Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 27 October 2012 09:33

የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ምርጫ ለመዘገብ ወደ አሜሪካ ተጓዘች

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በተለያዩ የግል ጋዜጦች ላይ ከሪፖርተርነት እስከ ዋና አዘጋጅነት በመሥራት የምትታወቀው የአዲስ አድማስ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ፤ ከሳምንት በኋላ በአሜሪካ የሚካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመዘገብ ተመርጣ ትላንት ወደ አሜሪካ ተጓዘች፡፡
የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የኤድዋርድ ሙር የ2012 የጋዜጠኞች ፕሮግራም ተመራጭ የሆነችው ጋዜጠኛዋ፤ የአሜሪካን ምርጫ እና ሂደት ለመዘገብ ከተለያዩ አገራት ተጋብዘው ከሚመጡ ጋዜጠኞች ጋር የልምድ ልውውጥ የምታደርግ ሲሆን ታላላቅ የአሜሪካ የሚዲያ ተቋማትንና በጋዜጠኞች መጎብኘት አለባቸው የተባሉ ቦታዎችን እንደምትጐበኝ ታውቋል፡፡

ኤምባሲው ሌሎች እጩዎችንም ለስቴት ዲፓርትመንት ጠቁሞ የነበረ ሲሆን እጩዎችን ያወዳደረው ስቴት ዲፓርትመንቱ፤ ጋዜጠኛ ጽዮንን በመምረጥ በፕሮግራሙ ላይ እንድትሳተፍና አጓጊ የሆነውን የ2012 የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን እንድትዘግብ ወስኗል፡፡
ፕሮግራሙ ለአንድ ወር የሚቆይ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ “እንቢልታ” የተባለ የራሷን ጋዜጣ አቋቁማ በዋና አዘጋጅነት ትሠራ እንደነበር ይታወሳል፡፡

Read 2630 times Last modified on Saturday, 27 October 2012 11:12

Latest from