Saturday, 01 October 2022 12:04

የወገብ ህመምን፤ የቁመት መቀነስን... የትከሻ መጉበጥን....

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

የወገብ ህመምን፤የቁመት መቀነስን እና ወይንም የትከሻ መጉበጥን ቀለል አድርጎ መመልከት አይገባም፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ እድሜአቸው ከ50 አመት በላይ ከሆኑ ከሶስት ሴቶች አንዳቸው እንዲሁም ከአምስት ወንዶች አንዳቸው የአጥንት መሳሳት ይገጥማቸዋል፡፡
እንደውጭው አቆጣጠር October 20/2022 የዛሬ ሀያ ቀን አለም አቀፉ የአጥንት መሳሳት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ነጥቦች ይወሳል። በዚህ አለምአቀፍ ጉዳይ በሚሆነው የአ ጥንት መሳሳት ቀን ትኩረት የሚደረግባቸው ነጥቦች፤ ስለጥን ቃቄው ንቃተ ህሊናን ማጎል በት፤ይህን ለማድረግ ለመላው የአለም ህዝብ መረጃ ማድረስ፤ችግሩ ምን ያህል ሰፊ እና ጎጂ መሆኑ ላይ ትኩረት ማድረግ፤በችግሩ ዙሪያ ያለውን ያልተስተካከለ አረዳድ ማስ ተካከል፤ መደረግ ወደሚገባው ነገር ሁሉም እንዲገባ እና እርምጃ እንዲወስድ ለማድረግ ነው፡፡
የአጥንት መሳሳት የተለመደ የጤና መጉዋደል እና ያጋጠማቸው ሰዎችም በቀላሉ በመው ደቅና በተለያዩ ምክንያቶች የሚሰበሩ ሲሆን በዚህም በአለም አቀፍ ደረጃ ከሶስት ሴቶች አን ድዋ ወይንም ከአምስት ወንዶች አንዱ እድሜአቸወው 50 አመትና ከዚያ በላይ ሲሆን በወደ ፊት ሕይወታቸው ሊያጋጥማቸው የሚችል ህመም ነው፡፡ ይህም እንደውጭው አቆጣጠር በ1990 ከነበረበት ወደፊት እንደውጭው አቆጣጠር በ2050 በወንዶች እስከ 310% እና በሴቶች ደግሞ በ240% ይጨምራል ተብሎ ይገመታል፡፡ በአለማችን በየአመቱ ከ8.9 ሚሊዮን ሰዎች በላይ አጥንታቸው የመሰባበር እድል የሚገጥማቸው ሲሆን በአለም ላይ በየ ሶስት ሴኮንዶች በአጥንት መሳሳት ምክንያት አንድ አጥንት ይሰበራል፡፡
በአለም አቀፍ የጤና ድርጅት አገላለጽ መሰረት በግምት 500 ሚሊዮን ወንዶችና ሴቶች በአለም አቀፍ ደረጃ በአጥንት መሳሳት ምክንያት ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡ በሆስፒታል አልጋ የሚይዙ ሴቶች ሁኔታ እንደሚያሳየው በጡት ካንሰር፤ በስኩዋር ሕመም፤ በልብ ሕመም፤እና ሌሎች ሕመሞች አልጋ ይዘው ከሚቆዩት በላይ በአጥንት መሳሳት ሕመም አልጋ ይዘው ቀናትን የሚያስቆጥሩት ይበልጣሉ፡፡ በወንዶች ደግሞ በፕሮስቴት ካንሰር እና ሌሎች ምክን ያቶች አልጋ ይዘው ከሚይዙት ይልቅ በአጥንት መሳሳት ምክንያት በሆስፒታል አልጋ ይዘው የሚቆዩት ይበልጣሉ፡፡
ከአሁን ቀደም በአጥንት መሳሳት ዙሪያ ያስነበብናችሁን ማስታወስ እንወዳለን፡፡ ምንጫችን ዶ/ር ጣሰው ኃይሌ የማህጸንና ጽንስ ህክምና እስፔሻሊስት ነበሩ፡፡
