Saturday, 13 May 2023 20:01

በአዲስ አበባ የመንግስት መ/ቤቶች የስራ ሰዓትን ወደ 16 ሰዓት ለማራዘም እየተሰራ ነው- ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ የመንግስት የስራ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበትን ሰዓት ከ8 ሰዓት ወደ 16 ሰዓት ለማራዘም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡  መ/ቤቶቹ አገልግሎታቸውን እስከ ምሽት ድረስ እንዲሰጡ የማድረጉ ተግባር የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴም ያነቃቃል ተብሏል፡፡የከተማ አስተዳደሩ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ባካሄዱት የጋራ ውይይት ላይ ይፋ የተደረገው እቅድ እንደሚያመለክተው፤ በከተማዋ የሚታየውን የተገልጋዮችን ችግርና መጉላላት ለመቅረፍ የሚቻልበት መንገድ እየተፈለገ ነው፡፡
የመንግስት መ/ቤቶች ለተገልጋዮች በሚሰጡት አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እየቀረቡ መሆኑን የሚጠቁመው ዕቅዱ፤ ይህን ቅሬታና ችግር ለመፍታት የአገልግሎት ሰዓቱን ወደ 16 ሰዓት ማራዘም እንደ አንድ መፍትሄ መወሰዱንና ይህም ለመተግበር እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።በዚሁ የመንግስት ስራን ወደ 16 ሰዓት ለማራዘም በተያዘው እቅድ ሰራተኞች በፈረቃ የሚሰሩበት ሁኔታ ሊመቻች እንደሚችልና አሰራሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞችን አዋጅ የማይጥስ እንደሚሆንም ተነግሯል፡፡ የከተማው አስተዳደር የመ/ቤቶቹን የአገልግሎት ሰዓት የማራዘም ፈቃዱን ተግባራዊ ለማድረግ ጥናት እያካሄደ መሆኑንና በመጪው በጀት ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡


Read 1618 times