Saturday, 08 October 2022 09:12

የሴቶች ሞት ሁሉ የእናቶች ሞት አይባልም፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

የሴቶች ሞት ሁሉ የእናቶች ሞት አይባልም፡፡

      ከእርግዝና ወይንም ወሊድ ጋር ባልተገናኘ የሚከሰተው ህመም ወይንም ሞት የእናትነት ህመም ወይንም ሞት አይባልም፡፡
የእናቶች ሕመም ወይንም ሞት የሚባለው ህይወትን ለመስጠት ስትል ህይወትዋን የምታጣውን እናት የሚመለከት ነው፡፡
አቶ ንጉሴ ማዘንጊያ የአዋላጅ ነርሶች ማህበር ስራ አስኪያጅ፡፡
እንደውጭው አቆጣጠር ሴፕቴምበር 5/2022 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ ነሐሴ 30/2014 አንድ መመሪያ ወይንም Guide Line ይፋ ተደርጎአል፡፡ በአዲስ አበባ ለሕክምና ባለሙያ ዎች የስራ መመሪያ ተደርጎ ይፋ የሆነው ይህ መመሪያ ወይንም ጋይድ ላይን ከወሊድ በሁ ዋላ በሚገጥም የደም መፍሰስ ምክንያት የሚደርስን ህልፈት ለመከላከል እንዲቻል የጽንስና ማህጸን ህክምና ባለሙያዎች በመላ አገሪቱ በተመሳሳይ ሁኔታ ጥንቃቄ የተመላውን ተገቢ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል ነው፡፡
መመሪያው ወይንም Guide Line ይፋ በተደረገበት ወቅት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፤ ከአዋላጅ ነርሶች ማህበር እና የጽንስና ማህጸን ሕክምና ባለሙያዎች እና ሌሎችም የሚመ ለከታቸው በስብሰባው ላይ ተገኝተው ነበር፡፡ በስብሰባው ላይ ከተገኙት መካከልም የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሕክምና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱልፈታህ አብዱልቃ ድር የመጀመ ሪያው ተጋባዥ እንግዳ ነበሩ፡፡ እሳቸውም የመመሪያውን Guide Line ዝግጅት አስፈላጊነት እንደሚከተለው ነበር ያብራሩት፡፡
‹‹…ይህንን ከወሊድ በሀዋላ የሚከሰትን የደም መፍሰስ እንዳይኖር ለማድረግ የሚረዳውን ብሔራዊ መመሪያ ወይንም Guide Line ማለቅና ስርጭትን በሚመ ለከት በመካሄድ ላይ ባለው ስብሰባ በመገኘቴ እና እናንተም ስለመጣችሁ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ ይሄንን መመሪያ ወይም Guide Line እጅግ በጣም አስፈላጊ የሚያደርገው ለእናቶች ሞት አስተዋጽኦ በማድ ረጉ ረገድ ዋነኛው ከሚባሉት ውስጥ ከወሊድ በሁዋላ የሚያጋጥመው የደም መፍሰስ ስለ ሆነ ነው፡፡ምንም እንኩዋን ብዙ ቢሰራም በሀገርም ደረጃ አመርቂ ውጤት ያላመጣንበት በመሆኑ መመሪያ ወይንም Guide Line መስራቱ ተገቢ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡ ስለዚህም የኢት ዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህር ከጤናጥበቃ ሚኒስቴር እና ከአዋላጅ ነርሶች ማህ በር ጋር በመተባበር ፊጎ ከተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በተገኘው ድጋፍ እነሆ መመሪያው ተሰርቶ ተጠናቆአል፡፡ ይህ Guide Line በቀጣዩ በሐገር አቀፍ ደረጃ በየህክ ምና ተቋማቱ ተሰራ ጭቶ መላው የህክምና አገልግሎት ለመላው ታካሚ እናቶች በተመሳሳይ እና ተገቢ በሆነ ደረጃ እንዲሰጥ ለማስቻል ስልጠናው እና ስርጭቱ ተከታይ ተግባር ይሆ ናል። ስለዚህ ዶክመንቱ ተባዝቶም ሆነ በኢንተርኔት አማካኝነት በሁሉም ሆስፒታች እና ጤና ተቋማት ዘንድ እንዲደርስ የበኩሉን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ይፈል ጋል፡፡ ስለ ሆነም የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር አሁንም ስልጠናዎችን ለማካሄድና ዶክመንቱን ለማዳረስ ድጋፍ ስለሚያስፈልገው በዚሁ ጥሪ አደርጋለሁ ብለዋል የኢሶግ ቦርድ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱል ፈታህ አብዱልቃድር…››
ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በተቻለ መጠን ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲሻሻል ትልቅ ስራ የተሰራው የእናቶችን እና ህጻናትን ሞት መቀነስ ነበር፡፡ በእርግዝናና ልጅን በመውለድ ወቅት በሚከሰቱ አንዳንድ እክሎች ምክንያት የሚያልፈው የእናቶች ሞትም ሆነ ህመም ሊከላከሉት ሲገባ ነገር ግን ያ ባለመደረጉ ምክንያት ሲሆን ችግሩ ግን ከአቅም በላይ ሆኖ ተቀባይነትን አግኝቶ የሚታለፍ አለመሆኑን ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡ በዚህም ምክንያት ከወሊድ በሁዋላ በሚከሰተው የደም መፍሰስ ምክንያት እናቶች እንዳይሞት ለማስቻል መመሪያውን Guide- Line ማው ጣት ግድ ሆኖአል፡፡
Postpartum haemorrhage ወይም ከወሊድ በሁዋላ ደም መፍሰስ ሲባል በምን ይገለጻል ስንል ጥያቁ ለአዋላጅ ነርሶች ማህበር ስራ አስኪያጅ ለአቶ ፈቃዱ ማንያዘዋል አቅርበን የሚከተለውን መልስ ሰጥተዋል፡፡
‹‹…እርግዝና በሶስት ይከፈላል፡፡ አንቲ ፓርተም ወይም ቅድመ ወሊድ፤ኢንትራ ፓርተም  ወይም ምጥ ከጀመራት ጊዜ ጀምሮ እስክትወልድ ድረስ፤ ከወለደች በሁዋላ በአራስነት ጊዜዋ ደግም ፖስት ፓርተም ይባላል፡፡ ፖስት ፓርተም ሄሞሬጅ የሚባለው ከወለደች በሁዋላ የሚከሰ ተው የደም መፍሰስ ሲሆን የደም መፍሰስ ግን ከመውለድዋም በፊት ይከሰታል፡፡ ዞሮ ዞሮ በማን ኛውም ጊዜ የሚከሰተው የደም መፍሰስ እናትየውን ሊገድል ይችላል፡፡ ልዩነቱ ከመውለድዋ በፊት የሚፈሰው ደም እና በዚያ ምክንያት የምትሞተው እናት ብዛት  ትንሽ በመሆኑ ከወለደች በሁዋላ እንደሚከ ሰተው የደም መፍሰስ እና የእናቶች ሞት ተጋኖ ስለማይወራ ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2017 /በአለም አቀፍ ደረጃ 295.000/እናቶች ከእርግዝና ወይንም ከወሊድ ጋር ተያይዞ በሚከሰት የጤና ችግር መሞታቸው ይፋ ሆኖአል። 2/3ኛው ወይንም 66% የሚሆኑት ሞቶች የተመዘገቡት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ነው፡፡ ይህ ግን ሊከላሉት ሲገባ የተከሰቱ ሞቶች ተብሎ ተመዝግቦአል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ 73% የሚሆኑት የእናቶች ሞቶች የሚከሰቱት ቀጥተኛ ከሆኑ ተያያዥ ነገሮች ሲሆን ወደ 27% የሚሆነው የእናቶች ሞት የሚከሰተው ግን ከወሊድ በሁዋላ ከሚከሰት የደም መፍሰስ ጋር በተያያዘ ነው፡፡  
ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ለእናቶች ሞት ምክንያት ከሚባሉት ውስጥ 24 % የሚሆነው ድርሻ ከወሊድ በሁዋላ የሚከሰት የደም መፍሰስ ነው፡፡ ከወሊድ በሁዋላ የሚከ ሰተው የደም መፍሰስ Postpartum haemorrhage በገዳይነቱ ቀዳሚ ከሚባሉት ውስጥ ነው፡፡
ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ብርቱ ጥረት ተደርጎአል፡፡ በመሆኑም፡-
በ1990 ከተመዘገበው የእናቶች ሞት ወደ 69% በሚሆን ደረጃ እንዲቀንስም አስችሎአል፡፡
በውጭው አቆጣጠር በ2017 በኢትዮጵያ ከ100.000 በህይወት ከሚወለዱ 401/ያህል የእናቶች ሞት ተመዝግቦአል፡፡
እኤአ በ2010 በተደረገው ቅኝት በኢትዮጵያ ወደ 82% የነበረው ሞት ሊከላከሉት ሲገባ የተከሰተ መሆኑን አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በኢትዮጵያ ከ41% በላይ የሚሆነው የእናቶች ሞት የሚከሰተው በሚከ ሰተው የደም መፍሰስ በመሆኑ ቀዳሚው የእናቶች ሞት ምክንያት ያሰኘዋል፡፡
በኢትዮጵያ ወደ 76% የሚሆነው ሞት የሚከሰተው ከወሊድ በሁዋላ በሚፈጠረው የደም መፍሰስ ምክንያት ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የእናቶችንና የጨቅላ ህጻናትን ሞት ለማስቀረት በሚያስችል መልኩ ትኩረት ሰጥቶ በጤና እቅዱ ውስጥ ያስገባው በመሆኑ እ.ኤ.አ በ2025 ከ100.000 በህይወት ከሚወለዲ ወደ 279/ ዝቅ ለማድረግ ያስችላል የሚል እቅድ ተነድፎአል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ሶስተኛው እና ቀጣይነት ባለው የልማት ግብ ውስጥ እ.ኤ.አ እስከ 2030 ድረስ የእናቶች ሞትን ከ100.000 በህይወት ከሚወለዱ ከ70 በታች ለማድረስ ነው፡፡  
ከላይ የተዘረዘሩትን ችግሮች ለማስወገድ የሚያስችል አሰራር በመላው ሀገሪቱ በተመሳሳይ ሁኔታ ለማዳረስ እንዲቻል በብሔራዊ ደረጃ ከወሊድ በሁዋላ የሚከሰተው የደም መፍሰስ Postpartum haemorrhage መመሪያ Guide- Line ተዘጋጅቶአል፡፡
ይህ መመሪያ ወይንም Guide- Line ፡-
በየትኛው አካባቢ ያሉ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ የደም መፍሰስ ሊያጋጥማቸው ይችላል የሚለውን ለመለየት፤
በየትኛው ተቋም ይበልጥ ችግር እንደሚደርስ አውቆ አስቀድሞ ለመከላከል፤
ከወሊድ በሁዋላ የሚከሰትን የድም መፍሰስ አስቀድሞ አውቆ አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ፤
የደም መፍሰስ ምክንያቱን አውቆ እንዳይከሰት ለማድረግ እና በተቋም ደረጃ አሰራሩን ለማጠናከር፤
ከማህጸንና ጽንስ፤ ከቀዶ ሕክምና፤ደም በመተካት አገልግሎት ወቅት ግልጽ የሆነ እና ሰአቱን የጠበቀ ግንኙነት በማድረግ ችግሩን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል እና የመሳሰሉትን ስራዎች ለመስራት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያግዝ መመሪያ ወይንም Guide- Line ነው፡፡


Read 15095 times