Print this page
Saturday, 29 October 2022 11:14

እንደ አዳል መጫኛ ሲረዝም ለሊቱ ይህን ጊዜ ነበር ከተፍ ማለቱ (የአፋር ተረት)

Written by 
Rate this item
(3 votes)

መንገዳችን ረዥም አገራችን ሰፊ ናት! መንግስታችን የዚያን ያህል ሰፊ እንዲሆን ምኞታችን ነው! ይሄ የሆነ ዕለት ህዝብ ያሸንፋል!
ደራሲ ከበደ ሚካኤል፡-
“አለ አንዳንድ ነገር
በዚህ ሙሉ በዚያ ከመሆን የማይቀር”
ይሉናል። ሀሳባቸው ዛሬም ከእኛ ጋር ነው። የምንጽፈው የምንኖረውን ነው። የምንኖረውም የምንጽፈውን ነው። እንግዲህ ለመንግስት በብርቱ ለማስታወስ የምንወደው፡-
የሚያውጀውን አዋጅ ይኑር!
የሚያወጣውን መመሪያ ይተግብር!
የሚያስበውን ዕቅድ፣ የሚወዳጀውን አገርና የሚፈራረመውን ፊርማ አይደብቀን። ግልጽነት  (Transparency) መርሁ ይሁን!
ይህ ከሆነ እኛም እንደ ህዝብ እናግዘዋለን!
“የመቻል ሁሉ መጨረሻ ማስቻል ነው” የምንለው ያኔ ነው!
***
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ለምድር ለሠማይ የከበደ የጦር ጀነራል ነበር። አካባቢውን በሙሉ በጦር አስገብሯል። ሰው ነውና መሸበት። ስለዚህም በዙሪያው ያሉት ትናንሽ ጦረኛ ንጉሶች፣ ይህንን ምሽት መሠረት አድርገው ሊወሩት ተነሱ። ጀግናው ግን ሁነኛ ልጆች ወልዶ ስለነበር ሦስቱንም ልጆቹን ጠርቶ ሦስት ምርጫ ሰጣቸው፡-
1ኛ. ልጆቼ ሆይ፤ ግዛቴን ትወርሱ ዘንድ ሃብት አላችሁ
2ኛ. ጦር አላችሁ
3ኛ. ጥበብ አላችሁ
የየምርጫችሁን ትነግሩኝ ዘንድ የሶስት ቀን እድሜ ሰጥቻችኋለሁ፤ በየፊናችሁ ሄዳችሁ አስባችሁ ተመለሱ። ከሶስት ቀን በኋላ ተመልሰው የየግል መልሳቸውን ይዘው መጡ። የመጨረሻ ትልቁ ልጅ የመጀመሪያውን መረጠ። ሁለተኛው ልጅ ጦር መረጠ። የመጨረሻ ትንሹ ልጅ ጥበብ መረጠ። አባትየው የሶስቱንም መልሶች ከሰማ በኋላ የራሱን ውሳኔ ነገራቸው።
ይኸውም እኔ እናንተን ብሆን ሶስቱንም አልመርጥም ነበር አላቸው። ሶስቱም ልጆች ከፋቸው። “ይኸን የምትለን ከሆነ አስቀድመህ ለምን ምርጫውን ሰጠኸን”
አባትየውም መለሰ፡-” ልጆቼ ሆይ፤ ከሰጠኋችሁ ውጪ እንድታስቡ ብዬ ነው።”
እስከ ዛሬ የሄድነው መንገድ በሙሉ አገር እንሰራለን ብለን ነው። ማንኛውም አገር- አፍራሽ (Destructive force) በአገርኛው ቋንቋ “አይመቸንም” ባዮች ነን። አገር የህዝብ እንጂ የመሪም ሆነ የአስተዳዳሪ (ገዢ) አይደለችም! የመጨረሻው ትንሽ ሰው የአገሩ ባለቤት ነውና!
ዛሬ ተመልሰን ይኸው ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሶስት ዓመተ ምህረት ደርሰናል። ህይወት የትግል ሳይሆን የድርድር የሆነበት ዘመን! ሃገርም ትውልድም መሪም ሆነ ፈጣሪው ሁሉም ነገ አለው።

Read 12134 times
Administrator

Latest from Administrator