Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 03 September 2011 12:21

የኖኅ ኅልውና በጊልጋሜሽ ይፈተሽ?

Written by 
Rate this item
(0 votes)

መቅድመ ነገር
የአምስት ሺ ዘመን ታሪክ ለኢትዮጵያ የቆጠራላት ጋዜጠኛ ፍሥሐ ያዜ ያቀረበውን መጽሐፍ ለመተቸት ዓለማየሁ ገላጋይ በአዲስ አድማስ ያቀረበውን ጽሑፍ ደግሜ ደጋግሜ አነበብሁት፡፡ ይህን ያህል ማንበቤ በርካታ የሚነቀሱ ነጥቦች በውስጡ ስለተመለከትሁ እነሱን በዓይነት በዓይነታቸው አውጥቼ በያንዳንዱ ረገድ መባል የሚገባቸውን ለመሰንዘር ስል ነበር፡፡ በሚያስገርም መጠን እያንዳንዱ ራሱን የቻለ ርዕስ እስኪሆን ድረስ የሚሄድ ሆነ፡፡ እንዲህ የሆነውን ደግሞ በጋዜጣ ገጽ እንዴት ማቅረብ ይቻላል? ሁሉንም እንዳሉ ከመተው ግን አንድ ሁለቱን ልምረጥ አልኩ፡፡ ስለኖኅ አና ስለንግሥተ ሳባ፣ ዓለማየሁ ያቀረባቸውን ማንሳትን ሊተውት የሚገባ አይሆንም፡፡ሌሎችን ነጥቦች ግን እንዲሁ በጥቆማና በጥያቄዎች በማንሳት ነጥቦቹ እንዲታሰቡ ሳያደርጉ ማለፍን ልቤ እሺ አላለኝምና እነዚያን አነጣጥቤ፣ በዚህ ጽሑፍ ቅድሚያ ከሰጠሁቸው አንዱንና የሚቀድመውን የኖኅ ህልውና እንደ አዲስ እንዲፈተሽ የተጠየቀበትን ነገር እይዛለሁ፡፡

ሎሞን አበበ ቸኮል
ሆነ በሌላው ታሪክ ላይ የተረትና የታሪክ ስም የመለጠፉ ነገርም ዓለማየሁ ካቀረበው በተቃራኒው የሆኑ መሆናቸውን የሚያመለክቱ በዘመናዊ ምርማሮ የተገኙ እየሞሉ ሳለ ምነው በዚያው ብቻ?
•yXWnT ተረት እንደሚባሉት የሆኑ ታሪኮች የሞሉ መሆኑንስ ዓለማየሁ ለምን አላየም? ለመሆኑ ሴሚቲክ፣ ኩሽቲክ፣ ሳባ፣. . . የተባሉ ስሞችን እንደ ስም የቆጠሩት እነማናቸው? ምን ያህል እውነትስ ይሆኑ?. . . ግና ሴም፣ ኩሽ. . . የተባሉትን ስያሜዎች የያዘውን ያደነቀ እንዴት ነው ኖኅ አልነበረም የሚለው?
•ዓለማየሁ ..የታሪክ አባቶች..ና ..የተረት አባቶች.. ብሎ በመመደብ የጠራቸው ታሪክ ፀሐፊዎችና የታሪክ ምሑራን ጉዳይም የሚያጠያይቅ ነው፡፡
•..የተረት አባቶች.. ብሎ ከዘረዘራቸው ውስጥ አብዛኞቹ ከዘመናዊው ታሪክ መርማሪዎች ወገን ለመቆጠር ወይም ለመስማማት ሲሉ አጉል የሆነውን ያቀረቡ፣ በቀጥታ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሥራ ከሌላው ዓለም ባለበት ሲፈልጉለት የሚገኙ ሁሉ ያሉበት መሆኑን፣ ..ተረቶች.. የሚባሉትን ትውፊታዊ ታሪኮችንና ትረካዎችን የነቀፉና ያጣጣሉት እንደሆኑ ዓለማየሁ ለምን አላየውም?. . .
•Xn አለቃ ታየ ባቀረቧቸው መጽሐፍስ ..የታሪክ ምሁራን.. ብሎ ካወደሳቸው መካከል የመግቢያ ጽሑፍ የጻፉም መኖራቸውም ማየት ጥሩ ነው፡፡
• የታሪክ ምሑራን ብሎ በስም ከጠቃቀሳቸው አብዛኞች በሌሎቹ ምሑራን ጽሑፎችና ሥራዎች የተመሠረቱባቸው መነሻዎቻቸው ጭምር ተረት ተረት እየተደረጉ የተገለጡ መኖራቸውንስ ምን ያህል ይታወቃል?. . . ..ሻተሪንግ ዘሚዝ.. ተብሎ የቀረበ አንድ አሜሪካ ውስጥ የቀረበ ታሪካዊ ወረቀት ብቻ ..ሂስትሪ.. ተብሎ ዛሬም ድረስ በየት/ቤቱ በየመጻሕፍቱ የሚቀርቡትን የነዚህን ሰዎች ሥራዎች ምን ያህል እንደፈረካከሷቸው ምን ያህል ይታወቃል?
