በሜትሮ PLC አስመጪነት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አገራችን የገባው ይኸው መሣሪያ፤ የሃይል መዋዠቅ ችግሮች በሚፈጠሩበት ወቅት ለመቋቋም የሚያስችለው መሣሪያ የተገጠመለት በመሆኑ በየጊዜው የሚከሰት የኃይል መዋዠቅ እንደማያሰጋው ተገልጿል፡፡ የ LG ኩባንያ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ዶኒር አቡበከር በበኩላቸው፤ ኩባንያው የተሻሉና ለህብረተሰቡ ጠቃሚ የሆኑ ዕቃዎችን በማምረት የሚታወቅ መሆኑን ጠቅሰው የአየር ማሞቂያና ማቀዝቀዣ መሣሪያዎች ተጨማሪ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉበትን መንገድ በማሰብና የወቅቱን የአየር ብክለት ከግምት ውስጥ በማስገባት አየርን ከማሞቅና ከማቀዝቀዝ ባለፈ የማጣራት አገልግሎት የሚሰጥ መሣሪያ ለገበያ ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡
LG ኩባንያ ላለፉት ስምንት ዓመታት በአንድ መቶ ሚሊዮን የአየር ማሞቂያና ማቀዝቀዣ ሽያጭ በአለም የአንደኝነት ደረጃ ይዞ መቆየቱ ይታወቃል፡፡