• ተጠርጣሪዋ በፖሊስ እየታደነች ነው ተብሏል
ቦታው እዚህ አዲስ አበባ፣ አስኮ አዲሱ ሰፈር አካባቢ ነው፡፡ ትናንት ከቀኑ 5 ሰዓት ገደማ ሲሆን፤ አንዲት የቤት
ሠራተኛ ቀጣሪዋን በአሰቃቂ ሁኔታ፣ በቢላና በዘነዘና ገድላ መሰወሯን፣ ቤተሰቦቿ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
ተጠርጣሪዋ በፖሊስ እየታደነች ነው ተብሏል፡፡
የቤት ሰራተኛዋ በሟች ወ/ሮ ፋሲካ ተሾመ ቤት ውስጥ ተቀጥራ ለአንድ ዓመት ከ6 ወር መሥራቷን የጠቆሙት ቤተሰቦቿ፤ እስካሁን ቀጣሪዋን የገደለችበት ምክንያት አለመታወቁን ነው የገለጹት፡፡የ60 ዓመቷ ሟች ወ/ሮ ፋሲካ፣ የሁለት ልጆች እናት ሲሆኑ፤ በትናንትናው ዕለት ቤታቸው ውስጥ ብቻቸውን ሳሉ ነው በቤት ሰራተኛቸው በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ተብሏል፡፡
ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ከፈጸመች በኋላ እቃዎቿን ሸክፋና በሟች ላይ በር ዘግታ ከአካባቢው መሰወሯን ነ ው ቤተሰቦች የገለጹት፡፡
በምስሉ ላይ የምትታየውን ተጠርጣሪ ወንጀለኛ በየትም ቦታ ያየ ፣ ለፖሊስ በመጠቆም በቁጥጥር ሥር እንድትውል ይተባበር ዘንድ የሟች ቤተሰቦች ተማጽነዋል፡፡
Published in
ዜና