Saturday, 19 November 2022 20:35

ያልተነበበው አንባቢ” መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

የዕውቁ ፖለቲከኛና የሰላማዊ ትግል አቀንቃኝ አንዱዓለም አራጌ አምስተኛ ስራ የሆነው “ያልተነበበው አንባቢ” መፅሐፍ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ጊዮን ሆቴል ውስጥ በሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ዎክ በድምቀት ይመረቃል።”ያልተነበበው አንባቢ” መፅሐፍ የቤተልሔም ፕላዛ ባለቤት በነበሩት በአቶ ነጋሽ ባልቻ ሰብቼ አስደማሚ የሕይወት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን ነው የተባለ ሲሆን አቶ ነጋሽ ባልቻ ከምንም ተነስተው ለከፍተኛ ስኬት የበቁበትን ምስጢር ይተነትናል ተብሏል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ፣ አቶ ብርሃነ መዋ፣ ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ፣ ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባው፣ የሜቄዶኒያው መስራች ቢኒያም በለጠ እና ዶ/ር ዮናስ አሸኔ የሚገኙ ሲሆን በመጽሐፉ ዙሪያ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከመጽሐፉ የሚገኘው ገቢ ለመቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ይውላልም ተብሏል። መጽሐፉ በ329 ገጽ ተቀንብቦ በ400 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ደራሲው ከዚህ ቀደም “ያልተሄደበት መንገድ፣ የሀገር ፍቅር ዕዳ፣ በዘመናት መካከል እና ሶስት ሺህ ሌሊቶች የተሰኙ መፅሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው አይዘነጋም።



Read 20778 times