Saturday, 03 September 2011 12:00

..አልቻልኩም..

Written by  አልአዛር ኬ
Rate this item
(0 votes)
  • ማለትን የደፈሩት ጠ/ሚኒስትር ...

ባሳለፍነው ሳምንት በዓለም የፖለቲካ መድረክ ግንባር ቀደም ዜናዎች     ከነበሩት አንዱ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የናኦቶ ካን በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣን መልቀቅ ነበር፡፡ የገዥው የጃፓን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ የነበሩት የስልሳ አራት ዓመቱ አዛውንት ፖለቲከኛ፤ ላለፉት አሥራ አምስት ወራት ወይም ለአንድ ዓመት ከሦስት ወር ጃፓንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መርተዋል፡፡
የጃፓንን ፖለቲካ የሚከታተሉ ምሁራን፤ ናኦቶ ካንን እድለ ቢሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሏቸዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትርntÜN ኃላፊነት ገና እንደተረከቡ ግብግብ የገጠሙት ከሀገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ከካዬን ጋር በተያያዘ ጃፓንን የገጠማትን የገንዘብና የኢኮኖሚ ችግር ለማቃለልና ለመፍታታ ነበር፡፡ የዚህን ፈታኝ ትግል ውጤት ገና እንኳ ፍንጩን ሳያዩ፣ ሀገራቸው ጃፓን መላ ዓለምን ባስደነገጠና እጅግ ከፍተኛ የሰውና የንብረት ጥፋት ባስከተለ የተፈጥሮ የሱናሚ አደጋ ተመታች፡፡

ከገጠማት የገንዘብና የኢኮኖሚ ፈተና ለመውጣት እልህ አስጨራሽ ትግል ላይ ለነበረችው ጃፓንና መላው ህዝቧ የሱናሚው አደጋ ጨርሶ ያልታሰበና በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ዓይነት ነበር፡፡ የሱናሚው አደጋ የፈጠረው መጠነ ሰፊ ችግር፣ እጅግ ውስብስብና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚም ሆነ ለህዝቧ ደህንነት እጅግ አስጊ፣ ጠባሳውም ጥልቅና ሰፊ እንዲሆን ያደረገው፣ በአደጋው ሳቢያ የፉኩሽማ የኒውክሊየር ጣቢያው ክፉኛ መጐዳቱና የኒውክሊየር ጨረር አፈትልኮ የመውጣቱ ጉዳይ ነበር፡፡
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናኦቶ ካንም የተጋፈጡትና መፍትሔውን የማፈላለግ የመሪነት ኃላፊነት የወደቀባቸው ከዚህ እጅግ ሰፊና አስቸጋሪ ፈተና ጋር ነበር፡፡ እናም የመፍትሔውን ጥበብና ማስተዋል አምላካቸው በልብና አዕምሯቸው ውስጥ ብርሃኑን እንዲያበራላቸው እየተማኑ፣ የአቅማቸውንና የችሎታቸውን ያህል ከወዲያ ወዲህ ሮጡ ባዘኑ፡፡
በአደጋው ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው እርዳታ እንዲያገኙና እንዲያገግሙ እንደ በፊቱ እንኳ ባይሆን ከደረሰው ሰፊና ትልቅ አደጋ አኳያ የእለት ህይወትን አቆይቶ፣ ነገንና ከነገ ወዲያን በአዲስ ግንባታ እንዲጀምሩ ለማድረግ፣ የሠራተኛ ሰማያዊ ጃኬታቸውን ሳያወልቁ የመሪነት ኃላፊነታቸውን ለመወጣትና ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ካጋጠማቸው የችግር ጉድጓድ ጐትቶ ለማውጣት ታግለው ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ናኦቶ ሀገራቸውና ህዝባቸው ያጋጠማቸውን አስቸጋሪ ፈተና እንዲወጡና ዳግመኛ በእግራቸው እንዲቆሙ የቻሉትን ያህል ቢጥሩም የህዝባቸውን ሞገስ ማግኘት ግን ሳይቻላቸው ቀረ፡፡ አደጋው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች ያልወረደባቸው የትችትና የውግዘት ናዳ አልነበረም፡፡ ነገር ግን እንኳን በእንደዚህ ዓይነት ፈታኝ ወቅት ይቅርና በሰላሙም ቀን ቢሆን የተቀናቃኝ ፓርቲ ውግዘትና ትችት ያለና የሚኖር ነው በሚል መቋቋም ችለው ነበር፡፡ ከአቅምና ከችሎታቸው በላይ ሆኖ ቀን ከሌት ናላቸውን ያዞረው ግን ከህዝቡ የሚሰነዘርባቸው ትችትና ቁጣ ነበር፡፡ አዛውንቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናኦቶ ካን፤ በሱናሚ አደጋው የተጐዱትንና የመልሶ ማቋቋሙን እንቅስቃሴ ለማየትና የቅርብ ክትትልና አመራር ለመስጠት፣ ከቦታ ቦታ በሚዘዋወሩበት ወቅት ያስተናገዱት የአደጋውን ሰለባዎች ቁጣና ስድብ ብቻ ሳይሆን ጥፊና በእንቁላል መደበደብን ጭምር ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ናኦቶ ግን የተቆጡና ያዘኑ ጃፓናውያንን ቁጣ፣ ስድብና ጥፊ ችለው ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሔ ለማስገኘት መንግሥታቸውን እየመሩ የቻሉትን ያህል ቢሮጡም፣ የሚመሩት የጃፓን ህዝብ በሳቸውና በአመራራቸው ያለውን አመኔታ እለት ተእለት ከመሸርሸርና ወደ ታች ከማሽቆልቆል ለማስቆም ጨርሶ ሳይቻላቸው ቀረ፡፡
ህዝቡም ከደረሰበት ከባድ የተፈጥሮ አደጋና የኢኮኖሚ ሸክም ጋር ፊት ለፊት እየተጋጠፈ፣ መልእክቶቹን በቀላልና ግልጽ ቋንቋ ለጠቅላይ ሚኒስትር ናኦቶ ካንና እርሳቸው ለሚመሩት መንግሥት ማቅረቡን ቀጠለ፡፡
በአንድ ድም በመሆን ..ጠቅላይ ሚኒስትር ናኦቶ ካን çY- ሥልጣን ከያዝክበት ቀን ጀምሮ በዋናነት ኤክስፖርት መር የሆነውን የሀገራችንን ኢኮኖሚ ይበልጥ እንዲያንሠራራና ከገንዘብ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን የኢኮኖሚ ቀውስ እንዲረጋጋ ማድረግ አልቻልክም፡፡ የሱናሚው አደጋ የፈጠረውን መጠነ ሰፊ ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር መቋቋምና ሀገሪቱን በተቻለ ፍጥነት መልሳ እንድትገነባና እንድታገግም የሚያደርግ፣ በተለይ ደግሞ የፉክሽማን የኒውክሊየር አደጋ ለመቀነስና ለመቆጣጠር የሚያስችል የረባ ፖሊሲ ማውጣትና በሥራ ላይ ማዋል ጨርሶ አልቻልክም፡፡ ሥልጣን ከያዝክ ጀምሮ የጠቅላይ ሚኒስትርntÜN ከፍተኛ ኃላፊነት ጃፓንና ህዝቧ የደረሰባቸውን ኢኮኖሚያዊና ሰብአዊ ችግር በተሻለ ተቋቁመው ዳግም በእድገት ጐዳና እንዲራመድ ለማድረግ ሳይሆን ጭራሹኑ የማይረባ ፖሊሲ መፈተኛና የአመራር ሀሁ መለማመጃ አደረግኸው፡፡ በአጠቃላይ አንተ ጃፓንና ህዝቧን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመምራት አቅምና ችሎታ የለህም.. በማለት ሀሳባቸውንና አቋማቸውን በቁርጠኝነት በግልጽ አቀረቡ፡፡
