Wednesday, 05 August 2026 18:55

"ጥቃቱን ፈጽሞ በመንግሥት ላይ ማሳበብ"፦ በትግራይ የታቀደው የሐሰት ጥቃት ሴራ

Written by 
Rate this item
(4 votes)
የሆርን ሪቪዩ መጽሔት ባወጣው የደህንነት ሪፖርት መሠረት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ አዲስ ግጭት ለመቀስቀስ በህወሓት እና በኤርትራው ህግደፍ አመራሮች መካከል ምስጢራዊ ስምምነት ተደርጓል።
ከሰሞኑ በዛላምበሳ ከተማ በተደረገው በዚህ ስብሰባ ላይ እነ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር (ሞንጀርኖ) እና ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል። የስምምነቱ ዋና ዓላማ በኢኮኖሚ ተቋማት፣ ገበያዎች፣ ሆስፒታሎችና የእምነት ቦታዎች ላይ የቦምብ ጥቃት በመፈጸም፣ ጥቃቱን በፌደራል መንግሥቱ ላይ በማሳበብ ሕዝቡን ለዓመፅ ማነሳሳትና ማዘጋጀት እንደሆነ ሪፖርቱ ገልጻል።
ይህንን እቅድ ለማስፈጸምም የሕዝቡን ስሜት የሚቀሰቅሱ የሐሰት መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨት ተጀምሯል። ሪፖርቱ እንደሚለው፣ በ2020-2022 ጦርነት ወቅት በትግራይ ሕዝብ ላይ ከተፈጸሙት በደሎች 76 በመቶ የሚሆነው በኤርትራ ሠራዊት የተፈጸመ ቢሆንም፣ አሁን ግን ህወሓት ከዚሁ አካል ጋር በመተባበር ሕዝቡን እንደ መሣሪያ ለመጠቀም እየሠራ ነው። በተጨማሪም የ1988ቱን የሐውዜን ጥቃት ትዝታ በመጠቀም ሕዝቡ በፌደራል መንግሥቱ ላይ እንዲያምፅ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እየተፈጠረ እንደሆነ የሆርን ሪቪዩ ዘገባ ያመለክታል።
በወታደራዊ በኩል ህወሓት በራያ፣ ዞብል፣ ዋጃ፣ ኮረምና በሱዳን ባሉ ኃይሎቹ በኩል የጦር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። በዚህ ስጋት ምክንያት በአላማጣ፣ ቆቦ እና ኮረም አካባቢ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የተስተጓጎለ ሲሆን፣ ብዙ ነዋሪዎችም ስጋት ስለገባቸው ወደ ሌሎች ቦታዎች በመፈናቀል ላይ ናቸው። የሆርን ሪቪዩ ሪፖርት እንደሚያስጠነቅቀው፤ መንግሥት የሕዝቡን ደኅንነት የመጠበቅ፣ የሐሰት መረጃዎችን የመመከት እና ሰላምን የማስከበር ትልቅ ኃላፊነት አለበት።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 4267 times Last modified on Wednesday, 05 August 2026 19:01