Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 September 2011 11:51

አቦይ ስብሀት እና ፕሮፌሰር መስፍን

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከተቻላችሁ ደህና ደህናውን አውርሱን፤ ካልቻላችሁ ገለል!..
ኦሮቢንዶ የተባለ ህንዳዊ ፈላስፋ፤ ..ምንም ጠንካራ ብትሆን መጨረሻ ላይየምትሸነፍበት ጦርነት አትጀምር..
ይላል፡፡በአቦይ ስብሀትና በፕሮፌሰርመስፍን መካከል እንደዋዛ
የተጀመረው የጋዜጣ ላይ አስጥ አገባ
መጀመሪያ ላይ የወደድኩትን ያህል ሄዶ ሄዶ ወደ ዘር ፖለቲካ በመቀየሩ ማዘኔ አልቀረም፡፡ ትልቅ ሰው ድሮ ቀረ! ብዬ ዝም እንዳልል ደግሞ እነዚህ ራሳቸው የድሮ ሰዎች ሆኑብኝ! ከዚያና ከዚህ ሆነው እኛና እነርሱ እያሉ ይጠዛጠዙ ገቡ፡፡ ይኸው እኔንም ጎትተው አስገቡኝ፡፡

ከዚህ ቀደም በአቦይ ስብሀት ነጋ ትንታኔዎች ላይ እኔም የበኩሌን ሐሳብ መስጠቴን የተመለከቱ አንዳንድ ሰዎች፣ ፕሮፌሰር መስፍን በተናገሩት ላይም የሚሰማኝን እንድጽፍ ጐተጐቱኝ፡፡ እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ ህሊናዬም ጐተጐተኝ፡፡ መቼም ቢሆን ለእውነት መቆም እንዳለበኝ ለራሴ የገባሁት ቃል ኪዳን ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆን እንኳ ማፍረስ እንደሌለብኝ ተገንዝቤ እንደወትሮው ሁሉ በታላቅ ልዕልና ወንጭፌን አነሳለሁ፡፡ (መቼም በዚህች አገር ጎሊያዶች በዝተዋልና)፡፡ በመሰረቱ አንድ ሕዝብ ለዚያውም በውሸትና በጥላቻ ታሪኩ ሲጎድፍ ዝም ብሎ ማየት ተገቢ አይደለም፡፡  በእርግጥ ፕሮፌሰር መስፍን አንድ ተራ ግለሰብ ቢሆኑ ኖሮ ንቆ መተው ይቻል ነበር፡፡ ለምሳሌ እንዲህ ያለ አስተያየት የሰጡት ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም ቢሆኑ ኖሮ መቼስ እሳቸው ወታደር ናቸው፤ ለማንበቢያ የሚሆን ጊዜ አልነበራቸው፡፡ በተፈጥሮአቸውም ቁጭ ብለው ታሪክ ለማጥናት የሚያስችል ትዕግስት ላይኖራቸው ይችላል በሚል እሳቤ ይቅርታ አደርግላቸው ነበር፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ግን ብዙ የተመራመሩ ሊቅ ናቸው፣ ፕሮፌሰር አንባቢ ናቸው፣ ታሪክ ያውቃሉ፣ ሊሳሳቱ አይችሉም በሚል ያሉትን ሁሉ የሚቀበል ይኖራል፡፡ በነገራችን ላይ የፕሮፌሰሩ ሑፎች አንባቢ እና አድናቂ ነኝ፡፡ ግን ደግሞ እንደማንኛውም ሰው ሊሳሳቱ እንደሚችሉ፤ አንዳንዴም ከእርሳቸው ፈፅሞ የማይጠበቅ ነገር ይዘው ለክርክር እንደሚቀርቡ አውቃለሁ፡፡ ለምሳሌ ..አማራ የሚባል ሕዝብ የለም፡፡ አማራ ማለት ክርስቲያን ማለት ነው.. ብለው ይከራከራሉ፡፡ ቢያንስ ይህ አባባል ሙስሊም የሆኑ የወሎ ወንድሞቻችንን ቅር እንደሚያሰኝ ማሰብ አይከብድም፡፡