የህዝባቸውን መልእክት የሰሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ናኦቶ ካን ይኼኔ እጅ ሰጡ፡፡ መቼም የሰለጠነና የዲሞክራሲ ሥርዓት በእውነት የሰፈነበት ሀገር ባለቤት መሆንና በዚያችም ሀገር እንደመኖር ያለ ጽድቅ፣ ለሰው ልጅ በዚህች ዓለም ላይ ከቶ የለም፡፡ ጃፓን ከእነዚህ ሀገራት አንዷ በመሆኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ናኦቶ ካን፤ የህዝባቸውን ግልጽና ቀጥተኛ መልእክት ቸል ብለውና ንቀው ሥልጣናቸውን የሙጥኝ ለማለት አልቻሉም፡፡
የህዝብ ድምጽ በሚሰማበት፣ የህዝብ ይሁንታና ፈቃደኝነት ከሁሉም ነገር በላይ በሚከበርበት ሀገር፤ የህዝብን ድምጽና ይሁንታ ቸል ብሎ የሥልጣን መንበሩን የሙጥኝ በማለት ህዝብንና ሀገርን እንዳሻው መግዛት ጨርሶ አይቻልም፡፡ ስለዚህም የህዝባቸውን አመኔታና ይሁንታ እንዳጡ የተረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ናኦቶ ካን፤ አንጃ ግራንጃ ሳያበዙ ሥራቸውንና የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ቁርጥ ውሳኔ ወሰኑ፡፡
በዋና ፀሐፊነት ይመሩት የነበረው ገዢው የጃፓን ዲሞክራቲክ ፓርቲ፣ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ በተዘጋጀላቸው መድረክ የፓርቲና የመንግሥት ጓዶቻቸውን የሀዘንና የቅሬታ ጥላ ባጠላበት ፊት እያዩ፣ የሽንፈት ስሜት በከባዱ በተጫነው የድም ቃና አንገታቸውን ሰብረው እንዲህ x§*cW:-
..እጅግ አስከፊና አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኜ ማድረግ ያለብኝን ነገር እንዳደረግሁ ይሰማኛል፡፡ አሁን ግን የተከበረና አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን የሚችል ሁነኛ ሰው ከመካከላችሁ ስትመርጡ ማየት እፈልጋለሁ፡፡..
ጠቅላይ ሚኒስትር ናኦቶ ካን፤ ይህችን አጭር ንግግር ለፓርቲያቸው አባላት ተናግረው እንደጨረሱ፣ በሀገራቸው ወግና ሥርዓት የስብሰባውን ታዳሚ፣ የፓርቲያቸውን አባላት ለጥ ብለው እጅ በመንሳት፣ ለአስራ አምስት ወራት ወይም ለአንድ ዓመት ከሦስት ወር የቆዩበትን የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣናቸውን በይፋ መልቀቃቸውን አሳውቀው፣ ወደ ቤተ መንግሥታቸው ሳይሆን ወደ ግል መኖሪያ ቤታቸው አለአንዳች አጀብና ከበርቻቻ በጥታ አመሩ፡፡
ይህንንም ተከትሎ ዋና ዋና የዓለም ዜና አውታሮች፣ ዜናውን በሰበርነት እየተቀባበሉ ለዓለም ህዝብ ዓይንና ጆሮ ሲያደርሱት፣ የጉዳዩ ዋና ባለቤት የሆነው የጃፓን ህዝብ ግን ሁኔታውን ልክ እንደተለመደ የአዘቦት ቀን ሥራ በመቁጠር፣ ትንሽም እንኳ ሳያካብድ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ናኦቶ ካንን የአመራር ጊዜ ተነቦ እንዳለቀ መጽሐፍ ወደ ታሪክ መደርደሪያው መልሶ፣ የእሳቸውንም ጉዳይ የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ታሪክ ወደሚመዘገብበት የታሪክ መዝገብ መርቶ፣ ዋነኛና አንገብጋቢ ትኩረቱን ገዢው የዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ አድርጐ በሚመርጠውና ቀጣዩ የጃፓን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር በሚሆነው ሰው ላይ ያዞረው በብርሃን ፍጥነት ነበር፡፡
አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የፓርቲ አባሎቹን ሰብስቦ ..በሉ እንግዲህ ይህችን ሀገርና ህዝቧን የመምራቱን ነገር እኔ አልቻልኩበትምና በእኔ ምትክ ህዝቡንና ሀገሪቱን ከእኔ በተሻለ ብቃትና ችሎታ መምራት የሚችል፣ የህዝቡን አመኔታና ሞገስም ከእኔ በተሻለ ያገኘና የተከበረ ሁነኛ መሪ ምረጡ.. ብሎ ያለአንዳች ኮሽታ፣ ሥልጣን መልቀቁ እጅግ ድንቅና ስልጡን የፖለቲካ ባህልን የሚያንፀባርቅ ከመሆኑም ባሻገር እንደ እኛ ላለው አገር የቅናት  ስሜት መፍጠሩ የማይቀር ቢሆንም ሁኔታው ግን ለልብም ሆነ ለመንፈስ ደስታን የሚያጐናፍ ነው፡፡
እንግዲህ ጨዋታን ጨዋታ ያመጣዋል እንዲሉ፣ የጃፓኑን ጠቅላይ ሚኒስትር የናኦቶ ካንን ፖለቲካዊ ክስተት ያጫወትኳችሁ በሀገርና በህዝብ አመራር ጉዳይ ዋናና ትልቅ ፋይዳ ያለውን አንድ ትልቅ ቁም ነገር በተሻለ ማስተዋልና ጥሞና እኛም ልብ እንድንለው አጽንኦት ለመስጠት ነው፡፡
የጃፓን ህዝብ ለአንድ ዓመት ከሦስት ወር የመሩትን ጠቅላይ ሚኒስትር፣ በሥልጣን ዘመናቸው ያሳዩትን የአመራር ችሎታና ብቃት በመመርመርና በመመዘን፣ እምነት የሚጥሉባቸውና ካጋጠማቸው ችግር ያወጣናል ብለው የሚተማመኑባቸው መሪ እንዳልሆኑም መረዳትና አቋም መያዝ ችሏል፡፡ የያዘውን አቋምም በግልጽና በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተላልፏል፡፡ ህዝቡ ለመሪው ካስተላለፋቸው መልእክቶች ዋነኛው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በያዙት ሥልጣን አማካኝነት ህዝቡንና ሀገሪቱን የፋይዳ ቢስ ፖሊሲዎች መሞከሪያና የሀገር አመራር ሀሁ መለማመጃ አድርገውታል የሚል ነው፡፡ ልብ ሊባል የሚገባው ትልቁ ቁም ነገርም ይኸው ነው፡፡የዲሞክራሲ ሥርዓት በሰፈነበት ሀገር የመሪዎች የመሪነት ሥልጣን የሚመነጨው ከህዝቡ ፈቃድና ይሁንታ ብቻ ነው፡፡ ህዝብ በነጻ ምርጫውና ፍላጐቱ ሲፈቅድና ይሁን ሲል ለፈቀደውና ይሁን ላለው ሥልጣን ይሰጣል፡፡ ሳይፈቅድና ይሁንታውን ሲነፍግ ደግሞ የሰጠውን የመሪነት ሥልጣን መልሶ ይነጥቃል፡፡ ዲሞክራት የሆኑና በዲሞክራሲÃêE ሥርዓት አምነው የተጠመቁ መንግሥታትም ዋነኛ ትኩረታቸውና ጥረታቸውም፣ የህዝቡን ይሁንታና ፈቃድ በማግኘት ብቻ ወደ ሥልጣን መውጣትና የህዝቡን ፈቃድና አመኔታ በማግኘትና በመጠበቅ በሥልጣናቸው መቆየት መቻል ብቻ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ታዲያ አቻ የሌለው ትልቁ የህዝብ ፈቃድና አመኔታ መጐናፊያ ቁልፍ የመንግሥት አመራር ችሎታና ብቃት ነው፡፡
እንደ ጃፓን ባሉ በዲሞክራሲ ባህላቸው የዳበሩና የሰለጠኑ ሀገራት፣ የመንግሥት የአመራር ችሎታና ብቃት፣ የመንግሥቱን የፖለቲካ ሥልጣን መወሰን የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ እንደ ጃፓን ባሉ ሀገራት ያለ በቂ ጥናትና የማስፈም አቅም የተለያዩ ፖሊሲዎችን በማውጣት ህዝብንና ሀገርን መሞከሪያ ማድረግና ሥልጣንን የአመራር ሀሁን መለማመጃ ማድረግ፣ በክብር ከወጡበት የሥልጣን መንበር በቅሌት አንገት አስደፍቶ ያስባርራል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት በጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በናኦቶ ካን ላይ ደርሶ ያየነው ይህ መሠረታዊ ፖለቲካዊ በእኛ አገር ብዙም የሚታወቅ አይደለም፡፡