• ..ሂስትሪ.. የተባለውም ራሱ ከፈጠራ ተረትነት ያልፀዱ ብዙ መሠረታዊ ጉዳዮች የያዘ መሆኑንም ሊጠየቅ ይችላል፡፡ ለምሣሌ፣ ዓለማየሁ ..ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት.. ብለው የጠሩትን በመቀበል የተጠቀመበትን የመሰለው ተረት ከሚባሉት እንዴት ሊወጣ ይችላል?
• ከዚህም የተነሳ በዓለማየሁ ..የታሪክ ምሑራን.. ተብለው ከተቆጠሩት መካከል በቀጥታ Ill educated Scholars” (የቅኝ ገዢዎችን ሃቅ አልባ ጠማማ ትምህርት ይዘው ..ታሪክ.. ብለው የሚያስተምሩ፣ በላዩ ላይ የሚከማምሩ) እንደሆኑ የተገለፀባቸው መኖራቸውስ ምን ያህል ይታወቃል?
• የኢትዮጵያ ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ በፊት ከ200 ዓመት በፊት ብዙም የማስረጃ መሠረት የለውም እንደተባለም በዓለማየሁ ጽሑፍ ተገልጿል፡፡
• በሌሎች ዘመኖች ያለውን ትክክለኛ ታሪክ ያህል የማይጠፋባቸው፣ ሊበልጡም የሚችሉበት ዕድል ያልጠፋ ቢሆንም በማይገባ መሠረት ላይ በገዢዎች ተሠርቶ ታላላቅ የታሪክ ሥራዎችን ሁሉ በስም ብቻ እየጠራ ማጣጣልን የመሰለ የቀለለ ሥራ እያለ ማን ሩቅ ይሂድ? ይህም ሆኖ እንዲያ የሚባልም አይደለም፡፡ እዚያው በዓለማየሁ ጽሑፍ ውስጥ፣ ከዚህ ወረድ ብሎ ከ200 ዓመት በፊት የነበረችቱን ንግሥተ ሳባን ተረት አካለ ለማድረግ (እንደብቸኛ ትልቅ ማስረጃ) ያኔ አክሱም ያልነበረች መሆኑን የመሰለውን ታሪክ አስረግጠው የገለፁበትን ጠቅሷል፡፡ ከዚያ ዘመን በፊትም ሆነ ከዚያ ዘመን ወዲህ፣ /ዓለማየሁ በበኩሉ ደግሞ (በሚያሳዝን ጥቅሻ)/ ከ13ኛው መቶ ዘመን ወዲህ ነው ..ታሪክ.. የሚባል ታሪክ ያለው ወደ ማለት ሲያጓድል ይታያል፡፡ ከዚያ ወዲህም ቢሆን ..እኩል.. ሊባል የሚበቃ መረጃ አላቸው ተብለው የሚነገሩንን ታሪኮች በሚቀልበን ትምህርት በኩል ታስቦ የኖረው፣ በቀላሉ 500 ዘመን የተቆጠረለት ሰው ዓላማ አይገኝምና ያን ያህል ሩቅ ዘመን አይኬድም፡፡ ያን ያህል ግን የለም የሚባል አይደለም፡፡
• አንዱ ካንዱ እየተደራረበ ከጥቆማም ያለፈብኝን ይህን በዚህ ላቁምና የኖኅን ..ህልውና ፍተሻ.. በተባለው ሐሳብ ዙሪያ የቀረቡትን መመልከት ልጀምር፡፡
በዓለማየሁ ጽሑፍ የተጠሩትን ኖኅንና ንግሥተ ሳባን ርዕሰ ጉዳይ አድርጐ ማንሳቱ ከላይ ከተጠቃቀሱት መካከል አንዳንዱን በተዘዋዋሪ ማሳየት
ስለሚችሉ፤ በዓለማየሁ በኩልም፣     እነዚያን (የላይኞቹን) ለማስረገጥም የረዱ ሆነው በመቅረባቸውና በእነዚህ ሰዎች የተጠቆሙትን ጉዳዮች መግለጽና ውጥረት የሚገባቸው ነገሮች መኖራቸው. . .፤ (ለዛሬ ግን ሁለቱንም አንዴ ማቅረብ እንደማይቻል በመገንዘብ፣ ቀዳሚውን በማቅረብ የሌላውን ጊዜ ደግሞ እንዲሁ በማሰብ እንድናቆየው መረጥሁ፡፡) እና ስለኖኅ በዓለማየሁ ገላጋይ የተገለትንና ረግጦ የደመደመበትን፤ እንዲሁም፣ ተያይዘው ..አዙሪታም ተረት.. ተብሎ በተጠራ ጉዳይ የተጠየቀውን ማነሳሳት እሞክራለሁ፡፡
በመጀመሪያ የኖኅን ሕልውና እንፈትሽ እንፈትሽ ዘንድ በማሳሰብ ..ለመሆኑ በዚች ምድር ኖኅ የተባለ ሰው ነበረ ወይ?.. ብሎ ይጠይቃል፡፡
ወደዚያው ደሞ፣ ..ብቸኛው ማስረጃ በብሉይ ኪዳን የተካተተው ታሪኩ ብቻ ነው?.. ይላል፡፡ ለኖኅ ያለው ..ብቸኛው የጽሑፍ ታሪክ..!
