Saturday, 07 January 2023 00:00

“አፍላ ገፆች” የግጥም ስብስብ በመተግበሪያ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

በገጣሚ ዮናስ መስፍን የተፃፉ 90 ያህል ግጥሞችን ያካተተው “አፍላ ገፆች” የግጥም መድብል “አፍሮ ሪድ” በተሰኘ የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ለንባብ በቃ፡፡ ግጥሞቹ በተፈጥሯዊ ፅንሰ ሀሳቦችና ማህበራዊ ጉዳዮች ያተኮሩ መሆናቸውን የገለፀው ገጣሚ ዮናስ መስፍን፣ መፅሀፉ በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ለንባብ መቅረቡ ስነፅሁፉ ከዘመኑ ጋር የሚያራምደውን ቴክኖሎጂ እንዲዛመድ ካለው ፅኑ ፍላጎት በዚህ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ መምረጡንም ጨምሮ ገልጿል፡፡
አፍላ ገፆች የግጥም ስብስብ በ4.99 ዶላር ለገበያ መቅረቡ የታወቀ ሲሆን አንባቢያን ግጥሞቹን በ “አፍሮ ሪድ” (afro read) የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ በኩል ማግኘት እንደሚችሉም ገጣሚው ጠቁሟል፡፡

Read 1145 times