Saturday, 07 January 2023 00:00

“በቋንቋ ማስተማር ልሳነ ብዟዊና ባህለ ብዟዊ ጭብጦች” መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ ፅሁፍ የአማርኛ ትምህርት ክፍል መምህር በሆኑት ኤፍሬም ጥሩነህ (ዶ/ር) የተሰናዳው “በቋንቋ ማስተማር ልሳነ ብዟዊና ባህለ ብዟዊ ጭብጦች” የተሰኘ አዲስ መፅሀፍ ለንባብ በቃ፡፡
መፅሀፉ የቋንቋና የባህልን ግንኙነት፤ ለመዳና ለውጥ፣ የልሳነብዟዊነት (multilingualism) እና የባህለብዟዊነት (multiculturalism) ሀሳቦች፣ ከቋንቋ እኩልነት ጋር በተያያዘ ስለሚነሱ ሙግቶች፣ ስለ ቋንቋ ፖሊሲ አስፈላጊነት፣ ልሳነብዟዊ የቋንቋ ፖሊሲ ሲተገበር ስለሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችና ተያያዥ ጉዳዮች ተዳስሰውበታል፡፡ በተጨማሪም በመፅሀፉ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማርን ጉዳይ ምሁራን የማያዩበት አዎንታዊና አሉታዊ ሁኔታ እንዲሁም የልሳነብዟዊና ባህለብዟዊ ትምህርት ምንነትና የሀገራት ተሞክሮ የተካተተበት ሲሆን በተለይ የቋንቋ መምህራን የልሳነብዟዊና ባህለብዟዊ ፅንሰ ሀሳብን እንዲረዱና የቋንቋ ትምህርት በሚያስተምሩበት ጊዜ ተማሪዎቻቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲያውቁ ይረዳቸዋል ተብሏል፡፡
መፅሀፉ በ5 ምዕራፎች ተመጥኖ በ194 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ500 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል፡፡ የመፅሀፉ አዘጋጅ መምህር ኤፍሬም ጥሩነህ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም ማለትም በ2006 ዓ.ም “የቃላዊ ተግባቦት ክሂል ማስተማሪያ” የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ ማብቃታቸው አይዘነጋም፡፡


Read 1608 times