እንዲሁም አፄ ቴዎድሮስን ከመንግስቱ ኃ/ማሪያም እና ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር ያነፃፀሩበት መንገድ ለባለራዕዩ ንጉሳችን የሚመጥን አልመሰለኝም፡፡ ነገር ግን ለፕሮፌሰር ያለኝ ክብር አጋደለብኝና ግድ የለም ምሑራዊ ስህተት ነው ብዬ አለፍኩት፡፡ ሌላም ሌላም ነገር መጥቀስ ይቻል ይሆናል ግን ለዛሬው የተነሳሁበትን ርእሰ ጉዳይ ላለመሳት፣ ባለፈው ጊዜ በ..ፍትህ.. ጋዜጣ ላይ በሰጡት አስተያየት ብቻ አተኩራለሁ፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን፤ ..በኤርትራና በትግራይ ይኖሩ የነበሩ የኤርትራና የትግራይ ዜጐች ተግተው ኢጣልያንን ቢወጉ ኖሮ ከሐረር፣ ከሀድያና፣ ከሲዳሞ፣ ከሸዋ ወደ ሰሜን መዝመት አያስፈልጋቸውም ነበር፤ ይህ ቢሆን ዛሬ ሌሎች ያልሞቱትን ሞት በመሞታቸው አይወቀሱም ነበር..፤ ካሉ በኋላ ወረድ ብለው ደግሞ፤
..አፄ ምኒልክ ጦራቸውን ሰብስበው በእግርና በበቅሎ ከደቡብ ተነስተው ትግራይ እስቲደርሱ ኤርትራና ትግራይ ምን አድርገው ጠበቋቸው? የኢጣልያ ጦር ትግራይን ሰንጥቆ አምባ አላጌ እስቲደርስ ማን ሊያቆመው ሞከረ? የኢጣሊያ ጦር መቀሌ ገብቶ ሲመሽግ ማን ተከላከለው? ስብሓት እስከዛሬ ሳይገለጥለት ቀርቶ ከሆነ የኢጣልያንን ጦር ከአምባ አላጌ ያስወጣው የምኒልክ ጦር ነው፡፡ ከመቀሌም ምሽግ ያስወጣው የጣይቱ ዘዴና የምኒልክ ጦር ነው፡፡ በኢትዮጵያዊ ይሉኝታ ተሸፋፍኖ የቆየውን እናፍረጥርጠው ከተባለ ለማን አሳፋሪ እንደሚሆን ግልጽ ነው፡፡.. በማለት ለአቦይ ስብሃት መልስ ይሰጣሉ፡፡
ይህን ስመለከት ..ፕሮፌሰሩ ምን ነካቸው?!.. አልኩኝ፡፡ በዚህ ጊዜ ህሊናዬ በጥልቅ ሽኩሽኩታ ይህን ነገር ቀድሞ አንድ ሰው ብሎት እንደነበር አስታወሰኝ፡፡ ለካ ካሁን በፊት የ..አዲስ ነገሩ.. መስፍን ነጋሽ ሁኔታቸው ግር ቢለው ..ፕሮፍ ምን ነካቸው.. ብሎ አስቀድሞ ጽፎ ነበር፡፡
የፕሮፌሰር ቀዳሚ ስህተት አቦይ ስብሀትን የትግራይ ሕዝብ ወኪል አድርገው መቀበላቸውና መልስ እንዲመልሱላቸው መጠየቃቸው ነው፡፡ እኔ ከእርሳቸው በላይ ባላውቅም የትግራይ ሕዝብ ለአቦይ ስብሀትም ሆነ ለፕሮፌሰር መስፍን እኩል ነው የሚደርሰው፡፡ ስለዚህ በኢጣሊያ ወረራ ጊዜ የትግራይ ሕዝብ የት እንደነበር የማያውቁ ከሆነ ጥያቄውን ለታሪክ ምሑራን ነው ማቅረብ የነበረባቸው፡፡
ፕሮፌሰር፤ ስብሀት ከማጥናትና ከመመርመር በፊት የሆነውን እንዳልሆነ፣ ያልሆነውን እንደሆነ አድርጎ መናገር ወደ ስህተት የሚያመራው፤ የራሱን መመሪያ ቢከተል ከስህተት ይድን ነበር ብለው ሲያበቁ ራሳቸው የአቦይ ስብሀትን ስህተት እንዳለ በመድገም፤ የሆነውን እንዳልሆነ፣ ያልሆነውን እንደሆነ አድርገው እንዲናገሩና ወደ ባሰ ጥልቅ ስህተት እንዲገቡ ሆነ፡፡
ለማንኛውም የፕሮፌሰር ጥያቄዎች ሳይመለሱ ቢቀሩ ወይም በዝምታ ብናልፋቸው የታሪክ ተወቃሽ ያደርገናልና የታሪክ መጽሐፍት ያሰፈሩትን ታሪክ እያጣቀስኩ የማውቀውን ልበል፡፡
..ዋናው ጥያቄ፣አፄ ምኒልክ ጦራቸውን ሰብስበው በእግርና በበቅሎ ከደቡብ ተነስተው ትግራይ እስቲደርሱ ኤርትራና ትግራይ ምን አድርገው ጠበቁዋቸው? የኢጣልያ ጦር ትግራይን ሰንጥቆ አምባ አላጌ እስቲደርስ ማን ሊያቆመው ሞከረ?.. የሚለው ነው፡፡
ኤርትራውያን ምን ያደርጉ ነበር ብለን መጠየቅ የምንችል አይመስለኝም፡፡ ቀደም ብሎ በአፄ ምኒልክ ለኢጣሊያ መንግሥት በመሸጡ፡፡ አፄ ምኒልክ ኤርትራን የሸጡት አፄ ዮሐንስ በህይወት እያሉ ነበር፡፡ ለዚህ እንደማስረጃ የምጠቅሰው አፈወርቅ ገብረየሱስ ..ዳግማዊ አጤ ምኒልክ.. በሚለው መጽሐፍ ላይ የሰጡትን ቃል ነው፡፡
.....ቀጥለውም ከኢጣሊያ መንግሥት ጋር ውስጥ ለውስጥ ተዋዋሉ፡፡ ውሉ አጤ ምኒልክ አጤ ዮሐንስን ወግተው በተገባዎ መንግስት ሊቆሙ፣ ለኢጣሊያ መንግስት በመሳሪአ ስላገዘ ተምጥዋ በላይ ጥቂት ተአውራጃው አገር አስመራን ሊሰጡ፣ ኢጣሊያ ግን ከተቀበለው ሌላ ተሻግሮ መሬት ለመያዝ እንዳያምረው ፍቅር እንዲሰፋ ንግድ እንዲለማ ነበረ፡፡ የዚህን ጊዜ አጤ ዮሐንስ ሰሐጢ ላይ ከኢጣሊያ ጦር ጋር ተሰላልፈው ነበረ፡፡..
wd TG‰Y ÞZB (እንደ ፕሮፌሰር መስፍን የትግራይ ዜጎች አልልም፡፡ የትግራይ ሕዝብ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ እንደሆነ የሚታወቅ ነውና) ስንመጣ ሌላ እውነት ነው የምናገኘው፡፡ የጣሊያን ጦር ወደፊት መግፋት ሲጀምር የራስ መንገሻና የአሉላ ጦር ነው መጀመሪያ የተጋፈጠው፤ ኢትዮጵያዊው የታሪክ ሊቅ አቶተክለ ጻዲቅ መኩሪያ፤ ..የኢትዮጵያ ታሪክ ከአፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ.. በሚለው መጽሐፋቸው ምስክርነታቸውን እንዲህ አስቀምጠውታል፡፡
