Saturday, 19 November 2022 20:06

“ባሎችና ሚስቶች” ቴአትር በብሔራዊ ቴአትር ለእይታ ሊቀርብ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በፊልሙ ዓለም አስደናቂ የሆነው የአሜሪካዊው የውዲ አለን ድርሰት የሆነው “ሀዝባንድስ ኤንደ ዋይቭስ” ፊልም በሳሙኤል ተስፋዬ “ባሎችና ሚስቶች” ወደሚል  አዛማጅ ትርጉም ተለውጦና ተዘጋጅቶ ለእይታ ሊበቃ ነው። ቴአትሩ የትዳርን ገመና አደባባይ እያወጣ በሽሙጥ እየሸነቆጠና እያዝናና የሚያስተምር ሲሆን በብሔራዊ ቴአትር በአይነቱ ልዩ በሆነ ተሽከርካሪ መድረክ ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ ለእይታ እንደሚበቃም ታውቋል፡፡ በዚህ ቴአትር ላይ ለረጅም ጊዜ  ከመድረክ ጠፍታ የነበረቸው ተዋናይት ሐረገወይን አሰፋ፣ ተስፉ ብርሃኔ፣ ቢንያም ወርቁ፣ እታፈራሁ መብራቱ፣ የምስራች ግርማ፣ አንዷለም ካሳሁንና ፀደይ ፋንታሁን፣ በትወናው ድንቅ ብቃታቸው እንደሚያሳዩ የተገለፀ ሲሆን እያንዳንዱ ትዕይንት የሚለዋወጠው ተሸከርካሪ ሆኖ በተሰራው መድረክ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ቴአትሩን ፕሮዲዩስ ያደረገችው እታፈራሁ መብራቱ ስትሆን ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰሩ ሰው መሆን ይሰማው (ሶሚክ) እንደሆነም ተገልጿል።


Read 780 times