..የብሉይ ኪዳን.. ብሎ የጠቀሰው ደግሞ በግልጽ የኦሪቶች ላይ የተጻፈውን የጥፋት ውኃ ታሪክ ነው፡፡ አንድ ዓቢይ ማጣጣያው ደግሞ የዚህ ታሪክ ፀሐፊ ሙሴ መሆኑንና የመጽሐፉን ስም ጠርቶ ባቀረበው ይታወቃል፡፡
..የዘፍጥረቱ ኖኅ ከዚህ ጀብዱ ግጥም (ከጊልጋሜሽ) በፀሐፊው (በሙሴ) የተቀዳ እንጂ በሕይወት ያልኖረ ሰው (ነው).. ይላል፡፡ ከዚህ ሌላም፣ በቀጥታ ስሙን ጠርቶ ..ሙሴ የኖኅን ታሪክ ከመጻፉ በፊት፣.. እያለ ጽፏል፡፡ በቀጥታ የኖኅ ታሪክ በኦሪት ዘፍጥረት ብቻ የሚገኝ ታሪክ እንደሆነ በመያዝ ነው ሕልውናው የተጠየቀው፡፡
ኖኅን ያላወቁት ኦሪት ዘፍጥረት ወይም ሌሎቹ የሙሴ መጻሕፍት ብቻ ናቸው! የዓለማየሁ ጥቆማና የደረሰበት ድምዳሜ ስህተት ከዚህ ልክ ያልሆነ መነሻ ይጀምራል፡፡
ከመጻሕፍቱ ውስጥ ቀድመው የተጻፉትም ወይም የተደረሱት እነዚህ የሙሴና ኦሪቶች ተደርገው መታሰቡን የመሰለ ዓለም አቀፋዊ ግንዛቤውና ከዚህ ተነስቶ የሚያንደረድሯቸውና የሚደርሱባቸው ነጥቦች ምንኛ ወልካፋ እንደሆነም እናይበታለን፡፡ ያን በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለፀ የአንድ አምላክ እምነት ..ጁዳይዝም.. ብሎ መጥራቱም ሆነ እምነቱም የእስራኤላውያን ብቻ መደረጉ፣ ከነዚያ ጋር የተስማሙ ባህሎችንም ከእስራኤል የተኮረጁ ማድረጉ ሁሉ፤ እንዲህ መጽሐፎቹ ሁሉ በሙሴና ከሙሴ ወዲህ ብቻ የተጻፉ ማድረጉን ከመሰለው ትልቅ ስህተት የመጣ ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ መጻሕፍት ውስጥ ቀድመው የተደረሱትና የታወቁት ብሔራነ ኦሪቱ ሳይሆኑ መጽሐፈ ሄኖክና መጽሐፈ ኢዮብ የተባሉት ናቸው፡፡ ስማቸው ለመጻሕፍቱ መጥሪያ የሆኑላቸው ሄኖክም ሆነ ኢዮብ ከሙሴ ዘመን ብዙ መቶዎች ዓመታትን የቀደሙ ናቸው፡፡
ስለኖኅም የሚናገረው መጽሐፍ፣ በስሙ የተጠራበት ሄኖክ በተለይ ከሙሴ ጋር የ42 ትውልድ ርቀት ያለው ነው፡፡ የሙሴን ትተን ከራሱ ከኖኅም ሆነ ከጥፋት ውኃ በፊት የኖረ ሰው ነው፡፡ እንዲህ በቀደመው ሰው ድርሰት ውስጥ ታዲያ ኖኅም ሆነ የጥፋት ውኃው ጉዳይ ተነስቷል፡፡
የራሱ የሙሴ ድርሰቶች ከሆኑት እንኳ ከኦሪት ዘፍጥረት ይበልጥ ለታሪክ በሚመችና የዘመን ቅደም ተከተልና በበለጠ ገለጻ ዘርዘር ብሎ ስለኖኅና የጥፋት ውኃው የቀረበው በኩፋሌ መሆኑም ቢታሰብ እንኳ ..ኖኅ የዘፍጥረቱ.. ብሎ ለመጥራት ያበቃውን ብቸኛው ምንጭ አድርጐ ለማሰብ ባልተቻለም ነበር፡፡ የኖኅን ታሪክም ይሁን የጥፋት ውኃን ከነዚህም በላይ በሚገባ ከልደት እስከ ዕለተ ሞት ድረስ፣ የወላጆቹን ማንነት (የናቱን)፣ የሚስቱን፣ በዘመኑ የነበሩት ሰዎችና ኑሯቸውን ሳይቀር፤ ያ ጥፋት በሆነ ጊዜ የሰውን ሁኔታ አይቶ የዚች ምድር ነገር አስደንግጦት ለራሱም ፈርቶ አቤት ማለቱን. . . (እንቀጥል?) እንዲህ በዝርዝር እንዳሉ ቢገለጽ ምን ይሆን የሚባለው?
