ወጣት ሰሎሞን አማረ (በማርኬቲንግ ማኔጅመንት የተመረቀ) አዲስ አበባ ውስጥ የሚያበራራትን ሜትር ታክሲ ወደ "ተንቀሳቃሽ ቤተ-መጽሐፍት" በመቀየር አዲስ ፈጠራን አስተዋውቋል።
-
ወጣቱ ከስልክና ማህበራዊ ሚዲያ ሱስ ተላቆ ወደ ንባብ ባህል እንዲመለስ ማስቻል፤ የትራፊክ መጨናነቅን ለንባብ አጋጣሚ መጠቀም።
-
ተሳፋሪዎች በጉዞ ወቅት መጽሐፍትን ያነባሉ፤ ከተመቻቸውም እዚያው ገዝተው ይሄዳሉ።
-
ከትራንስፖርት አገልግሎት ጎን ለጎን መጽሐፍትን በመሸጥ ድርብ ገቢ ያገኛል፤ በቲክቶክ (Sol Books) ገጹም መጽሐፍትን ያሰተዋውቃል።
-
ሌሎች የትራንስፖርት አቅራቢዎችም ይህን አርአያነት ያለው ተግባር በመከተል ታክሲዎችን የዕውቀት ማዕከል እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀርባል።

