ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ገጼን ሳይ Zerihun Gultie የ1955 ጋዜጣ ለጥፏል። ጋዜጣው ከሚያወሳቸው አንዱ ዜና 785,275 ኪሎ ግራም በቆሎ በ78,267 ብር ለሱማሊያና ለየመን እንደተሸጠ ይገልጻል።
ይህ ሽያጭ እስከ አሰብ የተጓጓዘው በኛ ትራንስፖርት ከሆነ በኩንታል ከብር 30.00 በታች መሆኑ ነው። ያኔ የሀገር ውስጥ ዋጋ በኪሎ ከ0.25 ሳንቲም አይበልጥም ነበር። እንቁላልም በኪሎ ከ1.00 በታች እንደሆነና በ2058 ብር ልዩ ልዩ የተሻለ ዝርያ ያላቸው ከብቶችን ከውጭ አገር ማስገባታችንንና አሜሪካ 225 ግመሎች ማጓጓዣውን ጨምሮ በ5060 ብር መግዛቷን ጋዜጣው ያወሳል።
የብርም ዋጋ ከዶላር በላይ ነበር። ባልሳሳት ያኔ 3USD 1EthD ነበር። ለማንኛውም በቆሎ ለውጭ የተሸጠው በ12 እጥፍ ሲሆ፣ እኔ ሳውቅ በአንድ ብር 100 እንቁላል ስለነበር ብዙ እጥፍ መሆኑ ነው። የምርጥ ከብቶቹንና የግመሎቹን ስሌት ለናንተ ልተወው። በአሁኑ ጊዜ ግን ለውጭ ገበያ የሚቀርበው ከሀገር ቤት ባነሰ ይመስለኛል።
ጋዜጣውን ለለጠፈው ወዳጄ ምስጋና አቀርባለሁ።
Teshome Berhanu Kemal
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