የሚገርመውም ይህ ነው! ኖኅ የተባለውን አንድ ሰው ከሕፃንነቱ ጀምሮ ይበልጥ የሚያነሱትና የሚያሳውቁት ሌሎች መጽሐፍትም መኖራቸው! ሌሎቹን ትተን ከመጽሐፍ ቅዱስ ሄኖክን ብቻ ብንይዝ ..በብሉይ ኪዳን ውስጥ በሙሴ ዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ ብቻ ነው የኖኅ ታሪክ የሚገኘው..፣ የሚለው ቀዳሚ ነገር በዓሌክስ ምልክት ውድቅ ያደርገዋል፡፡
በ1556 ዓ.ዓ. በኛ ጥር 27 (ከልደት በፊት 3945) ላይ ኖኅ ሲወለድ፣ በመልኩም ልዩ ሆኖ በመፈጠሩ፣ አባቱ ላሜኅ ደንግጦ ነበር፡፡ ጭራሽ ተረብሾ ወደ ራሱ አባት ወደ ማቱሳላህ ሮጠ፡፡ ..ኧረ ሂድና ያን ሄኖክን የዚህን ልጅ ነገር (እንደልማድህ) ጠይቀው?.. ብሎ እስከ መናገር ደረሰ፡፡ ይህን ገና ከማኅፀን ብቅ ባለበት ጊዜ የነበረውን ነገሩን በመጽሐፈ ሄኖክ ነው የምናገኘው፡፡
ሄኖክም ሆነ ድርሰቱ ከጥፋት ውኃ በፊት የነበሩ እንደመሆናቸው፣ ያን ጊዜ ወደ ጥፋት ውኃው ያመራ የነበረውን ሕዝብ ጉዞም ሳይቀር፣ በግልጽና በዝርዝር የሚተርኩም እነኚሁ ሄኖክና መጽሐፉ ናቸው፡፡ ስለጥፋት ውኃ ኖኅ ሳይወለድ በፊት ሄኖክ እንዲህ ሲል በትውልድ ቁጥሩ መናገር የጀመረበት በመጽሐፉ መነሻ ላይ ይገኛል፡፡ ..ነገር ግን ይህ የሚሆነው በኔ በሰባተኛው ትውልድ ሳይሆን በዐሥረኛው ትውልድ ነው.. ይላል፡፡ እንዲህ አስቀድሞም በሌላ መጽሐፍ መነገሩን ሁሉ ቢያውቁት ስለጥፋቱ ውኃ ታሪክም ሆነ ስለ ኖኅም ያለውን መጽሐፋዊ መረጃ አንድ በማድረግ እንዳለ የሰውዬውን ሰውነት ውድቅ ለማድረግ ማመቻቸት እንደተያዘ እናስተውል፡፡ ቀሪው ስለጉዳዩ እናገር ባይ ይህን እንዲሁ ይዞ ሲያጣጥል መኖሩ ይታወቃል፡፡ ግና ሌሎች መጽሐፍትን ለማጣት ለመፈለግ ባለመሻት እና በመሳሰለው ጐድሎበት ቀረ፡፡ ኢትዮጵያንና የመሳሰሉት ግን ስለኖኅ ስለጥፋት ውኃ ብዙ የተጻፉ ነገሮች አሏቸው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ በዕለት ተዕለት ሕይወት እየተፈሙ ሲገኙ በልቦና የተከተቡ ብዙዎችን ሊያስገርሙ የሚችሉ ኖኅዊ ውርሶች ሁሉ ሞልተዋል፡፡ ቀዳሚውና ብቸኛው ጽሑፋዊ አብነት የሙሴ ነው ብሎ ለቀጣይ ሐሳብ የተመቻቸ የተደረገበትን ነው እንግዲህ ዓለማየሁም ይዞ የተነሳው፤ ግና ይኼው ሌሎች መጽሐፍት መኖራቸው በመጠቆሙ ብቻ ..የዘፍጥረቱ ኖኅ.. ብሎ የጠራበትን እንዳለ ያነሳዋል፡፡ ባያነሳው ሌሎቻችን ያን መነሻውን ጥለን ማለፋችን አይቀርም፡፡
..መደንፊያ የእውነት ቀስት..