..በ1887 ዓም በጥር 8 ቀን ራስ መንገሻና ራስ አሉላ ከሚመጣው ከኢጣሊያ ወታደር ጋራ ኩዓቲት ላይ ጦርነት ገጥመው በዠግንነት ከተዋጉ በኋላ ራስ መንገሻ ድል አድርገው፣ የኢጣሊያም የጦር ወታደር ሽሽት ዠመረ፡፡ በኋላ ግን ተጠባባቂ የነበረው የጄኔራል አሪሞንዲ አዲስ ጦር ደርሶ ሲዋጋ፣ ጊዜው ስለመሸ ጦርነቱ ቆመ፡፡ በማግስቱም  እንዲሁ ተዋግተው በኋላ ለኢጣሊያኖች አዲስ ጦር እንደገና መጣ ማለትን ከሐሰተኛ ሰው ስለሰሙ ወደ ኋላቸው ወደ ሰናዓፌ አፈገፈጉ”” በዚያም ሰፍረው ሳሉ የኢጣሊያ ጦር በግስጋሴ ደርሶ አደጋ ጣለባቸው፡፡ ስለዚህ ራስ መንገሻ ሰፈራቸውን ከነድንኳናቸው ትተው ወደ ኋላ ሸሹ፡፡ ኢጣሊያኖችም ካሉበት ስፍራ ራስ መንገሻ ሰፍረውበት ወደ ነበረው ወደ ሰናዓፌ በደረሱ ጊዜ በራስ መንገሻ ድንኳን ውስጥ ብዙ ዕቃና ይልቁንም ከዐፄ ምኒልክና ከደጃች ባሕታ ሐጎስ ጋር የተጻጻፉትን ደብዳቤ ባገልግል ውስጥ በማግኘታቸው ደስ አላቸው፡፡
በዚህ ጦርነት ከራስ መንገሻ ወገን አንድ ሺህ ሰው ሲሞት እንደዚሁ ትልቁ ደጃዝማች ተድላ፣ ደጃች በየነ፣ ደጃች ካሳ፣ ቀኛዝማች አንዳርጋቸው የሚባሉት መኳንንቶቻቸው አብረው ሞቱ፡፡ ሹም አጋሜ ተስፋዬም ቆስለው ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ  በነራስ መንገሻና በእነራስ አሉላ ይመራ የነበረው የትግራይ ጀግኖች እስከ አፍንጫው ከታጠቀው የኢጣሊያ ጦር ጋር እየተከታከቱ ዓመቱን ሙሉ ሲከላከሉ ነበር፡፡ ከዚያም አድዋ፣ አዲግራት፣ መቀሌ እያሉ ተራ በተራ እየተሸነፉ ኢጣሊያኖች አላጌ ድረስ ገፍቷቸዋል፡፡..
እነራስ መንገሻ እነ ራስ አሉላ ለምን ተሸነፉ የሚለውን በአራት ነጥቦች ከፋፍዬ ለማየት ልሞክር፡፡
hùlt¾:- አብዛኛው የትግራይ ጦር ከንጉሰ ነገስቱ ጋር ወደ መተማ ዘምቶ ስለነበር፣ ከመተማ ሽንፈትና ከንጉሰ ነገስቱ  ሞት በኋላ እንደ በፊቱ የነበረውን ጥንካሬና የሞራል ልዕልና ይዞ ይቆያል ተብሎ የሚታሰብ አይደለም፡፡አፄ ምኒልክ  ንጉሰ ነገስቱ እንደሞቱ በመጋቢት 18 ቀን 1881 ዓም ለኢጣሊያው ንጉሰ ዑምበርቶ በጻፉት ደብዳቤ፤ ነፍጥ ካገኙ ለዙፋኔ ስጋት ይሆኑብኛል በማለት ወደ ትግራይ ምንም ዓይነት ነፍጥ እንዳያልፍ፣ በአስመራም በኩል ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ምፅዋ ላሉ የኢጣሊያ አዛዦች ትዕዛዝ እንዲያስተላልፉላቸው ባቀረቡት ተማፅኖ መሰረት ተግባራዊ በመሆኑ ፤ በኋላ ኢጣሊያኖች በዘመናዊ ነፍጥ ታግዘው ለወረራ ሲመጡ፣ የትግራይ መሳፍንት ለመከላከል የሚችሉበት የረባ ትጥቅና ጥይት አልነበራቸውም””
ƒSt¾:- ‰S መንገሻ አልገበረልኝም በሚል ራሳቸው አፄ ምኒልክ በስህተት የኢጣሊያ ሰው እንዳይገሉ ሰግተው ..ያመለጠ ሉሌየን ለመቅጣት ትግሬ እወርዳለሁና ከመረብ ወዲህ ያሉ ሰዎቻችሁን ወደ አስመራ እንዲከርከም አድርጉ፤ ይሄን ማለቴ የሸፈተ አሽከሬን ስቀጣ የእናንተ ሰው ድንገት ተመካከል ተገኝቶ የሞተ እንደሆነ፣ ባልሆነ ነገር ፍቅራችን እንዳይሻክር ብዬ ነው.. ብለው ለኢጣሊያ መንግሥት ደብዳቤ ከጻፉ በኋላ ወደ ትግራይ በመዝመት አገሩን በመውረራቸውና በኢኮኖሚም በሰው ኃይልም እንዲዳከም በማድረጋቸው ነው፤ እኔ እንዲህ ቀላል አድርጌ አቀረብኩት እንጂ የተለያዩ የታሪክ ሐፍት ይህን ሁኔታ በልዩ ልዩ መልኩ ዘግበውታል፡፡