ላለፉት ሃያ ዓመታት በቅርበት ለመታዘብ እንደቻልነው፣ የተለያዩ ፍሬ አልባ ፖሊሲዎችን ያለአንዳች በቂ ጥናትና የማስፈም አቅም በዘፈቀደ እያወጣ፣ ህዝቡንና ሀገሪቱን የፖሊሲና የመመሪያ መሞከሪያና መለማመጃ በማድረግ፣ የአመራርን አቡጊዳ እየተማረ የሚገኝ፤ እንዲህ እያደረገም ለሃያ ዓመታት ሥልጣኑን እንደተቆናጠጠ የሚገኝ ፓርቲና መንግሥት ቢኖር ኢህአዴግና እሱው የሚመራው መንግሥት ብቻ ይመስላል፡፡
ይህን ዋና ቁም ነገር ልብ እንዲባል አፍን ሞልቶ መናገር የሚቻለው፣ እንዲሁ በወቀሳ አባዜ ሳይሆን ለዘመናት በተደጋጋሚ የታዘብነውና መንግሥት ያለበቂ ጥናትና የማስፈም አቅም እያወጣ የሞከረብን ፖሊሲና መመሪያ የፈጠሩትን ችግርና ጉዳት ተሸክመን ስለኖርን ነው፡፡
አሁን ወረቱ አልፎ ስሙ ተነስቶ ከማያውቀው፣ ነገር ግን ከዓመታት በፊት የኢትዮጵያ በምግብ ራስን የመቻል ልዋጭ የለሽ ቁልፉ ነው እየተባለ ሲዘፈንለት ከነበረው የውኃ ማቆር ፖሊሲና መመሪያ አንስቶ፣ አሁን ትልቅ የችግርና የውዝግብ አቧራ እስካስነሳው የግብር ትመናና አሰባሰብ ፖሊሲና መመሪያ ድረስ በመዘርዘር ጉዳዩን መመርመር ስትጀምሩ፣ ኢህአዴግና የእሱ መንግሥት ሥልጣን ከያዙበት ከዛሬ ሃያ ዓመት ጀምሮ ያለበቂ ጥናትና የማስፈም አቅም የተለያዩ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን በማውጣት፣ የሚመራውን ህዝብና ሀገር መሞከሪያና የአመራር መለማመጃ ሲያደርጓቸው እንደኖረና አሁንም እንዳለ ለመረዳት ጨርሶ አይገዳችሁም፡፡ከጥቂት ወራት በፊት እጅግ አሰልቺ በሆነ ሁኔታ የድል አታሞ ሲደለቅለትና በደረቅ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ስንቀጠቀጥበት የነበረውን የዋጋ ቁጥጥር መመሪያ ብንወስድ፣ መንግሥት ያለበቂ ጥናትና የማስፈም አቅም እንዳሻው የሚያወጣቸውን መመሪያና ፖሊሲዎች ህዝቡ ላይ በግድ እየጫነ እንዴት መለማመጃ እንደሚያደርግ አንድ አብነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ይህን ፖሊሲ በተመለከተ መንግሥት እንዲያ በፉከራ እንዳላሰለቸን ሁሉ፣ ዛሬ እንዳልነበረ ያህል ወሬውን ለማንሳት እንኳ የማይደፍረው ለምን ይመስላችኋል? ፖሊሲና መመሪያው በእኛው ላይ ተሞክሮብን ውጤቱ ዜሮ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡እንዲህ ያለውን ነገር እጅግ አሳዛኝ የሚያደርገው ትልቁ ጉዳይ፣ አለአግባብ የመንግሥት ፋይዳ ቢስ ፖሊሲና መመሪያ መሞከሪያና የአመራር መለማመጃ መሆናችን ሳያንሰን፣ የተሞከረብን ፖሊሲና መመሪያ የሚፈጥሩብንን ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ጉዳትና ጫና ለብቻችን ተሸከመን፣ ህይወትና ኑሮአችን እለት ተእለት እንደ አለት እየከበደን፣ በነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ የምንንገላታው እኛው መሆናችን ነው፡፡
