነት ካላገኘ ሰብአዊ መተላለፊያ እንከፍታለን ብሏል፡፡
            
       እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እያለ  የሚጠራውና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው የሸኔ ታጣቂ ቡድን፤ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቀ፡፡ ቡድኑ የተኩስ አቁሙን የጠየቀው በኦሮሚያ ክልል በተጋረጠው አስከፊ የረሃብ አደጋ  ለሚያልቁ ወገኖቸች የሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ እንዲያስችል ነው ብሏል፡፡
አሶሴትድ ፕሬስ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት ሰራዊት መግለጫን ጠቅሶ እንደዘገበው “በአሁኑ ወቅት በክልሉ በርካታ አካባቢዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፋ ድርቅና ረሃብ ተጋልጠዋል፡፡
በዚህ አስከፊ ረሃብ ሳቢያም ብዙዎች እንደሞቱ ነው፤ እነዚህን ወገኖች ከረሃብ ከሞት ለመታግ እንዲቻልና የሰብአዊ እርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች ወደ እነዚህ አካባቢዎቹ ገብተው እርዳታ ማድረስ እንዲችሉ ጊዜያዊ  የተኩስ አቁም ስምምነትና ትብብር የማድረግ ሃሳቡን አቅርቧል፡፡ ቡድኑ በመግለጫው ያቀረበው የተኩስ ማቆም ሃሳብ ተቀባይነት ካላገኘ ወይም የኢትዮጵያ መንግስት በስምምነት ላይ ለመድረስ በሚያመነታ ጊዜ ሰብአዊ መተላፊያ እንደሚከፍትም አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ በተለይም በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ በርካታ እንስሳት ማለቃቸው የሚታወስ ሲሆን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ይህንን አስመልክክቶ ባወጣው ሪፖርት፣ በአገሪቱ የተከሰተው ድርቅ  በ40 ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ነው ብሎታል

Read 11949 times