x‰t¾:- x‰t¾W MKNÃT የኢጣሊያን ጦር እንኳ እንዲህ በተዳከመው የትግራይ ጦር ይቅርና እነ  ዐጼ ዮሐንስን ለመገዳደር የሚያስችል በጣም ዘመናዊ የሚባል መሳሪያ የታጠቀ ጦር ነበር፡፡ ይልቅ ከላይ እንዳየነው ውጊያው የተጀመረው በ1887 ዓ.ም በጥር ስምንት ነው፡፡ የአድዋ ጦርነት ደግሞ የተካሄደው ከዓመት በኋላ በ1888 የካቲት 23 ነው፡፡ አፄ ምኒልክ እስከዚያው ድረስ የት ነበሩ?  አፈወረቅ ገብረየሱስ ለዚህ መልስ አላቸው፤ ..የኢጣልያ ጦር መቸም ብርቱው ጦሩ ባሽ ብዙቅ ነበርና ትግሬን ሁሉ እስከ አሸንጌ ድረስ ያዘ፡፡ መቀሌ ላይም ብርቱ ምሽግ ሰራና ብዙ ጦር አስቀመጠ፡፡ ይሄ ሁሉ ሲሆን አጤ ምኒልክ ቶሎ ወደ ትግሬ ለመምጣት አልተቻኮሉም፡፡ ዝግ ብለው ብቻ ጦርነታቸውን ሁሉ ያሰናዱ ጀመረ፡፡.. ከሁሉም በላይ ከአላጌ እስከ አድዋ በተደረገው ጦርነት ላይ እነ ራስ አሉላ፣ እነራስ መንገሻ፣ እነራስ ሀጎስ፣ ሌሎችም የትግራይ መሳፍንት ከነሙሉ ጦራቸው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻቸው ጎን ተሰልፈው እንደተዋጉ ልዩ ልዩ የታሪክ ሐፍት አስፍረውታል፡፡ ይህን ሁሉ እኔ ለፕሮፌሰር መስፍን ማስረዳት ነበረብኝ? አገር ጉድ አይልም!
በመሰረቱ አንድን ሕዝብ ከሌላው ነጥሎ ይህ ሲሆን ምን ይሠራ ነበር ብሎ ጥያቄ ማቅረብ ተገቢ ሊሆን አይችልም፡፡ አንድ ሕዝብ በቦታው ሆኖ አመራር የሚሰጥ ሁነኛ መሪ ከሌለው ምንም ማድረግ እንደማይችል የታወቀ ነውና፡፡በዚህ አባባል መሰረት ጎንደር በመሀዲስቶች ስትቃጠል ጎጃምና ሸዋ ምን ያደርግ ነበር ብንል ያስኬዳል? እንዲያ ማሰብ እንደ ፕሮፌሰር መስፍን መሆን ነው፡፡ ቢያንስ የያኔው ንጉስ ምኒልክ የት እንደነበሩ መግለፁ ግን ተገቢ ይመስለኛል፡፡ የታሪክ ምሁሩ ባህሩ ዘውዴ፤ ..የኢትዮጵያ ታሪክ.. በሚለው መጽሐፋቸው ስለዚህ ያሉትን L_qS””|ዮሐንስ ከበታቾቹ ጋር የነበረው ግንኙነት እንዳይድን ሆኖ የሻከረውም በዚሁ ዓመት ነው፡፡ ወደ ሰሓጢ በሚዘምትበት ወቅት ምኒልክ ታማኝነቱን ለመግለፅ ያህል አብሬ ልዝመት ብሎ ካንገት በላይ ጠይቆ ነበር፡፡ ዮሐንስ ለጣሊያኖች እኔ እበቃለሁ፤ አንተ ከጎንደር በስተደቡብ አምባጮራ ላይ ሆነህ የማሀዲስቶችን እንቅሰቃሴ ተቆጣጠር ብሎ መለሰለት፡፡ የምኒልክ የሰሜን ኢትዮጵያ ዘመቻ ጎንደርን