..ከእምነቱ ባሻገር.. ያለውን ሌላ ከኖኅ የሚጠጋጋ ነገር ለመጠቆም ደግሞ ዓለማየሁ ወደ ከርሰ ምድር ምርማሮው ይሄዳል፡፡ ከኖኅ መርከብ ጋር የተነካኩ ግኝቶችና ለፍለጋው የተደረጉ ጥረቶች አንድ ሁለት የሚባሉ ቢሆኑም፤ አንዱን ብቻ ያቀርባል፡፡
..በ1955 ፈረንሳዊው ፌርናንድ ናባራ 3 የመርከብ ስብርባሪዎች አግኝቶ ሳይንስ ግን የኖኅ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ አጥሮት እስካሁን ነገሩ በእንጥልጥል ይገኛል፡፡.. እንዲህ ሳይንስ የተባለው ሳይንስ ..ማረጋገጫ.. አጠረው የተባለው ታዲያ እነዚያ ስብርባሪዎች በሳይንሳዊ ዕድሜ ግመታው 5000 ዓመት እንደሚሆናቸው ከተገለጠም በኋላ ነው፡፡ ልብ በሉ!
ከዚህም ጋር ብርቱ ኃይል ያለውን ቃሎች በመጠቀም ተከታዩን ድምዳሜን አስነብቧል፡፡
..የከርሠ ምድር ጥናት ሁሉ መደገፊያ የእውነት ቅስት እያጣ አልቆም ብሎ በመውሸልሸል አስቸግሯል፡፡.. ግሩም ነው! እስኪ በቅድሚያ አርኬዎሎጂያዊ ምርምሮች ለማድረግ የተደረጉት ሙከራዎችም ይሁኑ ግኝቶች የናባራው ብቻ ነው ወይ ብለን እንጠይቅ፡፡ ብዙዎች የሰሟቸው ሌሎች እንዳሉ ለምን አልተጠቆመም?  
የፌርናንድ ናባራ 3 እንጨቶች በአካባቢው ከተገኙት አንደኛው፤ ሊገኙ ከተሞከሩባቸውም ጥረቶች አንዱ ነው፡፡ ናባራ የኖኅ መርከብ የሚባል ነገርን ከእምነታዊ መጽሐፍ ባገኘው መሠረት፣ በአካባቢውም በትውፊት የሚጠቆሙ ቦታዎችና ታሪኮችን ሁሉ በመያዝ የከርሰ ምድር ቁፋሮ ያዘ፡፡ (ለምሳሌ፣ የኖኅ ባለቤት መቃብር አለበት ተብሎ ዛሬ ድረስ የሚጐበኝ ቦታ ሁሉ ይታወቃል)
የተገኙ የመርከብ ስብርባሪዎች ግን ናባራ ያገኛቸው ብቻ አይደሉም፡፡ አሁን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሌሎች እንደተገኙ በተለያዩ የዜና አውታሮች ከተገለፀው ጋር አስቀድሞ በንዝህላልነት መልሰው ካጧቸው የሩስያ አርኬዎሎጂስቶች ጥረቶች ጀምሮ በርካታ ሙከራዎችና ሥራዎች ተፈጽመዋል፡፡ ታዲያ ብዙዎቹ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ፣ የዘፍጥረቱም ታሪክ ቢሆን በትክክል እንደሆነ አምነው፣ ፍለጋ በወጡ ሰዎች የተደረጉ ነበሩ፡፡ ጥሩ ማስረጃ ቢሆኑን ከእነ ኒል አርምስትሮንግ ጋር በአፖሎ ፕሮጀክት የታወቀው የኤድዉንን ፍላጐት እንጥቀስ፡፡  
ጨረቃ ላይ እግራቸውን ካሳረፉት ሰዎች አንዱ የነበረው ኤድዊን እዚያ ጨረቃ ድንቡልዕቃ ላይ ሳለ፣ ይቺን ምድር አንጋጥጦ ሲያያት፣ አንዲት በቀላሉ ኳ-ኮርኳ-ክርክሽ-እንቅሽ በተቀበለውና በወሰነው ውሳኔ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ውስጥ የተጠቆሙ ዓለም ዓቀፍ ቅርሶችንና ቦታዎችን ፈላጊ ትልቅ ድርጅት ለመመስራት ቻለ፡፡ የመጀመሪያው ፕሮግራሙም የኖኅ መርከብን ፍለጋ አድርጐ፣ ብዙ ወጭ ያደረገበትን ቁጥር አንድ ፕሮጀክቱን ሊከውን ወደ ቦታው ጓዙን ጠቅልሎ ተነሳ፡፡ እርሱና ከርሱ ጋር የነበሩት የባለሞያዎች ቡድን በቱርክ መንግሥት የሰላይ ቡድን ተብሎ በመያዙ ሳይሳካለት ቀረ፡፡
