Print this page
Saturday, 27 August 2022 10:56

የህውሓት ነዳጅ መዝረፍ አለማቀፍ ውግዘትን አስከትሎበታል

Written by 
Rate this item
(2 votes)

      - የዘረፈውን ነዳጅ በአስቸኳይ እንዲመልስ ተጠይቋል
        -“ለዓለም ምግብ ድርጅት ያበደርኩትን ነው መልሼ የወሰድኩት”

      የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለእርዳታ ማጓጓዣ  ያጠራቀመውን 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ ህውሓት መዝረፉ ከዓለማቀፍ ተቋማትና ተቆርቋሪዎች ውግዘትን አስከትሎበታል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ቃል አቀባይ  ስቴፋን ዱጃሪክ ከትናንት በስቲ ማለዳ ከጀኔቫ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ማለዳ ህውኃት በመቀሌ ከሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን 12 ታንከሮችና 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ መዝረፉን ማስታወቃቸውን ተከትሎ፣ የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትና የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማትና፣ የሰብአዊ መብት  ተቆርቋሪዎች ድርጊቱን ክፉኛ አውግዘዋል። ቃል አቀባዩ በሰጡት መግለጫ፣ ህውሐት የዘረፈው 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ በክልሉ ለእርዳታ ማሰራጨት ተግባር ማሳለጫ፣ እንዲሁም ለአርሶ አደሮች ማዳበሪያና የተለያዩ ግብአቶች ማሰራጫ ሊውል የነበረ መሆኑን ጠቁመዋል። ነዳጁ መሰረቁ የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ተግባር በእጅጉ የሚያደናቅፍ በመሆኑ ህውሐት የዘረፈውን ነዳጅ አንድም ሳያስቀር በአስቸኳይ እንዲመለስ ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው አሳስበዋል።
ህወሃት በሰጠው ምላሽ፤ ለዓለም ምግብ ድርጅት ከወራት በፊት ያበደርኩትን ነዳጅ ወሰድኩ እንጂ አልዘረፍኩም ሲል አስተባብሏል።ህውሐት ነዳጁን ከመዝረፉም ባሻገር በመጋዘኑ የነበሩ አለማቀፍ የእርዳታ ሰራተኞችንም ማሰሩን መረጃዎች አመልክተዋል።በአሁኑ ወቅት በትግራይ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የእለት ደራሽ እርዳታ ጠባቂ  መሆናቸው ይታወቃል።



Read 11720 times
Administrator

Latest from Administrator