Wednesday, 02 November 2022 19:46

የፌደራል መንግስት እና ህወሓት ግጭት ለማቆም መስማማታቸው ተገለጸ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)


•  የህወሓት ተዋጊዎችን ትጥቅ ለማስፈታትም ተስማምተዋል

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህወሓት ግጭት ለማቆምና የህወሓት ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ፡፡

 ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ ለ10 ቀናት  በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ወደ ስምምነት ማምራቱን የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የገለጹት፤ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

በሁለቱ መካከል ከተደረሱ ስምምነቶች አንዱ የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት ማክበርና ሕገ መንግስቱን መጠበቅ በመሠረታዊነት የተጠቀሰ ሲሆን በኢትዮጵያ አንድ ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት ብቻ እንደሚኖርም ተስማምተዋል።

በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አመቻችነት ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ለሁለት ዓመታት ውጊያ ውስጥ የቆዩት  የፌደራል መንግስት እና የህወሓት ተደራዳሪዎች በይፋ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የተገናኙበት ነው።

 በሰላም ንግግሩ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የቀድሞዋ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ፑምዚ ለምላምቦ በደጋፊነት  ተካፍለውበታል።

ለአስር ቀናት በተካሔደው የሰላም ንግግር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ)፣ የአሜሪካ መንግስት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ተወካዮች  በታዛቢነት ተሳትፈውበታል።

Read 5470 times