ባይሳካለትም የኖኅ መርከብ ፍለጋን የተነሳው፣ ያንኑ ብቸኛ የተደረገውም ጽሑፍ የተነገረው ተይዞ ነበር፡፡ (ከዚያ በኋላ ያቋቋመው ድርጅት ያንኑ ዓላማውን ጠብቆ ደብረሲና የት እንደምትገኝ፣ እንዲሁም ከሲና በሙሴ እጅ የወረዱ ጽላቶች የት እንደገቡ በመፈለግ ግኝቱን ለመላው ዓለም አሳውቋል፡፡ በአማርኛም ቀርቧል፡፡)
ወደ ኋላ እንመለስና አንድ ብቸኛ ግኝት ተደርጐ መቅረቡን ታዝበን እንለፍና፣ ያውስ ብቻ ቢሆንስ? ብለን እንጠይቅ፡፡
ዓለማየሁም ሆነ ሌላው ግኝቶችን ..የእውነት ቅስት.. ለመሆን አቅም የለሽ የማድረጋቸው ምክንያት ብዙ ጊዜ የሚያጋጥም የተለመደ ምሑራዊ አቋም ሆኖ መኖሩን ነው፡፡
ናባራ የመርከብ እንጨቶችን አገኘ፡፡ ዕድሜያቸውን አስለካ፡፡ በሰፊው ግምትን በሚያቀርበው ሳይንሳዊ ዕድሜ ትመና አምስት ሺ ዓመታት አስቆጠራቸው፡፡ ታሪኩ ከቤተ እምነትና ከትውፊት የተገኘ ነውና በአንዳንዶች አሁንም ሌላ ማስረጃ ካልቀረበበት በቀር የዚህ ግኝት ዋጋ መቼም ቢሆን ይሄው ነው፡፡ በቂ ማረጋገጫ አይደለም፡፡
መርከቡ በተራሮቹ አናት ላይ በተአምር ድንገት ፍጥጥ ብሎ ቢታይ እንኳ የኖኅን ኅልውና ለማስረገጥ ይችል ይሆን? ብለን ስንጠይቅ ነው ጉዳዩ ሌላ መሆኑን የምናጐላው፡፡ በአጠቃላይ የከርሰ ምድር ማስረጃ ነገሩ በራሱ በዓለማየሁመ እንዲያው ወግ ሆኖ መጠቀስ ስላለበት የቀረበ ነውና፣ ቢገኝ ባይገኝ ከኖኅ ህልውና ጋር ያለው መያያዝ ልል ስለሆነ ሌላ ..ቅስት.. መኖሩንም ቢሆን በዚሁ እንለፈው፡፡
እነኝያ የናባራ ሦስት ሳንቃዎች ብቻ አለመገኘታቸውን ጨምረን፣ እነዚያም ቢሆን ከነዕድሜ ተመናቸው ጋር በጠቆሙት ግንዛቤያችን እንለይ፡፡
ጊልጋ ሜሻዊው TRKT-
ነባሩ ኖኅዊውን የጥፋት ውኃ ታሪክም ሆነ ኖኅ የተባለውን ሰው እንዳልነበረ ማድረጊያው የሱሜሩን ጊልጋሜሽ ትረካ ነው፡፡ ዓለማየሁም ይህንን አጥብቆ ይዟል፡፡ በአራራት ተራሮች የተገኙ የመርከብ ስብርባሪዎች የኖኅ መርከብ እንዳይባሉ የተበረታውን ያህል፣ የጊልጋሜሽ ታሪክ የኖኅ ታሪክ ምንጭ እንዳይባል የሚያበረታውን ለማሰብ ጊዜ የለም፡፡ በአንዴ ነው ዥው ብለው ከዚህ ሐሳብ ጋር ልብ የሚቀልጠው፡፡ ከዚያ ..የኖኅ ታሪክ አስቀድሞ ከተተረከው ከጊልጋማሽ ትረካ የተቀዳ ነውና፣.. ብሎ መያዝ፣ ለሌላውም መንገርና ማወጅ፡፡
ለዚህ የሚያበቃቸው አንድ ምክንያት ይኖር ይሆን? ትንሽ እንኳ ሊያሳምንላቸው ይችላል የሚባለው የታሪኩ መቀራረብ አይደለም፡፡ ትልቁ ሀቅ ሆኖ የሚቀርበው ሙሴ ከጊልጋሜሽ በኋላ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ ከጊልጋሜሽ በኋላ የነበረው ሙሴ ኦሪቱን መጻፉ ነው፡፡ (ያ ብቻ ነው ያለው ብቸኛ የመጽሐፉ ኖኅን ጠቃሽ ክፍል ተብሎ አስቀድሞ ተደምድሞ የለ?) ዓለማየሁም፣ ..ሙሴ የኖኅን ታሪክ ከመጻፉ በፊት ጊልጋሜሽ 1000 ዓመት ስለሚቀድመው፣.. በማለት ነው የገለው፡፡ በራሱም ቃል ሙሴን የጊልጋሜሽ ኮራጅና ጊልጋሜሻዊውN ታሪክ የእስራኤላዊነት ቅብ ቀቢም ያደረገው በቃ በዚችው ነው፡፡