(Osteoporesis) ኦስቲዎፖረሲስ ወይም የአጥንት መሳሳት ማለት የአጥንት መጠን ማነስና እንዲሁም አጥንትን የሚደግፉ አካሎች…የእነሱ ቅንጅት መሰባበር የሚያመጣው ችግር ነው የአጥንት መሳሳት የሚባለው፡፡ አጥንታችን በሚኒራል የተገነባ ነው እና አጥንት በሚሰበርት ጊዜ ቢታይ አጥንት የእራሱ ውፍረት አለው። እና ያ ውፍረት (ቦን ማስ) ወይም ደግሞ የአጥንቱና የአካሉ መጠን ነው ክብደት የሚባለው፡፡ የእሱ መጠን የሚለካው በሚይዛቸው ካልሺየም በመሳሰሉ የተለያዩ ሚኒራሎች ነው፡፡ እነዚህ ሚኒራሎች ይህንን ነገር መስራት ካቆሙ አጥንቱ በቀላሉ እንዲሰበር ወይም ችግር እንዳይችል ያደርገዋል፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ ይሳሳል እንደገና ደግሞ ለመሰበር በጣም ከፍተኛ እድል ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ ስለአጥንት መሳሳት ስናወራ ሶስት ቦታ ያሉ የሰውነታችን ክፍሎች ናቸው ለዚህ ችግር የሚጋለጡት ብለው ነበር ዶ/ር ጣሰው፡፡
አንደኛው የጀርባ አጥንት አከርካሪ የሚባለው ነው ፡፡
ሁለተኛው ደግሞ የቅልጥም አጥንት ነው። ይሄ የጭን አጥንትን የሚጨምር ነው። ምክንያቱም የሚገናኙበት ቦታ አንገት አለው። እንዲያውም የቅልጥም አንገት ይባላል፡፡
ሶስተኛው የአጥንት መሳሳት የሚደርስበት ደግሞ የእጅ መዳፍና እጅ  የሚገናኝበት ቦታ ነው፡፡ ይህም ሰአት ጌጣጌጥ የሚታሰርበት ቦታ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ሶስት ቦታዎች ናቸው ከጠቅላላው የሰውነት ክፍሎች የበለጠ ለአጥንት መሳሳት የሚጋለጡት፡፡
የአጥንት መሳሳት ችግር እድሜ ከመግፋቱ አስቀድሞም ይከሰታል፡፡ ለዚህም በምክንያትነት የሚጠቀሱት፡-
አንደኛው በቤተሰብ የሚተላለፍ በዘር አፈጣጠሩ ራሱ አጥንቱ ሲሰራ ትክክል እንዳይሰራ የሚያደርገው ነው፡፡
ሲጋራ ማጨስ አልኮል በብዛት መጠጣት እንቅስቃሴ አለማድረግም ለዚህ ህመም ያጋልጣል፡፡
ሌላው ቀጭን ሰውነት መኖር ነው፡፡ቀጭን ሰውነት ማለት በክብደት ደረጃ ማለት ነው ፡፡የዚህ ምክንያቱ ደግሞ አጥንታችን ክብደታችንን የሚሸከመው ዋና ክፍል በመሆኑ ያ ክብደታችን አጥንታችን ሁል ጊዜ እንዲጠነክር ይረዳዋል፡፡ ምክንያቱም ቆመን በተራመድንበት ጊዜ ሁሉ ስራ እያሰራ ነው፡፡ ክብደቱ አጥንታችንን በተዘዋዋሪ መንገድ ስፖርት እያሰራነው ነው ማለት ነው። ስለሆነም ወፍራም ሰዎች አጥንታቸውን ብዙ ስፖርት ሲያሰሩ ቀጭን ሰዎች ደግሞ አጥንታቸው የሚሸከመው መጠነኛ ጉልበት ስለሆነ በሚፈለገው ደረጃ አያሰሩትም፡፡ አጥንት በደንብ ካልሰራ ደግሞ በተፈጥሮ ብዙ ሚኒራል በውስጡ እንዲከማች አያደርግም ፡፡ ሌላው ምግብ ካልሽየም ያነሰው ከሆነ። እድሜ ከሀምሳ አመት በታች ቢሆንም ለአጥንት መሳሳት ምክንያት ይሆናል፡፡ ከጸሐይ ብርሃን ማነስ የሚመጡ ችግሮችም አሉ፡፡ማንኛውም ሰው በቀን ለተወሰነ ሰአት (ከ20-30 ደቂቃ) ሰውነቱን ለጸሐይ ብርሃን ማጋለጥ አለበት፡፡ ይህ በተለይም በህጻንነት እድሜ ሊታለፍ የማይገባው ቁምነገር ነው፡፡ጥናቶች እንደሚያመለክተቱት መጀመሪያ ላይ በእድገት ላይ ያለው ሰው የሚኖረው የአጥንት መጠን ነው እስከ እድሜ ልክ ድረስ የሚያገለግለው፡፡ስለዚህ ታዳጊ ትውልድን ፀሐይ ማሞቅ…አመጋገብን ማስተካል የሁዋላ ሁዋላ የሚደርሰውን የአጥንት መሳሳት ችግር ይቀንሳል፡፡ሌላው ደግሞ ሴቶች በተለይም የወር አበባቸው ከእድሜያቸው ቀደም ብሎ ከአርባ አምስት አመት በፊት ካቋረጠ ለአጥንት መሳሳት ችግር ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ ለአጥንት መሳሳት መንስኤ ከሚሆኑት መካከል ለተለያዩ ህመሞች የሚወሰዱ መድሃኒቶችም ይገኙበታል፡፡ ለምሳሌ…ለአስም በሽታ… ለተለያዩ አለርጂ  በሽታ የሚሰጡ እና እነዚያን መድሀኒቶች ለረጅም ጊዜ መውሰድ  አጥንትን ሊያሳሳ ይችላል፡፡ የሚጥል በሽታ መድሀኒቶች… ደም እንዳይረጋ መከላከያ መድሀኒቶች የመሳሰሉትን መውሰድ አጥንትን ያሳሳል ፡፡ሌሎች ደግሞ ለምሳሌ የደም ካንሰር …የመሳሰሉት የደም ችግሮች ከንጥረ ነገር ጋር የተያያዙ ስለሆነ የአጥንት መሳሳት ችግር ያመጣሉ፡፡ እነዚህና ሌሎችም ችግሮች ዋና ስራቸው ሰውነት ለአጥንት ግንባታ የሚያስፈልገውን ንጥረ ነገር በሰአቱ እንዳያገኝ መከልከል ነው፡፡ መድሀኒቶቹ ከእነዚህ ንጥረ ነገሮች ጋር ይቀራረባሉ፡፡ የጨጉዋራ የአንጀት የመሳሰሉት ችግሮች ምግቡን ብንመገበውም እንኩዋን እነዚያ ንጥረ ነገሮች ተስተካክለው ወደ ደም እንዳይገቡ ይከላከላቸዋል ፡፡
ከ55% በላይ የሚሆኑ ሕመምተኞች የወገብ አጥንት ሕመም የሚገጥማቸው ሲሆን ይህም በወደፊት ህይወታቸው የአጥንት መሳሳት ሕመም የሚገጥማቸው መሆኑን ይጠቁማል፡፡
አንድ ቀደም ሲል የተከሰተ የአጥንት ስብራት 86% ያህል በቀጣይ ለሚከሰት የአጥንት መሳሳት ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡
በአጥንት መሳሳት ምክንያት የሚደርስ በቀላሉ የመሰበር አደጋ ምናልባትም በቀጣዮቹ ሁለት አመታት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ሊከሰት በድጋሚ እንደሚችል መገመት ይገባል፡፡
የአጥንት መሰበር አደጋው የሚደርስባቸው ሰዎች ምናልባትም ወደ 80% ያህሉ የደረሰባቸው ስብራት ከአጥንት መሳሳት ጋር ይያያዛል ከሚል ጥርጣሬ ምንም ምርመራ እንደማይደርጉ ይገመታል፡፡
1/3ኛ ያህል የወገብ አጥንት ስብራት ወይንም የከፋ ህመም የሚገጥማቸው ሰዎች ወደክሊኒክ በመሄድ ችግራቸውን ይታዩ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡
የአጥንት መሳሳት ከመድረሱ አስቀድሞ ሁሉም ሰው መውሰድ የሚገባው የጥንቃቄ እርምጃ አለ፡፡
ችግሩ እንደሚደርስ ከገመቱ እና አንዳንድ ምልክቶችን ካዩ አስቀድሞውኑ ወደ አጥንት ሕክምና በመሄድ መማከር ይገባል፡፡
የአጥንት መሳሳት ሊከሰት የሚችለው በእድሜ ከመግፋት፤ በቁመት ከማጠር፤ ከሰውነት ክብደት፤ ከቤተሰብ ታሪክ ጋር በተገናኘ እና አንዳንድ ህመሞች ጋር በተያያዘ በመሳሰሉት ሊከሰት እንደሚችል መገመት ይጠቅማል፡፡
በቀላሉ ከቆሙበት ወድቀው በማንኛውም የአጥንት ክፍል ላይ ስብራት ቢያጋጥም የአጥንት መሳሳት ምክንያት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ወደሕክምና በመሄድ የከፋ ነገር ከመድረሱ በፊት ሁኔታውን ማወቅ ይገባል፡፡
ባጠቃላይም የወገብ ህመምን፤የቁመት መቀነስን እና ወይንም የትከሻ መጉበጥን ቀለል አድርጎ መመልት አይገባም፡፡ ይህ የአጥንት መሳሳጥ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡  
ምንጭ www.osteoporosis.foundation

Read 10763 times