ከማሀዲስት መዓት አላዳናትም፡፡ wd ¹ê sþmlS GN ¯©M ¯‰ BlÖ búR W¦ ሽንፈትና በቤተሰቡ የማሀዲስት ምርኮ መሆን ሲበሳጭ ከነበረው ከተክለ ሃይማኖት ጋር በንጉሰ ነገስቱ ላይ ለማመፅ አሲሮ ተመለሰ፡፡ ዮሐንስ ይህን እንደሰማ በጎጃም ላይ ለራሱም የዘገነነውን ፍጅት ዐወጀ፡፡ የሚቀጥለው ዒላማው ሸዋ ነበር፡፡ ምኒልክም ነገር መክረሩን ሲያውቅ ጣሊያኖች በመሳሪያ እንዲያግዙት ተማጠነ፤ የሸዋ ህዝብም ለክብሩና ለነፃነቱ እንዲጋደል ክተት ዐወጀ፡፡ ኢትዮጵያ ከርስ በርስ ጦርነት ጫፍ ላይ ተንጠለጠለች፡፡ በመጨረሻ ግን ዮሐንስ ሐሳቡን ለውጦ ጦሩን ወደ ማሀዲስቶች አዞረ፡፡
በየዋህነት ፕሮፌሰር ለዚሁ የብዕር ወለምታቸው በይፋ ይቅርታ ይጠይቁ ይሆናል ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ አሁን ግን ጠረጠርኩ፡፡ አቦይ ስብሀት ከመስፍን ጋር ጓደኛሞች ነን ያሉት ነገር እውነት እንዳይሆን! ምክንያቱም አብዮታዊ ዴሞክራሲን እንደ ርዕዮተዓለም የሚከተሉ ሰዎች ቢያጠፉ እንኳ ጥፋት መሆኑን እያወቁ  ይቅርታን መጠየቅን እንደ ነውር ይቆጥሩታል፤ ስለዚህ ቢሞቱ ይቅርታ አይጠይቁም፡፡ በአንፃሩ ሌላው ባይሳሳትም ይቅርታ እንዲጠይቃቸው አጥብቀው ይፈልጋሉ፡፡ ይህን ዓይነቱን ከአቦይ ስብሀት ተምረው እንዳይሆን ሰግቻለሁ፡፡የመጨረሻው መልዕክቴ ለሁለቱም ነው፡፡ ለአቦይ ስብሀት እና ለፕሮፌሰር መስፍንም፡፡ እኛ ከእናንተ መማርና መውረስ ያለብን ዘረኝነትና ጎጠኝነት መሆን የለበትም፡፡ እኛ ከእናንተ መውረስ ያለብን ቂመኛነትንና በቀለኛነትን አይደለም፡፡ አድርባይነትም አይደለም፡፡ እኛ መውረስ ያለብን ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ ሀቀኝነትን ነው፡፡ ደግሞ በምሁርነት ተከልሎ የዘር ፖለቲካ ማራመድ ፋሽኑ ያለፈበት ይመስለኛል፡፡ ከቻላችሁ ደህና ደህናውን አውርሱን፤ ካልቻላችሁ ገለል በሉልን፡፡ የራሳችሁን ጊዜ ጨርሳችሁ የእኛን ጊዜ አታባክኑብን፡፡ እኛ ፅኑ መሰረት ወዳለው ሀገራዊ አንድነት ለመሸጋገር ትግል ማካሄድ አለብን፡፡ አገር ከመፈራረስ እና ከመበታተን የማዳን ተልዕኮ ለዚህ ትውልድ የተሰጠ ዕዳ ነው፡፡ እርስ በርስ በዘር ከመጠፋፋት የማዳን ተልዕኮ ያለው በዚህ ትውልድ ትከሻ ላይ ነው፡፡ በሽኩቻ እና እንካ ሰላንታያ ዘመናችንን በከንቱ መፍጀት የለብንም፡፡/አስራት አብርሃም የዐረና ለፍትህና ለሉዓላዊነት ፓርቲ ፀላፊ ከአገር በስተጀርባ እና መለስ እና ግብጽ የተሰኙ ሁለት መጻሕፍት ፀሐፊ ናቸው/

 

Read 3943 times Last modified on Saturday, 10 September 2011 11:57