ልብ በሉ! ይህ መቀዳደም ቅቡል ሊሆን የሚችለው እኮ የኖኅን ነገር የያዘውና የጻፈው ሙሴ ብቻ ቢሆን ነበር፡፡ እነ ሄኖክ ጽፈውት ሲገኙስ ምን እንበል? እነ ማቱሳላህና ላሜህስ ያን የጥፋት ውኃና ተያያዥ ነገር በሄኖክ ትዕዛዝ እየጻፉ እንዲያኖሩት ሲነገራቸው ካገኘንስ? ያን የጥፋት ታሪክ እነሱም አስቀድመው ተናግረውት ነበር፡፡
ከመሠረቱ፣ በኖኅ ዘመን የሆነው የጥፋት ውኃ ታሪክ፣ በሰዎች ዘንድ ትልቅ ጥላ ትቶ ያለፈ፣ በቶሎ ከተረፉት ሰዎች አዕምሮ ሊወጣ ሊፋቅ ያልቻለ ታላቅ ነገር እንደነበር የሚያስገነዝቡ የመጽሐፍ ጥቆማዎች ያሉት ጉዳይ ነበርና እንዲህ በዋዛ የሚረሳ አልነበረም፡፡ በአፍም በመጣፍም ሲወርድ የነበረ እጅግ ዘግናኝ የምድሪቱ ታላቅ የጥፋት ክስተት ነበር፡፡ የምናውቃቸው ሱናሚዎች ሁሉ ተደምረው የማይመጥኑት ነበር፡፡ በቃል በጽሑፍ የታወቀው፡፡
ጊልጋሜሽን የመሰሉ፣ ከኖኅ ዘመን ሺ ዓመት ቆይተው የነበሩት በተለያየ መልክና ቅርጽ ሰጥተው ሊተርኩት እንደሚችል እንኳ ትንሽ ሊታሰብ አይፈልግም፡፡ ይኸው እኛም እኮ ያዝነው፡፡ ታዲያ በአፍም በመጣፍም ቢቀባበሉት ያን ያህል እንግዳ ነገር የማይሆን ነበር፡፡
የጊልጋሜሽ ትርክቶች ደግሞ ለየት የሚልበት አንድ ቁልፍ ጉዳይ ያለው ነው፡፡ የአጋንንት መናፍስታዊ ኃይልን የያዘ ትረካ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በሃይማኖት ውስጥ ያሉ ብዙ ትውፊቶች ላይ ሁሉ ጐን ለጐን ተዛምዶ፣ ተምታቶ፣ እንዲታዩ ተደርገው የሚገኙ፣ አንድ ሺ አንድ የሆኑ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ተለይቶ የማይታይ ነው፡፡ ታሪኮች፣ ስሞች፣ ሁሉ አንድ መስለው የሚገኙባቸው በሁለት ተጻራሪ ሆነው በሚያዙ አምልኮዎች ዘንድ ካሉ ጉዳዮች ጋርም ሊታይ የሚችል ነው፡፡
ዋናው መሟገቻው ግን ወዲህ nW-
•ሙሴ በጊልጋሜሽ ሺ ዓመት ይቀድማል፤ ትክክል!
•SlzþH ሙሴ ከጊልጋሜሽ ኮርጆ የኖኅን ታሪክ ጻፈ፡፡ ምን የሚሉት ሕፀ አስተውሎት (fallacy) ይሆን? - ይህ በሎጂክስ ምን ያህል ያሳምናል? ይህ ካሳመነ ደግሞ የሚከተለውስ አያሳምንም?
•ሙሴ ከጊልጋሜሽ ሺ ዓመት ይቀድማል፤ ትክክል!
•SlzþH# ጊልጋሜሽ ከኖኅ ታሪክ ኮርጆ ታሪኩን ጻፈ፡፡. . . (ምን እንበል?) ወጣም ወረደም ጉዳዩ በምሥራዊው ዓለምና ጭንቅላት ምን ያህል አድሎዓዊነት፣ ችኩልነት፣ ኢተጠየቃዊነት ያለባቸው ሀሳቦች ለብየናና ለድምዳሜ እንደሚያበቁ ቁልጭ አድርጐ የሚያሳይ ነው፡፡
•ጊልጋሜሽም ቢሆን ከነዚያ ቀዳ ለማለት እንደምንችል ከመጠየቅም በላይ፣ መቀዳደም ከሆነ፣ አስቀድመን እንዳየነው፣ ጊልጋሜሽም ተቀድሟል፡፡ ጊልጋሜሽ ከሄኖክ ጠባው እንበል?