መንግሥት ግን ምንም ችግር የለበትም፡፡ ለምን ቢባል? ያለበቂ ጥናትና አስፈጻሚ አካል እንዳሻው የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎችና መመሪያዎች በፈለገው ጊዜ የሚሞክርብንና አመራር የሚለማመድብን እኛ ስላለንና ለዚህም ብሎ እንዳሻው የሚያወጣው የህዝብ ገንዘብም በካዝናው ሁሌም ስላለው ነው፡፡የወጣውን ፖሊሲና መመሪያ ገና በወጣበት ቀን ሙሉ በሙሉ እንደተሳካ ቆጥሮ፣ በፕሮፓጋንዳ ጉሮ ወሸባዬ እየጨፈረ፣ እኛኑ ሲያሰለቸን የሚከርመው መንግሥት፤ ፖሊሲውና መመሪያው ከሽፎ የህዝብ ሀብትና ንብረት ሲጠፋና የዜጎች ህይወት ሲመሳቀል ግን ልክ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ያህል ውሾን ያነሳ ውሾ ብሎ ጭጭ ይላል፡፡
በዚህ ዓይነት አሳዛኝ የመንግሥት ድርጊት የተፈጠረው ችግርና ቀውስ፣ ለወደፊቱ እንዳይደገም ትምህርት እንዲሆንና ቢያንስ የመንግሥትን ስህተት ያለአበሳው እየተቀበለና እየተሸከመ በኑሮው ፈተና ለሚያየው ህዝብ፣ ትንሽዬ ክብርና ሞራል በሚል አጥፊው የመንግሥት አካል ለጥፋቱ በይፋ አለመቀጣትና አለመወቀሱ ተደራራቢ በደል ነው፡፡
የአንዲት ስኒ ቡና VAT አላስከፈልክም በሚል የቡና ሻጩን ጣት ለመቁረጥ በብርሃን ፍጥነት የሚንቀሳቀሰው መንግሥት፤ ያለበቂ ጥናትና አቅም እያወጣ ለማስፈም በሞከረብን የተለያዩ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ሳቢያ አንድና ሁለት ሰዎችን ሳይሆን የድፍን አገሩን ኑሮና ህይወት ሲያመሳቅለው፣ ለዚህ ከባድ ጥፋት እንደ መንግሥትነቱ ተጠያቂዎቹን በግልጽ መቅጣትና የጉዳቱ ሰለባ የሆኑትን ህዝቦቹን በጨዋ ደንብ ይቅርታ ጠይቆ፣ ፍርዳቸውን እንዲቀበሉ ማድረግ ሲገባው፣ ልክ መልካም ሥራ እንደሠራ ሁሉ ነገሩን በዝምታ ማለፉ፣ ለራሱና ለህዝቡ ያለውን አመለካከትና አቋም በግልጽ ያሳያል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ የመንግሥትን ነገረ ሥራ የታዘበ ሰው፣ ህዝብ መንግሥት የፈለገውን ዓይነት ፖሊሲና መመሪያ፣ አዋጭና አክሳሪነቱን ያለበቂ ጥናት ሊሞክርበትና ሊለማመድበት፣ በሙከራውና በልምምዱ የሚፈጠረውን እዳ፣ ጉዳትና የኑሮ ምስልቅልቅ ለብቻው እንዲችል የተፈረደበት፤ መንግሥት ደግሞ ያወቀ የመሰለውንም ሆነ በህልሙ ያየውን የፈለገውን ዓይነት ፖሊሲና መመሪያ በህዝቡ ላይ እየፈተነና እየሞከረ፣ የአመራርን ሀሁ ለመለማመድ የወሰነ ቢመስለው ጨርሶ አይፈረድበትም፡፡በእንደዚህ ዓይነት አሳዛኝ አሠራር፣ የህዝቡን ይሁንታና አመኔታ ይዤና አስጠብቄ እቀጥላለሁ ማለት ተመራጭና አዋጭ አሠራር እንዳልሆነ ለመንግሥት ማስረዳት ለቀባሪው እንደ ማርዳት ይቆጠራል፡፡
ከሁሉም የተሻለው ዘዴ እንዲህ ያለውን አጓጉል ድርጊት ማቆምና በምትኩ ሥራን በብቃትና በማስተዋል ማከናወን ነው፡፡ በሥልጣን ላይ ሆኖ የአመራርን ሀሁ፣ በህዝቡ ላይ መለማመድ የነገን እጣና አወዳደቅ አያሳምረውም፡፡ ህዝብን ያለአበሳው እዳ እያሸከሙና የሰውን አበሳ ተቀባይ እያደረጉ ለመኖር መወሰንም ሆነ መሞከር፣ የማታ ማታ ጫማን አውልቆ እፎይ ብለው የሚያርፉበት ጥግ እንዳያሳጣ ያሰጋል፡፡ እናም መንግሥት ለእኛም ሆነ ለራሱ ሲል ከዚህ አጓጉል ድርጊቱ እንዲታቀብ በትህትና እንጠይቃለን፡፡

 

Read 2488 times Last modified on Saturday, 03 September 2011 12:08