Saturday, 22 October 2022 14:06

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ለኑሮ ውድነት መንስኤ ናቸው ባላቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የወቅቱ የማህበረሰቡ አንገብጋቢ ችግሮች ናቸው ባቸውና የኑሮ ውድነቱን አንረውታል ባላቸው ነጥቦች ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ። ረቡዕ ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም ለግማሽ ቀን በተካሄደው ውይይት በተለይም የግብርና ውጤቶች ላይ የቫት ታክስ ማሻሻያ ዋና የትኩረት ማዕከል አድርጎ ተወያይቷል።
በዚህም መሰረት ለውይይት የቀረቡት ነጥቦች የግብርና ምርቶች በተለይም ለደሀው ማህበረሰብ የዕለት ከዕለት ጉርሱ በሆኑ ምርቶች ላይ ቫት ማስከፈሉ ተገቢነት አለው ወይ? በአንፃሩ ቫት የተነሳላቸው እንቁልልና ወተት በእርግጥ አሁን ላይ የአብዛኛው ህብረተሰብ ክፍል ፍላጎት ናቸው ወይ? ህጉ ገንዘብ ያለውን ብቻስ ተጠቃሚ አያደርገውም ወይ? የቫት ትርጉሙ እሴት መጨመር ላይ ያተኮረ እስከሆነ ድረስ ከገበሬው በቀጥታ መጥተው ምንም እሴት ሳይጨመርባቸው የሚከፋፈሉ የግብርና ምርቶች ላይ የቫት ታክስ መጨመሩ አግባብነት አለው ወይስ የለውም? ቫት ይጨመር ቢባል እንኳ ተመዝጋቢ ያልሆነ ያለቫት እየሸጠ ተመዝግቦ ግብር የሚከፍለውና የስራ እድል የሚፈጥረው ብቻ ቫት እንዲከፍል መገደዱ በሸማቹና በነጋዴው መካከል ኢ-ፍትሃዊ የሆነ ስርዓትን አይፈጥርም ወይ ሚሉና በአጠቃላይ በኑሮ ውድነቱ ላይ ያተኮሩ የውይይት ሀሳቦች ተነስተዋል።
የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሃ እሸቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው በነዚህ ማህበረሰቡን ባጎበጡ ችግሮች ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ በጉባኤው የሚነሱ ግብአቶችንና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማቀናጀት ወደ ቀጣይ እርምጃ እንደሚሄዱ አስታውቀዋል።Read 747 times