አማራ ባንክ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ አክሲዮን ለመግዛት የሚያስችለውን ስምምነት የፈጸመ ሲሆን፤ የ10% አክሲዮን ድርሻ ገዝቷል፡፡
የአማራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ተወያይቶ ባፀደቀው መሠረት፣ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ በመመደብ የአክሲዮን ድርሻ የገዛው ባንኩ፤ ሲሆን፤ ይህም በገንዘብ ሲተመን 90.6 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተገልጿል።
አማራ ባንክ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገትና ለህዝብ ኑሮ መሻሻል ጉልህ አስተዋጽዖ ከሚያደርጉ ተግባራት ጀርባ ሆኖ መገኘት መገለጫው እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይ ገበያው ጠንካራ ሆኖ እንዲቋቋምና ሀገራዊ ተልዕኮውን በብቃት መወጣት እንዲችል፤ አሠራሩ ቀልጣፋና ዘመናዊ እንዲሆን ብሎም የታሰበለትን ግብና አላማ እንዲያሳካ ባንኩ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ተባብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።
Friday, 29 March 2024 21:06
አማራ ባንክ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የ90.6 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ድርሻ ገዛ
Written by Administrator
Published in
ዜና