የውኃው ታሪክ ከነአስጨናቂነቱ ሲያስበረግጋቸው እንደኖሩ በርካታ ሌሎች የትውፊት ማስረጆችን ማምጣት ይቻላል፡፡ ከራሱ ከኖኅ ጀምሮ ዛሬ ድረስ መባቻዎች (ካላንዴስ) የምንላቸውንና ተያይዘው የሚቀርቡ ሌሎች የሰዎችን ሥርዓት፣ በየወንዙ የሚደረገው የአምልኮ ልማድ ሁሉ ከዚያ የጥፋት ውኃ የሚደርስ ነገር የሞላው ነው፡፡ ምን ያህል ጫና እንደነበረው ለመጠቆም ያህል ያልተሰማች አንዲት ታሪክ ራሷ መጣች፡፡ ከኢትዮጵያውያን ትውፊት የተገኘች፣ ሙሪታንያ (ሞሪታንያ) ከተባለች አገር አመሠራረት ጋር የተያያዘች ነገር ናት፡፡ ሞሪ-ሳቢ በተባለው የኩሽ ልጅ - ልጅ - ልጅ ዘመን የሆነ ነበር፡፡ በአፍሪካ ዱር ምድር አገርን እንዲያቀኑ የላካቸው ልጆቹ፣ በአባታቸው በሞሪ ስም አገርን አቀኑ፡፡ በተራራው ላይ (ሞሪያ ባሉት) ታዲያ የዚያን አጥፊ ውኃ የመሰለ ጥፋት እንዳይመጣብን ብለው ልዩ የአምልኮ ልማድን አምጥተው የየአሙን አጥንቶች ሰብስበው ይለማመኑ ነበር፡፡ እነዚህ ልጆች (ትውልዶች) በዚያ ጊዜ አልነበሩም፡፡ ከኖኅ ኋላ ወደ 25 እና በላይ ትውልድ ያህል በቆየ ጊዜ የሆነ ነበር፡፡ ጊልጋሜሽ የነበረበትም ወደዚህ ይጠጋል፡፡
ይህ እንግዲህ የዚያን ጥፋት ጥላ ምን ያህል እንደነበር ያሳያል፡፡ እንዲህ ወርዶ የደረሰውን ሊፈው ቢችል ለማን ያውቃል?
በኖኀኀ ዘመን እስራኤላዊ?
ዓለማየሁ ከኖኅ ተጀምሮ መተረኩን ይዞ፤ እስራኤላዊnTN በኖኀኀ በኩል ለማግኘት የተደረገ ጥረት አድርጐ መቁጠሩ ደግሞ በጣሙን አስቂኝ ነገር ነው፡፡ ..እስራኤል.. የሚባል ነገርም ይሁን ስም በኖኀኀ ጊዜ ነበር ወይ? ኖኅንስ እስራኤላዊ ያለውስ ማነው? ኖኅ እኮ ኢትዮጵያዊ፣ እስራኤላዊ ማለቱ ሳይጀመር የኖረ አንድ የጋራ አባት ሆኖ ነው የተጻፈው፡፡ የሁሉም የሰው ዘር አንድ አባት ሆኖ ነው የሚታወቀው፡፡ አዳም እስራኤላዊ ነበር? እንደዚያ ነው፡፡. . . ተራ የሆነ ነገር ግን የብዙ ተማሮች ነገር ሆኖ እየተያዘ የሚኖር ችኩል ድምዳሜ! እስራኤል የሚል ስም የተሰጠው ከኖኅ በኋላ ሃያ ሁለተኛ ትውልድ ለነበረው ያዕቆብ ሆኖ እያለ፣ ከኖኅ ጋር የሚያገናኘው |እስራኤላዊnTN ዘር ለመቁጠር ነው.. ሲባል መገኘቱ ከማሳቁም ጀርባ ክፉኛ ነክቶ፣ የኛ ነገር እንዲህ ባሉት ሁሉ እየተያዘ እስከ ምን ድረስ እንደምንሄድ አሰብ ያስደርግና ያሳዝናል፡፡ በመሠረቱ መቼም ቢሆን ኢትዮጵያውያን እስራኤላዊnTN ለመቁጠር የሚጥሩ ሰዎች የመደረጉ ነገር ፈጽሞ ሐቅነት የሌለውና ለዚህ የሚያበቁ ቃሎችንና ሐሳቦችን በሚገባ ካለማወቅ፣ ታሪኮችንም ካለማጥራት የሚሰነዘር እንደሆነ በመጠቆም ብቻ ስለበዛ እንተወው እንጂ፣ እንዲህ ያሉ ያልሆኑ ተረቶችንም ይበልጥ ያናፈሰው ..ታሪክ.. የተባለው ትምሕርት እንደሆነ ቢታወቅስ ምን ይባል ይሆን? ብለን፣ ለባለቀረኙም ዕድል ነፍገን እንሰናበት፡፡ ዋናው ነጥባችንም ተገልል፡፡ የኖኅ ህልውና አጠራጣሪም፣ ጨርሶ ያልነበረም የተደረገባቸው ነጥቦች ተቆጥረው ተነቅሰዋል፡፡

 

Read 2828 times Last modified on Saturday, 03 September 2011 12:27

Latest from